Get Mystery Box with random crypto!

#የክልል_እንሁን_ጥያቄዎች_ዘላቂ_ሰላምን_በሚያመጣ_መልኩ_ሊፈቱ_ይገባል! በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከእና | እናት ፓርቲ - Enat Party

#የክልል_እንሁን_ጥያቄዎች_ዘላቂ_ሰላምን_በሚያመጣ_መልኩ_ሊፈቱ_ይገባል!
በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከእናት ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ

ሀገራችን ኢትዮጵያ ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ የተዋቀረችበት የ”ክልል” አደረጃጀት ኢትዮጵያውያን ልጆቿ ለሦስት ሺህ ዓመታት አብረው የኖሩበትን እንዲሁም በሰላምና በመቻቻል ተጋግዘው የመኖር እሴታቸውን ያጠፋና ሀገራችንን ለከፋ ችግር የዳረገ አወቃቀር መሆኑን እናት ፓርቲ በጽኑ ያምናል፡፡
ኢትዮጵያውያን ለበርካታ ዓመታት የታገሉለት ጥያቄ ኹሉንም ዜጋ በእኩልነት የሚያስተናግድና በሚናገሩት ቋንቋ፣ በሚከተሉት ሃይማኖት እና የፖለቲካ ዝንባሌ የማያገልል፣ ሀገር ያላትን በረከቶች በእኩልነትና ግልጽነት የሚያቋድስ፣ አንድነትን፣ እድገትንና ዘላቂ ሰላምን ለድርድር የማያቀርብ ሥርዓት እንዲዘረጋ እንጂ በየጊዜው ወደ እርስ በእርስ ግጭት የሚከትና ለአላስፈላጊ የሕይወት መሥዋዕትነትና ንብረት ውድመት የሚዳርግ ቀውስ ውስጥ ለመግባት አልነበረም።
ፈጣሪ ሀገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ
እናት ፓርቲ
ነሐሴ ፬ ቀን ፳፻፲፬ ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

https://www.facebook.com/105146947885320/posts/pfbid028DGZZoaL7bwk6mrT1i2zmAFwWDuZWARf8BbTwPZKU3JMeaK1U33NP1gkBXEWym5Jl/