Get Mystery Box with random crypto!

እውነተኛ ስሜት❤️‍🔥

የቴሌግራም ቻናል አርማ eiduka — እውነተኛ ስሜት❤️‍🔥
የቴሌግራም ቻናል አርማ eiduka — እውነተኛ ስሜት❤️‍🔥
የሰርጥ አድራሻ: @eiduka
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 431
የሰርጥ መግለጫ

@Eiduka ቻናል ገራሚ
#ፎቶዎች 📂
#የፍቅር_መልክቶች📜
#ቪዲዮ 📀
#ደብዳቤዎች📝
#የልብን_የሚናገሩ_ሙዚቃዎች 🎶🎶
#ሌሎችንም..........
Administrators & create
👇👇👇👇 👇👇👇
@MarH_23 @eiduka23
Join&share
Be happy
Be smile

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-12-18 16:43:25
____

ራስህን ስጋት አታድርግ፡፡ መልካም ሰው ማንንም አያማርርም ። ያለፍቅር ሕይወት ዋጋ የለውም ፡፡ ፍቅር የሕይወት ውሃ ነው ፣ ፍቅርን የሚያቅ ሰው የነፍስ መብራት ነው። ሁሉም ነገር እና ሁሉም ሰው ከማይታዩ ብዙ ህብረቶች ጋር የተሳሰረ ነው።

ምን ዓይነት ፍቅርን መፈለግ እንዳለብህ አትጠይቅ…የምስራቃዊ ወይም ምዕራባዊ እያልክ ክፍፍል አትፍጠር፣ ያንተ ክፍፍሎች ወደ ብዙ መከፋፈል ከማምራት በቀር አንተን አይቀይሩህም፡፡ ፍቅር ስያሜ የለውም ፣ ትርጓሜ የለውም፡፡ንፁህ እና ቀላል ነው።

የሰዎችን ልብ አትስበር ፡፡ከአንተ ይልቅ ደካማ እንደሆኑ አርገህ ቁልቁል አትመልከት፡፡በአንደኛው የዓለም ክፍል ውስጥ ያለ ሀዘን መላውን ዓለም ሊያሰቃይ ይችላል ፣በዛው ልክ ደግሞ የአንድ ሰው ደስታ እና ፈገግታ መላውን ዓለም ፈገግ ሊያደርገው ይችላል።

አብዛኛዎቹ ግጭቶች እና ውጥረቶች በቋንቋ ምክንያት የሚከሰቱ ናቸው።ለቃላቶች በጣም ትኩረት ስጥ ፣ በፍቅር ሀገር ውስጥ ቋንቋ የራሱ የሆነ ቦታ የለውም።
ፍቅር ውብ ዝምታ ነው ፡፡
ከፍቅር ሌላ ምንም ዕዳ አይኑርባችሁ!!


@eiduka
41 views13:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-18 16:41:55 አለሜ ነሽ እድል ክፍል 38 """ """ """ """ ሄዋን፣አዳምና ቦስም ተኝተው ስለነበረ መልክቱን አላዩትም። ዲና በጠዋት ውሀ እረጭታ ስታስነሳቸው እንጂ አስደንጋጭ መልክት በስልካቸው ልካላቸው አንብበው አያውቁም....ሄዋን ከእንቅልፎ እንደነቃች የሌሊት ልብሷን ቀይራ ወደ ሳሎን ሄደች። ስልኳን ከእስማርት ቲቪው ጋራ አገናኝታ የዘወትር ልምዷን የሆነውን በጠዋት መዝሙር የመስማትና አብራ…
36 views13:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-23 14:58:48 ሰዎች የነዱት ሰው ጸጸት

“ሌሎች ሰዎች ከእኔ የሚጠብቁብኝን ሳይሆን እኔው ራሴ ያመንኩበትን ሕይወት የመኖር ድፍረት ኖሮኝ ቢሆን ኖሮ!”

ብሮኒ በመጀመሪያ የምትተርከው ግሬስ ስለምትባል በታላቅ ጸጸት ውስጥ ስላለች ሴት ነው፡፡ ግሬስ ከሃምሳ አመታት በላይ በጋብቻ ሕይወት አሳልፋለች፡፡ ግሬስ ከልቧ ከምትወዳቸው ልጆቿ ከምታገኘው ደስታ ባሻገር “የአስራዎቹ” አመታት ወጣት የልጅ ልጆች ማግኘቷ የማይጠገብ የደስታ ምንጭ ሆኖላታል፡፡ ሆኖም፣ ይህ ደስታዋ ሙሉ እንዳይሆን ያደረገባት አንድ ጥቁር ነጥብ ግን በሕይወቷ ነበር፡፡ ይህም ሁኔታ የባለቤቷ ጉዳይ ነበር፡፡

አምባ ገነንና ጨካኝ የሆነው ባለቤቷ ባሳለፉት አመታት ውስጥ ጋብቻን አስቸጋሪ ያደረገባት ሰው ነበር፡፡ ወደጋብቻ ከመጡበት እለት ጀምሮ የቅስም ሰባሪ ቃላትና የተለያዩ የክፉ ተግባሮች ሰለባ አድርጓታል፡፡ ይህንንም ሁኔታውን ለማስተካከል መውሰድ የነበረባት እርምጃዎች እንዳሉ ብታውቅም፣ አንዱንም ምርጫ ለመውሰድ ድፍረቱ ሳይኖራት ለአመታት ተቀጥቅጣ ኖራለች፡፡ የባለቤቷ አስቸጋሪነት እጅግ ከመክፋቱ የተነሳ ከጥቂት አመታት በፊት ከእርጅና የተነሳ በአረጋውያን መጦሪያ ማእከል በመግባቱ እርሷ ብቻ ሳትሆን ሁኔታውን የሚያወቁ ሰዎች ሁሉ ደስተኛ ነበሩ፡፡

ግሬስ በትዳር አመታቶቿ በሙሉ አንድ ቀን ከባሏ ክፉ ተጽእኖና ጨካኝ ሁኔታ ውጪ ሆና ደስተኛ ሕይወትን ለብቻዋ የምታጣጥምበትን ቀን እንደናፈቀች ኖራለች፡፡ አሁን በሰማኒያዎች አመታት ውስጥ ብትሆንም፣ ለእድሜዋ የሚመጥን መጠነኛ ጤንነትና የአካል ብቃት ነበራት፡፡ ወደማእከሉ ስትመጣ ወዲህ ወዲያ ለማለት የሚያበቃት አቅም ነበራት፡፡

እድሜዋን በሙሉ “በድብደባ” ያሳለፈው አእምሮዋ አሁን ለዚህ ሁኔታ ከዳረጋት ባለቤቷ በመለየቷ ምክንያት የእረፍትን ጭላንጭል ያየ ይመስላል፡፡ ለብዙ ዘመናት የጠበቀችውን ይህንን ለብቻ የመሆንና ካለምንም የውጪ ሰው ተጽእኖ የማሰብ “ነጻነት” ባገኘች በአጭር ጊዜ ውስጥ በድንገት በጽኑ መታመም ጀመረች፡፡ ሕመሙ ከተሰማት ከጥቂት ቀናት በኋላ ብዙም እድሜ እንደማይኖራት የሚጠቁም ምልክት ተገኘባት፡፡ ሁኔታውን እጅግ ልብን የሚሰብር ያደረገባት፣ የህመሙ መንስኤ ለብዙ አመታት ባለቤቷ በቤት ውስጥ ሲያጨስ ከነበረው የሲጃራ ጭስ እንደሆነም ማወቋ ነው፡፡ የበሽታው ደረጃ እጅግ ከመክፋቱ የተነሳ በአንድ ወር ውስጥ አቅሟን ሁሉ አጥታ የአልጋ ቁራኛ ሆነች፡፡

“ለምን ያንን ዘመን ሁሉ እኔ ያመንኩበትንና የፈለግሁትን ነገር አላደረኩም? ለምን እንደፈለገ እንዲገዛኝና እንዲያንገላታኝ ፈቀድኩለት?” የሚሉት ጥያቄዎች ካለማቋረጥ ከግሬስ አንደበት ሲወጣ ይደመጥ ነበር፡፡ ያመነችበትን ትክክለኛ ሕይወት ለመኖር ድፍረት ሳይኖራት ዘመኗ በማለፉ ምክንያት በራሷ ላይ እጅግ በጣም ትበሳጭ ነበር፡፡ ልጆቿም ቢሆኑ እንደፈለገ ባደረጋትና ባደረገባት ባሏ ምክንያት ስላሳለፈችው ከባድ ሕይወት በግልጽ ይመሰክሩ ነበር፡፡

“አንቺ ማድረግ የምትፈልጊውን ትክክለኛ ነገር ከማድረግ ማንም ሰው እንዲከለክልሽ አትፍቀጂለት” በማለት ለተንከባካቢዋ ለብሮኒ ደጋግማ ትነግራት ነበር፡፡ “እባክሽን ይህንን እኔ የሰራሁትን ስህተት እንዳትሰሪ ቃል ግቢልኝ” በማለት ታሳስባት ነበር፡፡ አንድ ቀን ግሬስ ይህንኑ ምክር ደግማ ከነገረቻት በኋላ፣ ብሮኒ በእሺታ ምክሯን ተቀብላ እንደምትተገብረው ቃል በመግባት፣ “ራስን የመቻልና ያመኑበትን ትክክለኛ ነገር የማድረግን ትምህርት ያስተማረችኝ እናት ስለነበረችኝ እድለኛ ነኝ” በማለት ለግሬስ ነገረቻት፡፡

“አሁን ያለሁበትን ሁኔታ ተመልከችው” አለች፣ ግሬስ በመቀጠል፡፡ “በመሞት ላይ ነኝ፡፡ በሞት አፋፍ! እንዴት ቢሆን ነው እነዚያን አመታት ሁሉ ነጻና ራሴን የቻልኩ ሆኜ ለመሆን ስጠብቅ ኖሬ፣ አሁን እዚያ የተመኘሁበት የሕይወት ምእራፍ ላይ የደረስኩ ሲመስለኝ ጊዜው ያለፈብኝ?” እነዚህን መራራ ቃላት የሰማችው ብሮኒ የግሬስ ሁኔታና ጸጸት እንድታስብ ያነሳሳትን እውነታ ማሰላሰል ጀመረች፡፡

የደረሰችበትም ድምዳሜ፣ “ማንኛውም ሰው የራሱን አመለካከት ማወቅ፣ ትክክለኛውን መንገድ መለየትና ያንንም ያመነበትን ትክክለኛ ጎዳና መከተል አለበት” የሚል ነበር፡፡

ግሬስ በውስጧ የምታምንበትንና የሚሰማትን ስሜት ሳይሆን የዚያን ተቃራኒ ገጽታን በውጪ እያንጸባረቀች ዘመኗን አባከነች፡፡ እድሜዋን በሙሉ እርሷ ያመነችበትንና ከነበረባት የጭካኔ ሰለባ የሚያወጣትን ሕይወት ሳይሆን ሌሎች ሰዎች ከእርሷ የሚጠብቁባትን አይነት ሕይወት ስትኖር ካሳለፈች በኋላ፣ አሁን በመጨረሻዎቹ አመቶቿ ምርጫው የእርሷ እንደነበርና፣ ፍርሃት ከትክክለኛው ምርጫ እንደገታት ተገነዘበች፡፡ ራሷን ይቅር የማለት አስፈላጊነት ቢነገራትም እንኳን አሁን ሌላ ምርጫ ያለውን ሕይወት ለመኖር ጊዜው ያለፈባት መሆኑን ስታስብ ከአቅሟ በላይ የሆነ ስሜት ይወርሳታል፡፡

ብሮኒ በሞት አፋፍ ላይ ያሉ ሰዎች በሚኖሩበት ማእከል ውስጥ ስትሰራ ካጠናቻቸው የሰዎች ጸጸቶች ይህኛው፣ “ሌሎች ሰዎች ከእኔ የሚጠብቁብኝን ሳይሆን እኔው ራሴ ያመንኩበትን ሕይወት የመኖር ድፍረት ኖሮኝ ቢሆን ኖሮ!” የሚለው ጸጸት አብዛኛዎቹን ሰዎች የሚያጠቃውና ቀንደኛው ነው፡፡ ብዙ ሰዎች የሕልማቸውን ግማሽ እንኳን ሳያጣጥሙ ዘመናቸው የሚያልፈው ያመኑበትን ትክክለኛ የሕይወት አቅጣጫ ለመከተል ምርጫ እንዳላቸው ካለማወቅና ወይም ትክክለኛውን ምርጫ እያወቁ ያንን ምርጫ ለመከተል ጉልበት ከማጣት የተነሳ ነው፡፡

ዶ/ር እዮብ
@eiduka
258 views11:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-23 14:58:47 መውደዴ ካልቀር ላንተ መገዛቴ
ማፍቀሬም ከሆነ የኔማ ስህተቴ
መታረም ካለብኝ እገዛልሀለሁ
ምክርና ስድብህን እቀበለዋለሁ ፍቅር ሀያል መሆኑን ካንተ ተምርአለሁ

@eiduka23
@eiduka
241 views11:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-20 15:47:26 ስብዕና ፍቅር ከሌለ ይታመማል። ስብዕና ፍቅር ከሌለ ይሞታል። ፍቅር ሌሎችን መርዳት ሌሎችንም መረዳት ነው።

ሁሉም ሰው እውነተኛ አፍቃሪ ይፈልጋል፤ ነገር ግን በእውነት ማፍቀር ይፈራል። ሁሉም ሰው ትክክለኛውን ሰው ይፈልጋል፤ ራሱ ግን ምንም ትክክለኛ የመሆን ሙከራ አያረግም።

አንተ መፈቀርና መደነቅ እንደምትፈልግ ሁሉ ሌላውም መደነቅና መፈቅር ይፈልጋል። ማፍቀር እና ማድነቅ ሳትችል መፈቀርና መደነቅ የምትሻ ክሆነ እራስ ወዳድና አላዋቂ ሰው ትሆናለህ።

ፍቅርን እንስበክ፤ ፍቅር ይለምልም፤ ፍቅር ይፋፋ፤ ፍቅር ይፍካ፤ ፍቅር ይግዛን፤ ከፍቅር ውጪ አንድ እርምጃ አናንሳ፤ በፍቅር ስም እንኑር።
Edel
@eiduka
@eiduka23
291 views12:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-20 15:46:19
#አናግሩልኝ
ሀገር ምድሩ ፡ፌሽታ ገጥሟል ፡ባለዉ ነገር ፣
እኔ ሞኟ፡ መሃል ቆሜ፡ መደናገር ።

ፍቅሩን ይዞ
ሲረዳዳ፡ ሲጠቃቀም፡ ሲለጋገስ ፣
እኔ በእርሱ፡ መላ እንዳጣ፡ ስቅለሰለስ ፣

ያ አይናዉጣ ፡
የሰላሜ እዉን ቀሚ፡ ልዩ አማላይ ፣
ምን ነክቶት ነዉ ፡
ረግጦኝ የሚያልፍ፡ በላዬ ላይ ።

~እባካችሁ ወዳጆቼ~
ልቤን በልቶ፡ በዝምታ ፡ በሀሳቤ ላይ ለነገሰዉ ፣
ሁሉም ቀርቶ፡ አናግሩልኝ፡ ያን ክፉ ሰዉ ።
edel
@eiduka23
@eiduka
292 views12:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-20 15:46:19
#አልፎ_አልፎ_መሞት
#ኤልያስ_ሽታኹን

ሰው
አንድም - በእግዜር፡
አንድም - በመውዜር፡
እያዋሀደ የዕድሜውን አመል፡
ማታ በውስኪ ጠዋት በጠበል።

ሰው ቢያጣ መንገድ ሰው ቢያጣ ምርጫ፡
ተከፋፍለው ተስፋን ለቅርጫ።

ተመዳደቡብኝ የመኖሬን ኮታ፡
አንድ ላይ ለበሱት ነፍሴን እንደኩታ።

እኔ ግን፡
ይጥቀማቸው ብዬ አልተወው መኖሬን፡
ብረግፍም አለሁኝ እድሜ ይስጠው ስሬን።

ሰው
ይመስለዋል እንጂ መተንፈስ አክራሞት፡
ስንቱን ያሻግራል አልፎ አልፎ መሞት።


@eiduka
207 views12:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-20 09:21:49 ፍቅርና ጊዜ

ሁሉም አይነት ስሜቶች የሚኖሩበት አንድ ደሴት ነበር፡፡ የደስታ ስሜት፣የመከፋት ስሜት፣ እውቀት እና ሌሎቹ ስሜቶች ፍቅርን ጨምሮ፡፡ አንድ ቀን ታዲያ ደሴቱ ሊሰምጥ እንደሆነና ሁላቸውም ስሜቶች ሊያመልጡ የሚችሉበትን ጀልባ መስራት እንዲችሉ አዋጅ ተነገረ፡፡ በዚህም መሠረት ሁሉም ስሜቶች ጀልባቸውን ሲሰሩ ፍቅር ግን ደሴቱ እስኪ ሰምጥ ድረስ ጀልባ አልሰራም ነበርና ከሊሎቹ ስሜቶች እገዛ ለመጠየቅ ወሰነ፡፡

ሀብታምነት የሚባለው ስሜት በፍቅር በኩል ሲያልፍ “ሀብታም ሆይ ከአንተ ጋ ይዘኸኝ ልትሻገር ትችላለህ?” አለው ፍቅር፡ “አይሆንም፡፡ አልችልም በጀልባየ ውስጥ በርካታ ወርቅና መዳብ የያዝኩ በመሆኑ ለአንተ የሚሆን ቦታ የለኝም” ሲል ጥሎት ሄደ፡፡ ፍቅር አቶ ስግብግብን ሲያልፍ ተመለከተውና እንዲረዳው ጠየቀው፡፡ “አልችልም አቶ ፍቅር ጀልባየን ታበላሽብኛለህ አይሆንም ብሎ” ትቶት ሄደ፡፡ አቶ መከፋትን በቅርብ አገኘውና አሁንም ፍቅር አብሮ እንዲያሻግረው ጠየቀው፡፡ “ኦው! ፍቅር አዝናለሁ እኔ ብቻየን ነው መሆን የምፈልገው፡፡” ብሎ አሰናበተው፡፡ ደስታም ፍቅርን አልፎት እየሄደ በጣም በፈንጠዝያ ደስታ ላይ ስለነበር ፍቅር ሲጠራውም መስማት አልቻለም፡፡ ባጋጣሚ “ፍቅር ና እኔ እወስድሃለሁ” የሚል ድምጽ ሰምቶ ሲዞር የተባረከ አዛወንት ነበር፡፡ “ጊዜው ነው” ወዳጀ ፍቅር ሲል እውቀት የተባለው ስሜት መለሰ፡፡ “ጊዜ ማለት!?” ፍቅር በመደነቅ ጠየቀው “ነገር ግን ለምን ጊዜው ሊረዳኝ ቻለ?” እውቀት ፈገግ እያለ ምክንያቱም “የፍቅርን ዋጋ መረዳት የሚችለው ጊዜ ነው፡፡” ሲል መልስ ሰጠው፡፡
Edel_
@eiduka23
@eiduka




መልካም ሰንበት ይሁንላቹ
228 views06:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-20 09:21:35
መልካም እለተ ሰንበት ይሁንላችሁ
171 views06:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-19 20:51:02 ሰዉስ አይደለህም

በሰማሁኝ ቁጥር የዝናቡን ኮቴ
በደስታ ይሞላል የደረቀው ፊቴ
ያለ ይመስለኛል መንፈስህ ከፊቴ
የማታውን ተወው ጭራሽ ጨልላለሁ
ሲያሻኝ እስቃለው
ሲያሻኝ አለቅሳለው
ከትራሴ ጋራ ሳልሳ ደንሳለው
ከጎኔ አንተ እንዳለህ በሀሳቤ ስላለው
መልሼ አለቅሳለው እነፋረቃለው


በዝናቡ ኮቴ የምታሳስቀኝ
የማታ የማታ የምታጃጅለኝ
ቁጭባልኩኝ ቁጥር ትውስ የምትለኝ
ሰውስ አይደለህም ሰው ነኝ አትበለኝ

Edel
@eiduka
188 views17:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ