Get Mystery Box with random crypto!

Ethiopian Electric Utility

የሰርጥ አድራሻ: @eeuethiopia
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 24.33K
የሰርጥ መግለጫ

EEU Official Telegram Channel
Web: www.eeu.gov.et

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-05-11 09:20:25
ውድ የድህረ-ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞቸቻችን ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብዎን #በቴሌና ንግድ ባንክ በኩል ከተዘረጉ ዘመናዊ የክፍያ አማራጮች በተጨማሪ #በአዋሽ ብር ፕሮ ይክፈሉ፡፡

የፍጆታ ሂሳብዎን በተዘረጉ ዘመናዊ የክፍያ አማራጮች ሲፈፅሙ ጊዜዎን፣ ጉልበትዎን እንዲሁም ገንዘብዎን ይቆጥባሉ፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
5.8K views06:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-10 14:38:05
የጥገና ስራ ለማከናወን ሲባል የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት

ነገ ግንቦት 3 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10:00 ሰዓት ድረስ በአዲስ አበባ ጦር ኃሎች ሆስፒታል፣ መኮንኖች ክበብ፣ ገዳመ ኢየሱስ፣ ፅዮን ሆቴል ፣ ሰሜን ማዘጋጃ ፣ 6 ቁጥር ማዞሪያ ፣ መርሐቤቴ ሆቴል አካባቢ፣ በላይ ዘለቀ ት/ቤት አካባቢ፣ ድልበር እና አካባቢዎቻቸው የኤሌክትሪክ መስመር ጥገና ስራ ለማከናወን ሲባል የኃይል አቅርቦቱ ሙሉ በሙሉና በከፊል ይቋረጣል፡፡

ስለሆነም ከላይ በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን የኃይል አቅርቦቱ እንደሚቋረጥ አውቃችሁ ከወዲሁ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
5.9K views11:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-10 10:18:31
ለጥገና ስራ ሲባል የኃይል አቅርቦቱ ይቋረጣል

ነገ ቅዳሜ ግንቦት 3 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 12:00 እስከ ምሽቱ 12:00 ድረስ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል 132 ኪ.ቮ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ተሸካሚ መስመር ላይ የጥገና ስራ ስለሚያከናውን በድሬዳዋ፣ ሀረማያ፣ ሐረር፣ ጅጅጋ፣ ደገሀቡር፣ ፊቅና አካባቢው የኃይል አቅርቦቱ ይቋረጣል፡፡

ስለሆነም ከላይ በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን የኃይል አቅርቦቱ እንደሚቋረጥ አውቃችሁ ከወዲሁ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
5.7K views07:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-05-10 09:48:53
የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት የመስመር ማዛወር ስራ ተጠናቀቀ

የአዲስ አበባ ከተማ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የኮርደር ልማት የኤሌትሪክ መስመር ማዛወር እና መልሶ ግንባታ ስራ አጠናቆ ለደንበኞች አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡

በመስመር ማዛወር ስራው የልማት ተናሺ ለነበሩ 2 ሺ 7 መቶ ደንበኞች በአዲስ መልክ በሰፈሩበት አካባቢ አዲስ ኃይል የማገናኘት ስራ ተከናውኗል፡፡

የኃይል መስመር ማዛወር ስራው አጠቃላይ 68 ኪ.ሜ የሚሸፍን ሲሆን፤ በቀጣይ የኃይል መቆራረጡን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲቀንስ ታሳቢ በማድረግ 50 ኪሜ የመካከለኛ እና 18 ኪ.ሜ የዝቅተኛ ኃይል ተሸካሚ መስመር ላይ ማሻሻያ ተደርጓል፡፡

ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ማስፈንጠሪያውን ተጭነው ያንብቡ!!
http://www.ethiopianelectricutility.gov.et/news/detail/771?lang=am
5.6K views06:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 10:28:20
በከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ በተገዙ የኤሌክትሪክ #መሰረተ-ልማቶች ላይ የሚፈፀም ስርቆትና ውድመት በተቋሙ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ አሉታዊ ተፅኖ ከማሳደሩም በላይ በቴሌ ኮሚኒኬሽንና የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማት አውታሮች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 464/97 መሰረት በህግ ያስጠይቃል፡፡አዋጁን ተላልፎ ድርጊቱን የፈፀመ ማንኛውም አካል ከ5 ዓመት እስከ 20 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት የሚቀጣ ይሆናል፡፡

ስለሆነም ይህን መሰል እኩይ ተግባር የምትፈፅሙ አካላት ከድርጊታችሁ እንድትቆጠቡ እያሳሰብን፤ በየደረጃው የሚገኘው የህብረተሰብ ክፍልም የኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶችን እንደራሱ ንብረት አድረጎ ሊጠብቅና በኤሌክትሪክ መሰረተ-ልማቶች ላይ ጉዳት የሚያደርሱና ስርቆ የሚፈፅሙ ግለሰቦችን ሊመለከት በአካባቢው ለሚገኝ የፀጥታ አካላት በማሳወቅ ሃገራዊ ሃላፊነታችንን ሊወጣ ይገባል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ ይህንን ድረ-ገፅ ይመልከቱ፡ http://www.eeu.gov.et
1.3K viewsedited  07:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 18:26:22
የኦፍግሪድ ፕሮጀክት የግብዓት አቅርቦት ግዥ ውል ስምምነት ተፈረመ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ከዋናው የኤሌክትሪክ መረብ /ግሪድ/ ርቀው የሚገኙ 70 የገጠር ከተሞችን ከፀሃይ ኃይል የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችል የግብዓት አቅርቦት ግዥ ውል ስምምነት ትናንት ሰኔ 26 ቀን 2015 ዓ.ም ተፈራረመ፡፡

የግዥ ውል ስምምነቱ የተፈረመው ከኤክስ ጀ ግሩፕ ኮርፖሬሽን ኤንድ ሻንዶንግ ኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግና ኢኩይፖመንት ግሩፕ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ ጋር ነው፡፡

ስምምነቱን የፈረሙት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሽፈራው ተሊላ እና የኤክስ ጀ ግሩፕ ኮርፖሬሽን ኤንድ ሻንዶንግ ኤሌክትሪካል ኢንጂነሪንግና ኢኩይፖመንት ግሩፕ ተወካይ ናቸው፡፡

የግዥ ስምምነቱ አጠቃላይ ወጪ አምስት ሚሊዮን አምስት መቶ ሠላሳ ስድስት ሺሕ ዘጠኝ መቶ ስልሳ ዘጠኝ ዶላር ወይም ሁለት መቶ አርባ አራት ሚሊዮን ሦስት መቶ ዘጠና አራት ሺህ አራት መቶ ብር ነው፡፡

ስምምነቱ የተፈረመው በመላ ሃገሪቱ የሚገኙ 70 የገጠር መንደሮችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ የሚያደርጉ የመካከለኛና የዝቅተኛ ዲስትረቡሽን ኔትወርክ ለመገንባት የሚያስችል የግባዓት አቅርቦት ግዥ ለመፈፀም ነው፡፡

በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ ዋና ስራ አስፈጻሚው ጨምሮ ከሁሉት ተቋማት የሚመለከታቸው የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ ይህንን ድረ-ገፅ ይመልከቱ፡ http://www.eeu.gov.et
2.9K views15:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 17:25:49
16 የገጠር ቀበሌዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ሆኑ

በአማራ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት በባህርዳር ዲስትሪክት ስር ያሉ 16 የገጠር ቀበሌዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ ሆኑ፡፡

በክልሉ የአገር አቀፍ ኤሌክትሪክ አቅርቦት ፕሮግራም የባህርዳር ዲስትሪክት ማስተባበሪያ በ2015 በጀት ዓመት 10 የገጠር ቀበሌዎችን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ አቅዶ ባከናወነው ስራ ሁሉም ቀበሌዎች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡

በተጨማሪም ባለፈው በጀት ዓመት ግንባታቸው ያልተጠናቀቁ የ6 ቀበሌዎችን ግንባታ በማጠናቀቅ በአጠቃላይ በ16 ቀበሌዎች ለሚገኙ 6 ሺ 412 ነዋሪዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎትን ተደራሽ ማድረግ ተችሏል፡፡

እነዚህን የገጠር ቀበሌዎች የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ለማድረግ 153 ነጥብ 4 ኪ.ሜ የመካከለኛ መስመር እንዲሁም 196 ነጥብ 1 ኪ.ሜ የዝቅተኛ መስመር ዝርጋታ የተሰራ ሲሆን የ36 የተለያየ አቅም ያላቸው የትራንስፎርመሮች ተከላ ስራም ተከናውኗል፡፡

በከፍተኛ ወጪ የተገነባውን ይህን የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት የአካባቢው ህብረተሰብ እንደ ራሱ ንብረት እንዲጠብቅ እንዲሁም ህገወጥ ተግባር ሲፈፀምም ከተቋሙና ከፀጥታ ሀይሎች ጋር በመተባበር ወደ ህግ በማቅረብ ረገድ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ማስተባበሪያው አሳስቧል።

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት
ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ ይህንን ድረ-ገፅ ይመልከቱ፡ http://www.eeu.gov.et
2.9K views14:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 10:39:52
በማሰራጫ ጣቢያ ላይ ባገጠመ ብልሽት የተቋረጠ የኃይል አቅርቦት

በአምቦ ዲስትሪክት በጌዶ የኃይል ማሰራጫ ጣቢያ ላይ ባገጠመ የቴክኒክ ብልሽት ምክንያት አምቦ፣ ጉደር፣ ድሬ እንጭኒ፣ ሜጢ እና አስጎሪ ከተሞችና በዙሪያቸው በሚገኙ አካባቢዎች የኤሌክትሪክ ኃይል ለጊዜው ተቋርጧል፡፡

ስለሆነም ከላይ በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን ይህንን ተገንዝባችሁ ከወዲሁ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ በአክብሮት እንገልጻለን፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ ይህንን ድረ-ገፅ ይመልከቱ፡ http://www.eeu.gov.et
3.2K views07:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-04 10:30:55
ውድ የድህረ ክፍያ ደንበኞቻችን፤ የተጠቀማችሁበትን የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳብ በተዘረጉ የክፍያ አማራጮች በመጠቀም ይፈፅሙ፡፡ #ዘመናዊ የክፍያ አማራጮችን ሲጠቀሙ አስፈላጊ ካልሆነ ወጪና እንግልት ያድናል! ኑሮንም ያቃልላል! በጥሬ ገንዘብ ለመክፈል ወደ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት በመምጣት ጊዜዎትን፣ ጉልበትዎትንና ገንዘብዎትን አያባክኑ፡፡ ካሉበት ሆነው በተዘረጉ ቀላልና ዘመናዊ የክፍያ አማራጭ ብቻ ይጠቀሙ!

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ ይህንን ድረ-ገፅ ይመልከቱ፡ http://www.eeu.gov.et
3.2K views07:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-03 11:35:03
ለተቋሙ ቁልፍ ደንበኞች አገልግሎት የሚሰጥ ነፃ የጥሪ ማዕከል ስራ ሊጀመር ነው

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለተቋሙ ቁልፍ ደንበኞች አገልግሎት የሚሰጥ 904 የተሰኘ ነፃ የጥሪ ማዕከል ስራ ሊያስጀምር መሆኑን በተቋሙ የደንበኞች አገልግሎትና ቴክኒካል ሳፖርት ዳሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መንግስቱ ካሴ ገለፁ፡፡

የጥሪ ማዕከሉ ከ160 ኪ.ዋ በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ከተቋሙ አስፈቅደው የሚጠቀሙ እንዲሁም ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና ፖለቲካዊ ፋይዳቸው ከፍተኛ ለሆኑ ተቋማት አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

በጥሪ ማዕከሉ አገልግሎት የሚያገኙ 22,565 ቁልፍ ደንበኞችን የመለየትና ደንበኞቹ 904 የጥሪ ማዕከል ላይ መደወል እንዲችሉ ስልክ ቁጥራቸው ሲስተም ላይ እንዲተዋወቅ የተደረገ ሲሆን በቀጣይ መሰል ተቋማትን የመለየትና የማካተት ስራ የሚከናወን ይሆናል ብለዋል አቶ መንግስቱ፡፡

በመሆኑም የ904 የጥሪ ማዕከል አገልግሎት የሚሰጠው ከላይ ለተጠቀሱ ቁልፍ ደንበኞች ብቻ ሲሆን ሌሎች ደንበኞች በነባሩ የ905 የነፃ ጥሪ ማዕከል መገልገላቸውን እንደሚቀጥሉ ጠቁመዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ማዕከሉን የማደራጀትና ሰራተኞችን የመመደብ ስራ በመጠናቀቅ ላይ ሲሆን በቅርቡ ስራ እንደሚጀምር ዳይሬክተሩ ጨምረው ገልፀዋል፡፡

የ24 ሰዓት አገልግሎት የሚሰጠው ይህ ጥሪ ማዕከል አገልግሎት የሚሰጠው በመላ ሀገሪቱ ለሚገኙ ቁልፍ ደንበኞች ነው፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ ይህንን ወቅታዊና ትኩስ መረጃዎች ወዲያውኑ እንዲደርሳችሁ ይህንን ድረ-ገፅ፡ http://www.eeu.gov.et
4.7K views08:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ