2022-02-26 06:15:15
ህይወት ደረጃ የመውጣት ወይም የመውረድ ያህል ቀላል ነች ማስተዋል ያለብን ትልቁ ነገር ግን ትክክለኛው መንገድ ላይ ነን ወይ ብለን ነው::
አንድ ጊዜ ሁለት ጓደኛማቾች የሚፈልጉት ቦታ ለመድረስ 100 ደረጃ ያለው ፎቅ ወጡ ቦታው ሲደርሱ አንዱ ጓደኛው 2 ዜና አለኝ አንዱ መጥፎ አንዱ ጥሩ ከየትኛው ልጀምር አለው:: ጓደኛውም ከጥሩው አለ እንኳን ደስ አለህ 100ኛው ፎቅ ላይ ደርሰናል መጥፎውስ ዜና ሲለው የተሳሳተ ፎቅ ላይ ነው የወጣነው::
አብዛኞቻችን እንደዛ ነን መክሊታችንን አውቀን ከውስጣችን ሳይሆን ጉዟችን የምንጀምረው በያዋጣል በያበላል በሰዎች ጫና ነው በኃላም ትክክለኛው ፎቃችን ይጠፋብናል ወይም የራሳችን ያላሆነው ፎቅ ላይ ሳንወደው እንቀጥላለን
ስለዚህ ወንድሜ የትኛው ደረጃ የትኛው ፎቅ ላይ ነህ? ራስህን መርምር ያለህበት ትክክል ካልሆነ ከፎቁ ወርደህ ትክክለኛው ፎቅህን ወይም ደረጃህን ፈልገህ ውጣ ከዛም በደስታ በስኬት ኑር
መልካም የከፍታ ጊዜ ይሁንልን!
የእናንተው እንቁ!
@EnkuEldaa
@EnkuEldaa
ለአስተያየትዎ እና ጥያቄ
@Eldako
የYoutube channelን (ELDA DIAMOND)
ወይም https://www.youtube.com/channel/UCfMXaw9_pjaleY-gOIpXDxA
ይጎብኙ
557 viewsedited 03:15