2022-06-30 21:35:30
#ፍትሐ #ነገሥት #አንቀጽ #አምስት
ስለ ኤጲስ ቆጶሳት ይናገራል። ኤጲስ ቆጶስ:-
@ ጉቦ ከፍሎ የተሾመ ኤጲስ ቆጶስ ካለ ከሹመቱ ይሻር። የሾሙት ኤጲስ ቆጶሳትም ይሻሩ።
@ ከሀገረ ስብከቱ ውጪ ክህነት የሰጠ ይሻር። ከሀገረ ስብከታቸው ውጭ የሚሾሙ ካህናትም ይሻሩ።
@ በዚህ ዓለም መኳንንት እንዲሁም ነገስታት ኃይልና እርዳታ የተሾመ ይሻር።በመንግስት ትእዛዝ የተሾመ ይሻር።
@ የኃጢኣተኛን ንሥሓ አልቀበልም የሚል ኤጲስ ቆጶስ ቢኖር ይሻር።
@ አራጣ የሚቀበልና ነገር ሰርቶ ሰውን ከሰው የሚያጣላ ይሻር።
@ ዝሙት የሰራ ኤጲስ ቆጶስ ካለ ይሻር።
@ ዓለማዊ ሥራን የሚሰራ ጳጳስ ከሹመቱ ይሻር።
@ 50 ዓመት የሆነው ሰው ይሾም። 50 ዓመት የሆነው ባይገኝ ለሹመት የበቃ ሆኖ ከተገኘ ከ50 ዓመት በታች ያለውንም ይሹሙት
@ ፓትርያርኩ ሳይጽፉለት ወይም ሳይፈቅዱለት ወደ ንጉሡ የሄደ ጳጳስ ይሻር።
@ ለመፈራት ብለው ሰውን የሚደበድቡ ወይም የሚማቱ ቀሳውስት ዲያቆናት እና ጳጳሳት ይሻሩ።
@ የጠንቋዮችን ነገር አምኖ የሚቀበል እንዲሁም ኮከብ ቆጣሪ እና ለጥንቆላ ቅጠል የሚበጥስ ይሻር።
@ ከሐራጥቃ ጥምቀትን የተቀብለ ወይም የቆረበ እንዲሁም በቦታ ከእነርሱ ጋር የጸለየ ይሻር።
@ ኤጲስ ቆጶሳት የተሾሙበትን ሀገረ ስብከት ትተው በሌላ ቦታ የትንሣኤን በዓል ካከበሩ ይሻሩ።
@ ሁለት ጊዜ የተሾመ ኤጲስ ቆጶስ ወይም ቄስ ወይም ዲያቆን ይሻር።
@ ቆሞስ የኤጲስ ቆጶስ ተወራጅ ነው። በኤጲስ ቆጶስ ትእዛዝ መሰረት ይሰራል።
።
።
@ ኤጲስ ቆጶስ ቀሳውስትን ይባርክ እንጂ እርሱ በቀሳውስት አይባረክ። የክርስቶስን ሥጋውን ደሙንም ከኤጲስ ቆጶሳት ይቀበል እንጂ ከቀሳውስት አይቀበል።
@ የኤጲስ ቆጶሳት ጉባኤ በዓመት ሁለት ጊዜ ይሁን። ይኽውም ጥቅምት 12 እና ከትንሳኤ በኋላ በ28ኛው ቀን ነው። በጉባኤውም አንድ መጽሐፍ ቅዱስ በአንድ ወንበር ይቀመጥ
@ ኤጲስ ቆጶስ የተቸገሩትን ይርዳ። ሕዝቡ እየተራበ እየተቸገረ እርሱ ማእደ ሥጋውን የሚያሳምር አለባበሱን የሚያስጌጥ ጳጳስ አይባልም።
@ መሥዋእት ሠው ተው ጸሎት ጸልየው ወደ እግዚአብሔር የሚያማልዷችሁ ናቸውና ኤጲስ ቆጶሳትን አክብሩ።
@ በቀለኛ ጳጳስ ጳጳስ አይባልም።
@ በቅዳሴ ጊዜ የኤጲስ ቆጶሱን ሥም ይጥሩ።
@ ኤጲስ ቆጶሳት የበደለውን ይገሥጹ
@ ኤጲስ ቆጶሳት ያልተማሩትን ያስተምሩ ያመኑትን ያጽኑ።
@ ኤጲስ ቆጶስ ሆይ ሽማግሌዎችን አረጋጋቸው እንጂ አታሳዝን።
@ ኤጲስ ቆጶስ ሆይ ሽማግሌዎችን እንደ አባትህ ደስ አሰኛቸው። ወጣቶችን እንደ ወንድሞችህ እያቸው። ቆነጃጅትን እንደ እህቶችህ እያቸው። ባልቴቶችን እንደ እናትህ እያቸው። እናት አባት የሌላቸውንም እንደ እናት እንደ አባት ሆነህ ደስ አሰኛቸው።
@ ኤጲስ ቆጶስ አንዱንስ እንኳ ሳይመረምር መሾም የለበትም።
@ ኤጲስ ቆጶስ ከንቱ የሆነ የዚህን ዓለም ነገር አይስማ።
።
።
@ ኤጲስ ቆጶስ የላመ የጣመ አይቅመስ። የሞቀ የደመቀ አይልበስ።
@ ኤጲስ ቆጶስ ነዳያንን እየጠላ ባለጸጎችን አይውደድ።
@ ኤጲስ ቆጶስ ወደ አሕዛብ በዓል አይሂድ። በአነጋገር በሥራ ለምእመናን አርዓያ ይሁን።
@ ኤጲስ ቆጶስ ልቡ እንዳይገዝፍ ሥጋ አይብላ። ጽኑ ደዌ ከታመመ ግን ዓሣ ይብላ። ወይንም ጥቂት ይጠጣ።
@ ራሱን የሰለበ ሰው ኤጲስ ቆጶስና አይሾም። በግድ ሌሎች ሰልበውት ከሆነ ግን ከሹመት አይከልከል።
@ ኤጲስ ቆጶስ ከተሾመ በኋላ ሶስት ሱባኤ ይጹም።
@ ዕውር፣ መናገር የማይችል፣ መስማት የማይችል፣ ኤጲስ ቆጶስነት አይሾም።
@ ኤጲስ ቆጶስን ቢገኙ ሦስት ባይገኙ ሁለት ኤጲስ ቆጶሳት ይሹሙት።
@ ኤጲስ ቆጶስናን ድንግልና ከምንኩስና ያለው ሰው ይሾም። ቢታጣ ግን ሕዝባዊ ይሁን
@ ኤጲስ ቆጶስ ለሰው የሚያዝን የሚራራ፣ ልቡናው ከቂም ከበቀል ከክሕደት የተለየ፣ በበጎ ሥርዓት ሁሉ የጸና ይሁን።
።
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
336 viewsNigatu Ye Enatu Lij, 18:35