Get Mystery Box with random crypto!

ድምፀ ተዋህዶ

የቴሌግራም ቻናል አርማ eloh_eloh_eloh — ድምፀ ተዋህዶ
የቴሌግራም ቻናል አርማ eloh_eloh_eloh — ድምፀ ተዋህዶ
የሰርጥ አድራሻ: @eloh_eloh_eloh
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.45K
የሰርጥ መግለጫ

ሰላም ለናንተ ይሁን channel አችን የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሲሆን ስብከት እና ለተለያዩ ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጡበት የተለያዩ ስብከቶች እና መንፈሳዊ ትረካ በvoice የሚያገኙበት ነው ለመቀላቀል 👇👇
@eloh_eloh_eloh
የእግዚአብሔር ሰላም የእናታች የቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃና ፀሎት የመላእክት ጥበቃና የቅዱሳን በረከት ከናንተ ጋር ይሁን
@eloh_eloh_eloh

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-06-28 17:02:44 በእግዚአብሔር ቤት እኖር ዘንድ
1.1K views14:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-28 17:00:37 ​​​​ሰኔ 21 ለሚከበረው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

#ሰኔ_20_እና_21

ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት አንዱ ነው፤ ህንጸተ ቤተክርስቲያን ይባላል።

የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን የታነጸው በዛሬዋ ቀን ነው አናጺውም እራሱ ባለቤቱ ጌታችን መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ነው፤ ቦታው ፊልጰስዩስ ነው፤ ቤተክርስቲያኗ የተሰየመችው ደግሞ በእመቤታችን ስም ነው።

ጴጥሮስ፤ ዮሐንስ በርናባስና ሌሎችም ሐዋርያት በፊልጰስዩስ ተሰብስበው ሳለ ጌታችን መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በኪሩቤል ጀርባ ላይ ሆኖ እልፍ አእላፍ መልአክትን አስከትሎ ይወርዳል እመቤታችን በቀኙ ነበረች፤ 3 ድንጋዮችን አንስቶ ጎተታቸው እንደ ሰም ተለጠጡ እንደ ግድግዳም ሆኑ ዳግመኛም የብርሃን ምሰሶ ወረደ በሰማያዊቷ እየሩሳሌም አምሳያ አድረጎ አነጻት ሁለንተናዋም ተጠናቀቀ፤ ዳግመኛ በበነጋው ሰኔ 21 ቀን እመቤታችንን እና ቅዱሳን መልአክትን አስከትሎ ይወርዳል ቅዳሴ ቀድሶ ለሐዋርያቱ አቆረባቸው ፍጹም ደስታም ሆነ።

ከዚህ በኃላ ሐዋርያት ከጌታ እንዳዩት በዓለም ዞረው ቤተክርስቲያን አንጸዋል። ከዚያ በፊት የነበረው የነሶሎሞን ቤተ መቅደስ የአይሁድ ምኩራብ የአይሁድ ስርዓተ አምልኮ መፈጸሚያ እንጂ የአዲስ ኪዳን የቁርባንም ሆነ የጥምቀት ስርዓት መፈጸሚያ አልነበረም፤ ታዲያ ሐዋርያት የት ነበር ህዝቡን የሚያጠምቁት የሚያቆርቡት ካሉ በየሰው ቤት ነበር።

ዳግመኛ በዛሬዋ ቀን ታላቁ ነብይ ኤልሳዕ አረፈ። ይህ ነብይ በ 12 ጥማድ በሬ ሲያርስ ቴስቢያዊው ነብዩ ኤልያስ ተከተለኝ አለው ምንም ሳያቅማማ ሀብት ንብረቱን ትቶ ተከተለው፤ ኤልያስ በእሳት ሰረገላ ከማረጉ በፊት ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ ይለዋል ባንተ ላይ ያደረ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ እጥፍ ድርብ ሆኖ ይደርቢኝ ይለዋል፤ እንደ ቃሉ ሆነለት ተደረገለት፤ ኤልያስ አንድ ሙት ሲያስነሳ ኤልሳዕ ሁለት ሙት አስነስቷል፤ ኤልያስ አንድ ጊዜ ባህር ሲከፍል ኤልሳዕ ሁለት ጊዜ ባህር ከፍሏል።

የእምቤታችንን የኤልሳዕ ጋን ይላታል ኤልሳ የመረረውን ውኃ እንዳጣፈጠ እመቤታችንም ይህን መራራ ዓለም ጌታን በመውለዷ አጣፍጣዋለች፤ የዚህ ነብይ ድንቅ ታሪኩ 2ኛ ነገስት ላይ በስፋት ተጽፏል ሰኔ 20 ቀን እረፍቱ ነው ቤተክርስቲያን የዛሬውን ቀን እመቤታችንን እና ነብዩን አስባ ትውላለች።

ከበዓሉ ያሳትፈን የእመቤታችን ምልጃና ረዳትነት አይለየን!

@eloh_eloh_eloh

@eloh_eloh_eloh

@eloh_eloh_eloh
1.1K views14:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 20:17:24 ( ያንተን ሙሴ ስጠን ! )

የንፁኃን ደም ሲጎርፍ ፥ ምድር በደም ታልላ
ዋይታና ጩኸት ሲበረታ ፥ የፈርዖናዊያን ግፍ ፅዋውን ሲሞላ

የራሄል እንባ ፥ ሲፈስስ ...
በልጆቹ ደም ተነክሮ ፥ የእናት አንጀት ሲላወስ
"አምላከ እስራኤል አዶናይ
የለም ወይ በዚህ ሰማይ?"
የሚል የፍጥረት ሲቃ ፥ ምድርን ሲያናውጣት

በመፅሐፍ ያነበብነው ፥ ይሄ የግፍ ጊዜ፥ የሰቆቃ ወራት
በእኛ ለኢትዮጵያውያን ሲደርስ
ፍርድ ሲገመደል ፥ እውነት በግፍ ሲታመስ ...

አገዛዝ ሲፀናብን ፥ የህዝብ ልብ ሲታወክ
ድረስልን ጌታ ፥ ሙሴን ለእኛ ላክ።

እውነት ነው ... !

የሙሴን መገለጥ ስለመራብ ፥ ስለ ፅኑ ናፍቆት ፥ ስለ ሙሴ ስስት
ባንተ ያልተቀባውን ፥ አንተ ያልሾምከውን ፥ ሙሴ ነህ በማለት
የራሳችን ሙሴ ፥ ልናቆም ፥ ቀብተን ልናነግስ
ቃላት በመደረድር ቅኔን ስንቀኝ ርሱን ስናወድስ ፥ ርሱን ስናሞግስ...

ብናሳዝንህም በዚህ ስንፍናችን
ጌታ ይቅር በለን ፥ አሁን ድረስልን
"የእኛን ሙሴ" ወስደህ ፥ "ያንተን ሙሴ" ስጠን።

#መታሰቢያነቱ ፦ ለአራት አመታት በኢትዮጵያ ለዘለቀው የንጹሐን ሰላሚዊ ዜጎች አሰቃቂ ግድያና ሀብት ንብታቸውን ተዘርፈው ለተፈናቀሉ ወገኖቼ ትሁንልኝ !

አቤቱ ክንድህ በክፉዎች ላይ ይጽና፤ በነፈሰ ገዳዮች ላይ የቅጣት ጂራፍህ ይጩህ፤ አቤቱ ግፈኞችን ተበቀል !

@eloh_eloh_eloh

@eloh_eloh_eloh

@eloh_eloh_eloh
846 views17:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-26 09:06:43
((ቅዱስ ገብርኤል )))

የሰለስቱ ደቂቅ መጠሪያ ስማቸው
ሳትመራመረው በእውነት ልጆች ናቸው
በእሳት ሲጫወቱ ከገብርኤል ጋራ
ንጉሡ ተደንቆ ለአራተኛው ፈራ
የሰለስቱ ደቂቅ ቁመት በማነሱ
ከፍ ከፍ ብለው እላይ እንዲደርሱ
ተቀጣጠሉ ሲል አዘዘ ንጉሡ
የሰለስቱ ደቂቅ ፀባይ መጠንከሩ
ወደ ፍቅር ጌታ ሄዱ በረሩ
እንደ ንጉሡ ፍርድ እንዳነጋገሩ
የጠብ ሰው ነውና ተጠብሰው በቀሩ
ናቡከደነጾር እዩት ሐሳቡን
ከምስል ቢጣሉ በዚያ ቀውጢ ቀን
የሠለሰስቱ ደቂቅ ገላጋይ ሊሆን
ይልቅ የእርሱ አሽከሮች መልካም ገላጋይ
መላ ቢስ ነው ለካ ፍጹም ወላዋይ
ከላይ ወረደ እንጂ መና ከሰማይ
ናቡከደነጾር በቁጣ ተናዶ
በሰለስቱ ደቂቅ በመሳሳት ፈርዶ
ገብርኤል ነህና ታዳጊ ለሁሉ
እስከ ሰራዊትህ ላትነጣጠሉ
ከጧት እስከ ማታ ለአምላክህ ባለሟል
እናት ኢትዮጲያን ቅዱስ ገብርኤል
እንደባቢሎን ተአምረኛ ገድል
ከአለማውያን እሳት የጦር ነበልባል
ጠላቷን አጥፋላት በበትረ መስቀል
ሲድራቅን ሚሳቅን አብድናጎን ሶስቱን
ቅድስት እየሉጣን ቂርቆስን ሁለቱን
እንደታደግሀቸው አጥፍተህ እሳቱን
ኢትዮጲያን ታደጋት አደራ
ካሰከረው ከጠላት ወረራ
ቀልድ አይወድም ሲባል ቅዱስ ገብርኤል
በዘካርያስ ላይ አፍ ይዟል በቃል
ድንግል ሀርና ወርቅ ፈትላለች በአዋጅ
ለወልድ ሙሉ ልብስ ሆኖ ሊዘጋጅ
መንፈስ ቅዱስ ነበር ድርናማግ አዋሀጅ
ገብርኤልን ልኮ አብስር አለው እንጅ !!
@eloh_eloh_eloh

@eloh_eloh_eloh

@eloh_eloh_eloh
837 viewsedited  06:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-24 10:34:39
በሀገረ እግዚአብሔር / በቅድስት ምድር /
በእመቤታችን ርስተ ምድር በሆነችው በኢትዮጵያ የሰው ልጅ ደም እየፈሰሰ ነው ፡፡
ኢትዮጵያ ሹሙ እንደ ጠፋበት ንብ ህዝቡ ከተበታተነ ሰነበተ። የሰው ሕይወት የውሻ ሕይወት ያክል ተቆጥሮባታል ፡፡
አምላክ ከ 22ቱ ፍጥረታት ለይቶ አምላካዊ ክብሩን
የሰጠው የሰው ፍጡር እየሞተም እየገደለም ነው ፡፡ ሰው ሠውን እያደነ ነው ፡፡
ከሰው ሕይወት ይልቅ ስንዝር መሬት ትልቅ ከበሬታ አግንታለች። ሁሉም ነገ ጥሎት ለሚሄድ መሬት እየተስገበገበ ነው። በዚች ሀገር የጥይት
ባሩድ እየሸተተ ነው ፡፡ ህዝቡ ደስታውን ሳያጣጥም ጥቁር ደመና እየመጣበት ነው ፡፡ በዚች ሀገር ፈሪሀ እግዚአብሔር ያለው አስታራቂ ሽማግሌ ይፈለጋል፡፡
ቅዱሳን የመነኑበት ምድር በእግዚአብሔር ቁጣ እንደ እስራኤላውያን ቤተ መቅደስ እንዳትሆን እንፈራለን፣የሙሴ ጽላት ያለባት ምድር የሶረያን እጣ እንዳታገኝ እንፈራለን። ምንግዜም ሰው ሲያጠፋ ሀገር ባድማ ትሆናለች፡፡
በፈረሱ የተማመነ ይጠፋል ይላል ነብዩ ዳዊት።
የፈርዖን ታሪክ እንዳይደገም እንፈራለን ፡፡ የሰው ደም ከባድ ነው። ትልቅ መከራ ያስከፍላል ፡፡ ሳጥናኤል ክፉ
ነው። ከላይ ከትዕቢት ተራራ ላይ ሰቅሎ ወደ ውርደት ሸለቆ ይፈጠፍጣል፡፡
ምን ይሁን ኢትዮጲያውያን እርስ
በርስ አዳኝና ታዳኝ ሆነው በደማቸው ይራጫሉ ፡፡
አንደበቱ ቅባ ቅዱስ የተቀባ መሪ እቺ ሃገር ትፈልጋለች።
870 views07:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-23 06:22:28 አቤቱ፥ ቃሌን አድምጥ፥ ጩኸቴንም አስተውል፤ የልመናዬን ቃል አድምጥ፥ ንጉሤና አምላኬ ሆይ፥ አቤቱ፥ ወዳንተ እጸልያለኹና።

በማለዳ ድምፄን ትሰማለኽ፥ በማለዳ በፊትኽ እቆማለኹ፥ እጠብቃለኹም።

አንተ በደልን የማትወድ፟ አምላክ ነኽና፤ ክፉ ከአንተ ጋራ አያድርም።

በከንቱ የሚመኩ በዐይኖችኽ ፊት አይኖሩም፤ ክፉ አድራጊዎችን ዅሉ ጠላኽ። ሐሰትን የሚናገሩትን ታጠፋቸዋለኽ፤ ደም አፍሳሹንና ሸንጋዩን ሰው እግዚአብሔር ይጸየፋል።

እኔ ግን በምሕረትኽ ብዛት ወደ ቤትኽ እገባለኹ፤ አንተን በመፍራት ወደ ቅድስናኽ መቅደስ እሰግዳለኹ።

አቤቱ፥ ስለ ጠላቶቼ በጽድቅኽ ምራኝ፤ መንገዴን በፊትኽ አቅና።

በአፋቸው እውነት የለምና፥ ልባቸውም ከንቱ ነው፤ ጕረሯቸው የተከፈተ መቃብር ነው፤ በምላሳቸው ይሸነግላሉ።

አቤቱ፥ ፍረድባቸው፥ በምክራቸውም ይውደቁ፤ ስለ ክፋታቸውም ብዛት አሳዳ፟ቸው፥ እነርሱ ዐምፀውብኻልና።

ባንተ የሚታመኑት ዅሉ ግን ደስ ይላቸዋል፤ ለዘለዓለሙ ደስ ይላቸዋል፥ እነርሱንም ትጠብቃለኽ፤ ስምኽንም የሚወዱ ዅሉ ባንተ ይመካሉ። አንተ ጻድቁን ትባርከዋለኽና፤ አቤቱ፥ እንደ ጋሻ በሞገስ ከለልኸን።
@eloh_eloh_eloh

@eloh_eloh_eloh

@eloh_eloh_eloh
883 views03:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-22 09:47:46 ( የንስሐ ግጥም ! )

አባ ስማ ድምፄን ደጅህ ቆሚያለሁኝ
የጠፋሁት ልጅህ በር እየመታሁኝ
በሀፍረት ታጥሬ እንደተሸማቀቅኩ
በፀፀት ታጅቤ እንደተኮራመትኩ
ከናፈቅኩት ቤትህ አይኔን እያማተርኩ
ቁጭ ብያለሁ ደጅህ አንተን እየጠበኩ
አባ ተመልከተኝ እንዲህ ተጎድቼ
የልጅነት መልኬን ወዜን ሁሉ አጥቼ
ካንተ የተቀበልኩት ጥሪቴን አጥፍቼ
በዚህች ወረተኛ አለም ተከድቼ
አዎን መጥቻለው ጉስቁልቁል እንዳልኩኝ
እርቃኔን ሳልሸፍን እንደተራቆትኩኝ
የህሊና እስረኛ መንገድ የጠፋብኝ
ሆኜ ቀርቻለው አለም ተጫውታብኝ
አባ ያንን ጊዜ ካንተ እንደተለየው
የዝ'ችን አለምን ጉድ ስንት ነገር አየው
ለካንስ እውነት ነው ምድር ከንቱነቷ
አያልቅም ተወርቶ ኮተታኮተቷ
አሳስቃ ወስዳ እያታለለችኝ
ይኸው አንገዋላ ከመንገድ ጣለችኝ
የምሸሸግበት ማርፍበት እስካጣ
ወዳጅ ተለውጦ እስኪሆን ባላንጣ
አይመስለኝም ነበር የጭካኔዋ ጥግ
አላስተዋልኳትም ያሻትን ስታደርግ
በርሀብ እና በጥም እየተሰቃየው
መሄድ እስኪያቅተኝ እየተንገላታው
የችግሬን ዳገት ብቻዬን ስገፋው
አልደረሰልኝም ወዳጅ ያልኩትም ስው
ግን ጥርሴን ነክሼ ሰው ለመሆን ዳግም
ስቃይ ያደቀቀው ማንነቴን ላክም
በጉልበቴ ድኼ እንዲያ ስፍገመገም
ያን ጊዜ አየሁት ፊት ለፊቴ ሲቆም
ትንሿን ተስፋዬን ድጋሜ ሊያጨልም
ለካን ውሸት ኖሯል ፍቅራችን የይምሰል
ለካን ለጌጥ ሆኗል የለበስነው መስቀል
ይሄኔ ነው ታዲያ ልቤ ቤትህን ናፍቆ
ይቅርታ ሊጠይቅ ከእግሮችህ ስር ወድቆ
የመጣው በድፍረት ተስፋውን ሰንቆ
አባ አደራህን እንዳትጨክንብኝ
በርህን ለመክፈት እንዳትዘገይብኝ
በመከራ ምክር  በጣም ስለደከምኩ
መኖር መርጫለው ለአንተ እያገለገልኩ
እንጂማ ከእንግዲህ ሌላም እቅድ የለኝ
አባ ቶሎ መተህ እንዳረከኝ አርገኝ
ወዲህ ወዲያም ሳልል ቆሚያለው በርህ ላይ
በይቅርታ አይኖችህ ዳግም እስከምታይ
ፈራ ተባ እሚለው ልቤን እየሞገትኩ
እስካሁን በርህ ለይ እንደተኮራመትኩ
ቁጭ ብያለው እና አንተን እየጠበኩ
አባ ናልኝ ባክህ ኧረ እኔስ ተጨነኩ
አንዴ ብቻ መተህ በሩን ከፍተህ ካየህ
በልጅህ መሰበር ስንቱን ታስባለህ
ግን አንድ እውነት እውቅ ከመምጣትህ በፊት
በርህን ደብድቤ ብጣራም በድንገት
አጥፍቼው ብመጣም ያንን ሁሉ ንብረት
ገንዘብ የማይገዛው ልብን ገዝቻለው
ከትናንቱ ግብሬ ዛሬ ተሽያለው
ስለዚህ ስትመጣ በሩን ልትከፍትልኝ
በዛሬ እኔነቴ እንድትቀበለኝ
ከቤት አስገብተህ አገልጋይህ አድርገኝ
ልጅህ ልባል እንደው አልሻም ከ'ንግዲህ
አገልጋይህ ሆኜ ልሩጥ ወዲያ ወዲህ
አዎን አባ መጥተህ በሩን ስትከፍትልኝ
አልሻም ድጋሜ
የአባትነት ዋጋን እንድትከፍልልኝ
ከቤታችን ካሉት ከአገልጋዮች ጋራ
እንድትፈቅድልኝ አብሬ እንድስራ
እለምንሀለው እሺ በለኝ  ባክህ
ያንን የትናንቱን ደጉን ቀን አስብህ
እንጂማ እንደግብሬ እንደ'ኔማ ቢሆን
አንተን ባለፈለኩህ ወዳጁ አውሬ ሲሆን
በቃኝ ስልችቶኛል ደክሞኛል እንግልት
በደንብ ገብቶኛል የምድር ከንቱንት
ላልመልሰው ፊቴን እርም ይሁን ብያለው
ቤትህ ነው አለሜ አባ ተምሪያለው!!!

ለሁላችንም መሃሪ ይቅር ባይ አምላካችን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለንስሐ ሞት ያበቃን አሜን !!
1.0K views06:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 13:44:53 Watch "ዘማሪ ዲያቆን ኪሮስ ይኄይስ አዲስ ዝማሬ ''ከመልአኩ ክብር የተነሳ ምድር አበራች'' ራዕ 18:1 ከቁጥር 1 ዝማሬዎቹ መካከል በቅድሚያ የተለቀቀ #rama" on YouTube


965 views10:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-16 18:09:33
@eloh_eloh_eloh

@eloh_eloh_eloh

@eloh_eloh_eloh
949 views15:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-16 18:08:10
@eloh_eloh_eloh

@eloh_eloh_eloh

@eloh_eloh_eloh
855 views15:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ