2022-03-12 19:21:29
ስንፈተ-ወሲብ(#Erectile_Dysfunction)
****
ሰላ
ም ጤና ይስጥልኝ ቤተሰቦች! እንዴት ናችሁ?
ለዛሬ ስለ ስንፈተ-ወሲብ (Impotence/Erectile Dysfunction) ወይም የወንድ ልጅ ብልት መልፈስፈስ ጠቃሚ መረጃ እንሆ:-
ስንፈተ-ወሲብ(Erectile Dysfunction)
ይህ ችግር በተደጋጋሚና ለረጅም ጊዜ የወንድ ልጅ ብልት ለፍትወተ-ስጋ ዝግጁ አለመሆን ማለት ነው። በአጭሩ ብልት በስርአቱ ቆሞ ለግንኙነት ዝግጁ መሆን ሳይችል ሲቀር ነው።
ብዙ ወንዶች ለአጭር ጊዜ በተለያየ ምክናየት ሊገጥማቸው ቢችልም በቀላሉና በራሱ ጊዜ ችግሩ ይቀረፋል።
ይሁን እንጅ አንዳንዶች ላይ ይህ ችግር ዛላቂና ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ሲሆን መፍትሔውም ውስብስብ ይሆናል።
መፍትሔውን ውስብስብ የሚያደርገው የችግሩ ተጋላጮች ስለችግሩ የሚያስቡት የተሳሳተ ግንዛቤ ነው።
ይህ ችግር ሁለት ዋና ዋና ምክናየቶች አሉት
1. አካላዊ
2. ስነ-አእምሮአዊ(በተለምዶ ስነ-ልቦናዊ) ናቸው።
አካለዊ ምክናየቶች
• እርጅና
• መጠኑ የጨመረ አልኮል ጠጭ መሆን
• የተለያዩ የረጅም ጊዜ ህመሞች እንደ ስኳር፡ ግፊት፡ ኩላሊትና ሌሎችም
• ስኳር በሽታ
• የነርቭ ችግር
• ሲጋራ ማጤስ
• የድብርት መድሀኒቶችን መጠቀም
• የእንቅልፍ መድሐኔቶችን መጠቀም
• የሆርሞን መዛባት
• ወደ ብልት የሚሄደው የደም መጠን መቀነስ
• አነቃቂ መጠጦችንና መድሀኒቶችን መውሰድ
• የደም ግፊት መድሐኒቶች
• ሽንት ትቦ ላይ የሚደረግ ቀዶ ጥገና
በስነ-አእምሮ ችግር ምክናየት
• መጨነቅ፡ መፍራት፡ ውጥረት ውስጥ መሆን፡ ድብርትና ድካም ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
• ስለችግሩ እያሰቡ ግንኙነት ለማድረግ መሞከር
• የትዳር አለመስመር
• የሴቶን ምላሽን መፍራት
• አልችልም ስሜትን እያሰቡ መሞከር
• ብዙ ጊዜ ከተቃራኒ ፆታ የሚመጣን ስሜት ችላ ብሎ መቆየት
• በግንኙነት ጊዜ የሚያስጨንቅና የሚያስፈራ ነገር ካለ
ዉድ ተከታታዮቻችን ይህ ችግር ብዙ ጊዜ ምክናየቱ ግልፅ ላይመስል ይችላል። ምክናየቱ ግን አካላዊ ወይም ስነልቦናዊ ነው።
አንዳንዶች በእንቅልፍ ሰአት ወይም ጧት ጧት ብልት ይቆምና ዝግጅ ሲሆኑ ይጠፋባችዋል።
ይህ የሚነግረን ችግሩ ስነልቦናዊ መሆኑን ነው።
ይህ ችግር ቀድሞ የዘር ፈሳሽንም ከመልቀቅ ጋር አብሮ ይከሰታል። ከጅምሩ ከቆመ ለምን ይመለሳል? ለምን ቶሎ ዘር ፈሳሽ ይለቃል? ካልን ችግሩ ስነ አእምሮአዊም ጭምር ነው።
ይህን ችግር ለመቅረፍ የጤና ባለሙያን በአካል ቀርበው ቢያማክሩ ችግሩን የመቅረፍ እድለዎ ከፍተኛ ነው።
ችግሩ በተጨማሪ ከላይ የተዘረዘሩትን ምክናየቶች ካሉ ፈፅሞ በማስወገድ፡ በአፍና በመርፊ በሚሰጡ መድሀኒቶችም ይታከማል። በውጭው አለም ብልት እንድወጠር የሚያደርግ መሳሪያ ከመኖሩም በላይ በቀዶ ጥገና የብልት ጡንቻ ውስጥ የሚቀመጡ ተጣጣፊና የሚወጠሩ ነገሮችም አሉ።
ለበለጠ ባለሙያዎች የእርስዎን ችግር በቻሉት አቅም ሊቀርፉ ዝግጁ ናቸውና ያማክሩዋቸው።
መልካም ጤንነት!
መረጃውን ሼርርርር ያድርጉ!!!
ስለሚከታተሉን ከልብ እናመሰግናለን።
#medicinedaily
@Eclink
215 views16:21