Get Mystery Box with random crypto!

ታዘብንሽ ታዘብንሽ ግን አለም፥ አሁንም አልሞላሽም፤ አለው ደላው ያልነውም፥ አላረፈብሽም። ዘወት | ማዕደ ሰማይ

ታዘብንሽ

ታዘብንሽ ግን አለም፥
አሁንም አልሞላሽም፤
አለው ደላው ያልነውም፥
አላረፈብሽም።

ዘወትር ከርታታ ላፍታም ዕረፍት የለሽ
መሽቶ እየነጋም አለሽ ተቅበዝብዘሽ።

መላ ያልሽው ፈጥሮ ቁስል
ያኖርሽውን ሲያመሳቅል

ጠቢባንሽ ደም ሲያቃቡ
ጎዳኖችሽ ሰላም ጤና እንደተራቡ
ሳቅሽ ራሱ ሀዘንሽን እያሳበቀ
ሀሴት ከአንቺ እንደራቀ።

በቅብ ምስል በሽውሽው
ያጀበሽን እያሳወርሽው
እያታለልሽው
በአቦ ሰጠኝ እየመራሽው

ዛሬም ወናፍ ከንቱ ለፊ
በሞት መንገድ ህይወት ሽቶ ተሰላፊ
እውነት አልባ ወሸት ሰፊ
በሺ ዘመን ለሺ ዘመን ነሽ ቀጣፊ

ታዘብንሽ አለም ታዘብንሸ

ይብላኝ እንጂ
አንቺን
ዛሬም ድረስ በልቡናው ላደመቀ
የተናቅሽውን ላገዘፈ
ውጥን ስርሽን ላላወቀ።

እኛስ ለይተናል ሰፊውን ከጠባብ
መንገድ አንስትም ተወጥረን በሀሳብ።

በህይወት ጎዳና በጠበበው ገብተን
የታረደውን በግ
ክርስቶስ ኢየሱስን እንጠብቃለን።


━━━━⊱✿⊰━━━━━
@elgraceministry
@elgraceministry