Get Mystery Box with random crypto!

+።።። ተሸክሜህ ነው ።።።።።+ ... በበርሃ ይሄድ የነበረ ሰው ወደ ኋላው ዞሮ ሲያይ ከእርሱ ሌ | ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች

+።።። ተሸክሜህ ነው ።።።።።+
...
በበርሃ ይሄድ የነበረ ሰው ወደ ኋላው ዞሮ ሲያይ ከእርሱ ሌላ አንድ ጥላ ይመለከታል:: የዚህም ጥላ ነገር አሳስቦት የማን እንደ ሆነ ያመለክተው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ።
እግዚአብሔርም :- "ከኋላህ የተመለከትከው ጥላ የእኔ ነው። አንተን እየጠበኩህ እንደሆነ ታውቅ ዘንድ ይህን ምልክት አሳየውህ" አለው። ያም ሰው ፈጣሪው ከእርሱ ጋር እንዳለ በመስማቱ እጅግ ደስ እያለው ጉዞውን ቀጠለ። ጥቂትም እንደተጔዘ ወጣ ገባ የሆነ በጣም አስቸጋሪ መንገድ አጋጠመው:: ሰውየውም ያን አስቸጋሪ መንገድ እንደ ምንም ብሎ ለመውጣት ታገለ። በትግሉ መካከል ግን ወደ ኋላው ዞር ብሎ ቢመለከት ቀድሞ ያየውን ጥላ አጣው። ከዚያም ፈታኝ መንገድ እንደ ምንም ብሎ ከወጣ በኋላ፣ በታላቅ ኃዘን ሆኖ እየተበሳጨ ፈጣሪውን እንዲህ ሲል ጠየቀው :- "ምንም ችግር ባልገጠመኝ በሰላሙ ጊዜ "ከአንተ ጋር ነኝ ስትል ጥላህን አሳየኸኝ፣ የአንተ እርዳታ በሚያስፈልገኝ ጊዜ ግን ራስህን ሰወርክብኝ:: ይከተለኝ የነበረውን ጥላም ዘወር ብዬ ባየው አጣኹት። ለምን ተውከኝ ?" ::

እግዚአብሔርም :- "በመከራህ ጊዜ ጥላዬን ያጣኸው ትቼህ እኮ አይደለም። ተሸክሜህ ነው!" ብሎ መለሰለት።

ክፉውን ዘመን በክንፈ ረድኤቱ ተሸክሞ የሚያሻግረን እግዚአብሔር ነው። እርሱ አይተወንም፤ አይንቀንም። እኛም ከእርሱ ውጭ ተስፋ የምናደርገው የለንም።

ጌታ ሆይ ስንት ዘመን ተሸክመኸኝ ምነው ተውከኝ ብዬህ ይሆን? ደካማው ልጅህን ይቅር በለኝ።

https://t.me/eotcy