፨፨፨፨፨፨፨፨ለምን ይጥፋ ስሙ፨፨፨፨፨፨፨፨ "ወይ እሱ እብድ ነው አልያ ቀልድ ነው፣" የሚል ቃል ብቻ ነው ስለኔ ምሰማው። በውስጤ ያለውን ሀሳቤን ባነሳ፣ ሁሉም ሊፈርድብኝ፤ በቃላት ሊወግረኝ አድፍጦ ተነሳ። ሀሳብ አይደለም ወይ የሰው ልጅ ምጥቀቱ፣ ተፈጥሮን መርምሮ መኖር በህይወቱ። ለማሰብ አይደል ወይ አእምሮ ጥቅሙ፣ ታዲያ ይህ ከሆነ እውነታው ትርጉሙ፣ ሰው ባሰበ ቁጥር ለምን ይጥፋ ስሙ። ከ፦ካሌብ https://t.me/Eliyaskedir https://t.me/Eliyaskedir 507 views13:13