Get Mystery Box with random crypto!

ለካ ይቻላል እያስመሰሉ መሳቅ ውስጥህ እንደ እሳት እየነደደ ጥርስን ማሳየት ለካ ይቻላል አብሮህ | 🦋pic🦋

ለካ ይቻላል እያስመሰሉ መሳቅ ውስጥህ እንደ እሳት እየነደደ ጥርስን ማሳየት
ለካ ይቻላል አብሮህ ያለው ሰው በትርፍ ሰአቱ እንደሚመጣ እያወክ ደስተኛ መስለህ መኖር
ለካ ይቻላል መውደዱ የውሸት እንደሆነ እያወቅህ እወድሀለሁ ስልህ የእውነት አርጎ ማሰብ……ልብህ እውነቱን እያወቀ ውሸቱን መናፈቅ ለካ ይቻላል መጨረሻው እንደማያምር እያወቁ በንፁህ ልብ ያንን ሰው መቀበል
ግን ህመም አለው ውሸቱ አልቆ አንድ ቀን እንደሚሄድ እያወቁ የሚሄድበትን ጊዜ ትንሽ አርዝመው ጌታ ብሎ መፀለይ እየሞቱ ለመኖር እንደመጣጣር ማለት ነው