Get Mystery Box with random crypto!

ቁምነገር

የቴሌግራም ቻናል አርማ enkopawiyan — ቁምነገር
የቴሌግራም ቻናል አርማ enkopawiyan — ቁምነገር
የሰርጥ አድራሻ: @enkopawiyan
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 866
የሰርጥ መግለጫ

አሁን ትሞት በሗላ ዛሬ ትሞት ነገ ለማታውቅበት ለዚች አጭር ህይወት በቆምክበት ደቂቃ ቁምነገር ሰርተህ የነብስ ስንቅህን አዘጋጅ !
እነሆ ቁምነገር!!!
#እንቆጳውያን_ነን ከጎደለን ይልቅ ያለን እጅግ ይገዝፋል
#ለመቀበልም መስጠት ያስፈልጋል @Fekrawi
0948000004

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-05-15 07:00:58 ደህና ነኝ!

ሰላምታ ሲጠየቅ በተለምዶ ሁሉም ሰው መልሱ ደህና ነኝ ነው! እየከፋው፣ እያዘነ፣ ውስጡ ተጎድቶ፣ ለህይወት ትርጉም አጥቶ፣ ዲፕሬሽን ውስጥ ሆኖ፣ 'ደህና ነህ?' ስንለው ወግ ነውና 'ደህና ነኝ!' ይላል! እያለቀሰ ብታገኘው 'ደህና ነኝ' ይልሀል! ቆዝሞ ብታገኘው 'ደህና ነኝ!' ይልሀል... ስንት የምናቃቸው ወጣቶች ዛሬ ሰላምታ ስንሰጣቸው 'ደህና ነኝ!' ብለውን.. በንጋታው ራሳቸውን አጥፍተዋል! ስንቱ ለቅሶ ላይ ተገኝተን... ትላንትኮ፣ የዛሬ ሳምንትኮ፣ የዛሬ ወር ኮ አጊኝቼው... 'ደህና ነኝ!' ብሎኝ ነበር... ምነው ለዚህ ውሳኔ ያበቃውን ባማከረኝ ብለን አልቅሰናል ስንቱ ጠዋት 'ደህና ነኝ!' ብሎን ከሰዓት ራሱን አጠፋ ተብለናል!

ምክንያቱም እንዴት ነህ? ለሚለው የለመድነው፣ ያደግነው፣ 'ደህና ነኝ!' እያልን ነው! መርምሮ፣ ቀርቦ፣ ያለንበትን ሁኔታ ተረድቶ፣ አጥብቆ ካልጠየቀን 'ደህና ነህ?' ለሚለው መልሱ የቱን ያህል ቢከፋን፣ ብናዝን፣ መልሱ ደህና ነኝ ነው! እስኪ ራሳችንን እንጠይቅ?! ስንቱ ደህና አለመሆኑን እያወቅን.. 'ደህና ነኝ!' ስላለ ብቻ አልፈነዋል ስንቱ ራሱን ሊያጠፋ በኪሱ መርዝ፣ ገመድ ይዞ 'ደህና ነኝ!' የሚል ቃል እያወጣ ደህና አለመሆኑ ሁኔታው እያሳበቀ አልፈነው የሞቱን ዜና ሰምተናል? ደህና ነኝ! ያለ ሁሉ ደህና ነው? ደህና ነኝ! የሚል ቃልስ ደህንነትን ይገልፃል?

ስለዚህ ምናልባት ደህና ነኝ! ከሚለው ቃል ጀርባ ያለውን ህመም ተረድተን ወይም ገምተን ደህና መሆኑን አጥበቀን ብንጠይቀው..... ደህና አለመሆኑን ነግሮን... ምናልባት ላለበት ችግር መፍትሔ ማስቀመጥ ችለን ካለበት ዲፕሬሽን ወይም ራስ የማጥፋት ስሜት እንታደገው ይሆናል ኮ! እስኪ እንጠይቅ ስንቱ ሀሳቡን፣ ጭንቀቱን፣ የሚያካፍለው አቶ ደህና ነኝ! እያለ አተነዋል? ምናልባት ቤታችን ውስጥ አንድ ጣሪያ ስር እየኖርን ቀርቦ ባለመጠየቁ፣ አይዞህ ያልፋል ባለመባሉ ከባድ ጊዜን ብቻውን እያሳለፈ ነው? ከጊዜ በኋላ ወይ በሽታ ላይ ወይ ሞት ወስዶብናል? ብዙ ባለማውራታችን፣ ባለመወያየታችን፣ ባለመጠየቃችን፣ ባለመረዳታችን በአከባቢያችን ያለን ሰው እያጣን ነው?

አሁን እየተበራከተ የመጣው የወጣቶች ሱሳይድ ቀርቦ የሚጠይቃቸው አተው፣ ችግራቸው የሚያዋዩት አተው 'ደህና ነህ?' 'ደህና ነኝ!' በሚል ቃል እያለፍናቸው በጣም ከተጎዱ በኋላ ያኔ ባወራሁት ብለናል! በተለይ ጉዳታቸውን፣ ስሜታቸውን፣ ስብራታቸውን ለሰው ማዋየት ልምድ እንደሌላቸው የምናውቃቸው ምናልባት የቤተሰባችን አካልም ሊሆን ይችላል እሱ/ሷ እንደዛ ነው! እንደዛ ናት! ማውራት አትወድም፣ አይወድም ብለን አንለፋቸው! የሰው ልጅ በተፈጥሮ መፍትሔ ማግኘት ባይችል እንኳ ችግሩን በአፅኖት የሚያዳምጠው ካገኘ ይቀለዋል ማውራት በራሱ የመፍትሔው 50% ነውና!

Via: Rediet Aseffa

@enkopawiyan
@enkopawiyan


@betina21
https://youtube.com/channel/UCxka5u6a9gTqzyfgL8fRJZQ
586 views04:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-08 03:10:40
507 views00:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-05 17:04:10 ችግር ያሳድጋል!
ችግራችሁን ተጋፈጡ እንጅ አትሽሹ!

☞ ኑሮ በየቀኑ የምንወጣው ተራራ ነው ፡፡ አንዱን ጨርሰን ስንደሰት ሌላኛው ይደቀናል ፡፡ ሌላኛውን ስንወጣ የባሰው ደግሞ ይጠብቅናል ፡፡ የማያቋርጥ ስቃይ አለብን ፡፡ ስቃዩ ግን ጥሩ ነው ፡፡ ትክክለኛ አቅማችን የሚወጣው ከትክክለኛ ፈተና ጋር ስንታገል ነው ፡፡

☞ ብዙ ሰው ከፊቱ ያለውን ተራራ ግዝፈት እንጂ በውስጡ ያለውን የፈጣሪን ጉልበት አያውቅም ፡፡ ተራራው ከፊትለፊቱ ሲደቀን የሚወጣበትን መንገድ ከመፈለግ ይልቅ ማማረርን ይመርጣል ፡፡ ምክንያቱም ማማረር ቀላል ነዋ ፡፡

☞ ማለቃቀሱን ማንም ያውቅበታል ፡፡ ወደ ተራራው ጫፍ የሚወስደውን መንገድ ማግኘት ግን ከባድ ነው ፡፡ ይህ የጥቂት ጀግና ሰዎች ስራ ነው ፡፡ ላብ ፣ ደምና እንባ ማፍሰስን ይጠይቃል ፡፡ ብዙ ሰዎች ደግሞ ይህን ማድረግ አይፈልጉም ፡፡ ፈሪና ሰነፎች ናቸው ፡፡ በራሳቸው ጉልበት ፤ በፈጣሪያቸውም ሐይል እምነት የላቸውም ፡፡ ምኞታቸው ሁሉም ነገር አልጋ በአልጋ እንዲሆን ነው ፡፡ ህይወት ደግሞ ተራራ በተራራ እንጂ አልጋ በአልጋ አይደለም ፡፡

☞ ዓለም አሁን ካለችበት ከፍታ የደረሰችው በችግር ነው ፡፡ ችግር ባይኖር ? ሰዎች ዛሬም ድረስ በዋሻ ውስጥ ነበርን ፡፡ መብራት ፣ መኪና ፣ እርሻ ፣ ፕሌን ፣ ኢንተርኔት ፣ ስልክ ፣ ኮምፒውተር ፣ ቤትና ሁሉም ለሰው ልጆች ጠቃሚ የሆኑ ነገሮች የተወለዱት በችግር ምክንያት ነው ፡፡

☞ ሰዎች ችግራቸውን ለማሸነፍ ሲታገሉ ዛሬ ፍጹም ልዩ የሆነ አለም ፈጥረዋል ፡፡ ታዲያ ምስጋና ለአቶ ችግር አይገባም ትላላችሁ ? ከፊት ለፊታችሁ ያለው ተራራ ምንድን ነው ? ችግራችሁ ምንድን ነው ? ገንዘብ ማጣት? ስራ አጥነት ? የተበላሸ ትዳር ? ስደት ? በሽታ ? በራስ መተማመን ማጣት ? ሱስ ? ምንድን ነው ?

☞ ችግራችሁን የምትመለከቱትስ እንዴት ነው ? ተራራችሁን የምታዩት እንዴት ነው ? ሊያሳድጋችሁ እንደመጣ ስጦታ ? ወይስ ሊያስቆማችሁ እንደመጣ ፈተና ? ይህ የምርጫ ጉዳይ ነው ፡፡ ብዙ ሰው ችግሩን እንደ ጠላት ይመለከታል ፡፡ ችግራችሁን እንደ ወዳጅ አድርጋችሁ ካያችሁ ግን እናንተ ትክክለኛ ጀግና ናችሁ ፡፡

☞ እሱን ለማሸነፍት ስታነቡ ፣ ሰው ስታማክሩ ፣ ሞያ ስትለማመዱ ፣ ስትነግዱ ፣ ገንዘብ ስትቆጥቡ ፣ ጸሎት ስታደርጉ ፍጹም ሌላ ሰው ትሆናላችሁ ፡፡ ሌሎች ከታች ሆነው ሲያማርሩ እናንተ ከተራራው ጫፍ ትደርሳላችሁ ፡፡ ከአናቱ ሆናችሁ ንፁህ አየር ትምጋላችሁ ፡፡በከፍታው ያለውን ቪውም enjoy ታደርጋላችሁ ፡፡ ሌላ ችግር ሲጋረጥባችሁም አትደናገሩም ፡፡ ሌላ መፍትሄ ፈልጋችሁ ታሸንፉታላችሁ ፡፡

@enkopawiyan
@enkopawiyan


@betina21

https://youtube.com/channel/UCxka5u6a9gTqzyfgL8fRJZQ
518 views14:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-02 08:06:00
ውድ ቤተሰቦች ቁምነገራውያን እና መላዉ የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1443ኛው ዒድ አል ፊጥር በዐል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን መልካም በዓል

ዒድ ሙባረክ መልካም በዓል

•═••• •••═• ​​


@Fekrawi
345 views05:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-01 18:50:38
በ አለማችን ላይ ከ 4000-4300 በላይ ሀይማኖቶች አሉ ተብሎ ይታመናል::

ነገር ግን የሁሉም ሀይማኖት ቅዱስ መዝገባት አማኞቹን ለማፅደቅ ወይም ለ እምነቱ ተከታዮች በረከትን ለማደል
* Facebook
* TikTok
* Instagram
* Tweeters
* Telegram
* YouTube ....... እነዚህ እና እነዚህን የሚመስሉ የ ሶሻል ሚዲያዎች ላይ ፖስት ማድረግን መስፈርት አድርገውት አያውቁም::!

ወዳጆቼ በተለይ ፖስተኞች ስለምታምኑት ፈጣሪ ብላችሁ እባካችሁ ያላችሁበትን ሀይማኖት ለማክበርም ሆነ ከፍ ለማድረግ ሌሎች ሀይማኖቶችንም ሆነ የ እምነቶቹ ተከታይ የሆኑ አማኞችን መንቀፍ ተገቢ አይደለም ነውርም ነው::

ፖስት ማድረግ አማኝ ተቆርቋሪ አያሰኝም አያስሞግስም አያስከብርም እባካችሁ የምናመልከው አምላክ እንደየ ሀይማኖቶቹ ብዛት የተለያዩ ቢሆኑም እንኳ ለሁሉም ሀይማኖት ጠላት የሆነው ብቸኛ ጠላት #ሰይጣን ነውና በመገፋፋት በመገዳደል በመጣላት እርሱን ደስ አናሰኘው እርሱን አናገልግለው

ሀይማኖት የግል ነው ! የምንኖረው ግን በጋራ ነው እምነታችን የሚያዘንን አስተምሮ እና ህግጋት መከተል አማኝ ያሰኘናል ቀና ልባም ያስብለናል!

ሁሉም እምነቶች ውስጥ ያሉ አስተምሮቶች
* ቀናነትን
* ለጋስነትን
* ለችግረኞች ማሰብን
* ምፅዋት ማድረግን
* ተገፍቶ መክበርን እንጂ ገፍቶ መቅለልን የሚያዝ የለምና ስለምታምኑት ብላችሁ ሁላችሁም ተለመኑኝ እባካችሁ ሶሻል ሚዲያዎቻችንን ለመልካም እንጠቀምበት
የታመመ ገንዘብ ተሰብስቦ በሚታከምበትን ሶሻል ሚዲያ ለሞት ምክንያት የሆኑ ግን ተራ የሚመስሉ ፅሁፎችን ባንለጥፍባቸው መልካም ነው:: ! ለኛ ቀላል እና ስሜታችንን ማረገፊያ የሆኑ ፅሁፎች ብዙዎችን ያቀያይማል እናም እባካችሁ አማንያን እንጂ አማኝ መሳይ አጋዳዮች አንሁን !!!
1.7K views15:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-17 21:21:45
368 views18:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-17 21:21:45
329 views18:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ