#ሱዳን የዓለም የጤና ድርጅት ለ10 ተከታታይ ቀናት በመላ ሱዳን በቀጠለው ውጊያ ከ420 የሚበልጡ ሰዎች መሞታቸውን እና 3ሺ 7 መቶ የሚሆኑ መቁሰላቸውን አዲስ ባወጣው ሪፖርቱ ይፋ አደረገ ። ****** በሱዳን የተባባሰውን ግጭት ተከትሎ በርካታ ሀገራት ዜጐቻቸውን ከሃገሪቱ ለማውጣት እየተረባረቡ መሆኑ ተሰምቷል። ብሪታንያ ፣ ፈረንሣይ፣ ጣሊያን ፣ ኔዘርላንድስ ፣ ግሪክ እና በርካታ የአውሮፓ ሀገራት በካርቱም የነበሩ ዜጐቻቸውን እያወጡ መሆኑን አሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል :: ***** የአሜሪካ ልዩ የአየር ኃይል ባካሄደው ዘመቻ በመዲናዋ ካርቱም የነበሩ 70 የኤምባሲው ዲፕሎማቶችን እና ቤተሰቦቻቸውን ከከተማዋ በተሳካ ሁኔታ ማውጣት መቻሉን የአሜሪካ ባለስልጣናት አስታውቀዋል፡፡ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እንደ ኢትዮጵያ፣ ጅቡቲና ሳዑዲ አረቢያ ያሉ አገሮች ባይተባበሩን ኖሮ ዘመቻው ስኬታማ አይሆንም ነበር ብለዋል፡፡ **** ሳዑዲ አረቢያ በበኩልዋ በካርቱም የነበሩ 157 ዜጐቿን ባካሄደችው ዘመቻ በተሳካ ሁኔታ ማውጣት መቻሏን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤትዋ በኩል አስታውቃለች ። 3.5K views17:26