የሚጥል ህመም’ ላለበት የክብሪት ጭስ ማሸተት ይጠቅማል? የሚጥል ህመም /EPILEPSY/ የሚጥል ህመም ያለባቸው ሰዎች ያለጊዜ የመሞት እድላቸው ከጠቅላላ ሕዝብ በ 3 እጥፍ ይበልጣል ፣ ነገር ግን ለሞት መንስኤ የሚሆኑትን ነገሮች (እንደ ከከፍታ መውደቅ ፣ መስመጥ ፣ በጋለ ነገር መቃጠል ፣ የመኪና አደጋ ፣ስብራት፣ የአየር ቧንቧ መዘጋት ፣ መደፈር እና የመሳሰሉትን) መከላከል ይቻላል። እንዴት? የሚጥል ህመም /EPILEPSY/ የአንጎል ነርቭ ጊዜያዊ ኤሌክትሪካል ንዝረት እንጂ የክፉ መንፈስ ውጤት አይደለም ! ከሰው ወደ ሰው ተላላፊም አይደለም። ስለዚህ የሚጥል ህመም ያለባቸው ሰዎች እራሳቸውን ስተው ባዩ ጊዜ ችላ አይበሏቸው። መደረግ ያለባቸው የመጀመሪያ እርዳታዎች - ከጭንቅላት ስር ለስላሳ ትራስ ነገር ማድረግ - ሲንፈራገጥ ራሱን እንዳይጎዳ በዙሪያው ያሉ ሊጎዱት የሚችሉ ነገሮችን (እሳት፣ ኤሌክትሪክ፣ ስለታማ ነገሮችን) ማስወገድ - እንዳይንፈራገጥ በኃይል ለመያዝ አለመሞከር (የአጥንት ወይም የጡንቻ ጉዳት ሊያስከትል ይችላልና) - አንገት አካባቢ ያሉ የልብስ ቁልፎችን ማላላት ፤ መነፅሩን ማዉለቅ - መንቀጥቀጡ ከቆመ በኃላ እስኪነቃ ድረስ በጎኑ ማስተኛት( የአየር ቧንቧ እንዳይዘጋ ለማድረግ) - ክብሪት አለማሽተት (የሚጥል በሽታ ያለበት ሰው ወድቆ ሲንፈራገጥ የመተንፈሻ አካሉ በምራቅ አረፋና በምላስ ሊዘጋ ይችላል ፤ የክብሪት ጪስ ሲጨመርበት ይባሱን ይዘጋል ፤ ጪሱ በራሱም አንጎልን የሚጎዱ ኬሚካሎች አሉት) - ህመምተኛው እስኪነቃ ድረስ አብሮ መቆየት -ህመምተኛው ከነቃ በኋላ ማረጋጋት - መንቀጥቀጡ ከ 5 ደቂቃ በላይ የሚረዝም ከሆነ ወይንም የታማሚዉ የቆዳ ቀለም ወደ ሰማያዊነት ከተለወጠ በአስቸኳይ አምቡላንስ መጥራት ከ care epilepsy, ethiopia ፅሁፍ የተወሰደ. By Dr. Eyob Dagnew 219 views18:53