Get Mystery Box with random crypto!

ዩዴሞኒያ 6- ሊዚ =========== እናቷን ያዋለዳት ሀኪም የተወለደችው ልጅ ሲያይ ደነገጠ። እን | Mental wellness የአእምሮ ጤና

ዩዴሞኒያ 6- ሊዚ
===========
እናቷን ያዋለዳት ሀኪም የተወለደችው ልጅ ሲያይ ደነገጠ። እንደዛ አይነት ልጅ አይቶ አያውቅም። እናቷ እንዳትደነግጥ ልጇን አላሳያትም። ፎቶ አንስቶ ሰጣት። እናቷ ግን ምንም አልመሰላትም። ልጇን ማቀፍ ነው የፈለገችው።

እናትና አባቷ ሊዚ የተለየች እንደሆነች እንዳይሰማት አድርገው ነው ያሳደጓት። ትምህርት ቤት ስትገባ ተማሪዎች ይጠቋቆሙባታል፣ ያንሾካሽካሉ፣ ይሸሿታል። ሆናም ሊዚ ተቋቁማ አለፈችው።

ሰባተኛ ክፍል ስትደርስ የቤት ስራ ተሰጥቷት ልትሰራ ኢንተርኔት ከፈተች። "በyou tube ትንሽ ዘና ብዬ የቤት ስራዬን እሰራለሁ።" ብላ Youtube ውስጥ ስትገባ ከ4 ሚሊየን በላይ ሰዎች ያዩት ቪዲዮ ከላይ አለ። "የአለማችን እጅግ አስቀያሚዋ ሴት"The ugliest woman in the world ይላል። ስትከፍተው የእሷ ቪዲዮ ነው። ማን እንደቀረፃትና you tube ላይ እንደጫነው አላወቀችም። ለሊቱን ሙሉ ስታለቅስ አደረች።

ቆይታ ግን "እኔ ማለት ሰዎች የሚሉኝን አይደለሁም። ግሩም ድንቅ ነኝ። የሚሰድቡኝ፣ መጥፎ ነገር የሚናገሩኝ ሰዎች ማንነቴን እንዲወስኑ አልፈቅድላቸውም። ከድክመቴ ይልቅ ጥንካሬዬ ላይ ከጎደለኝ ይልቅ የተሰጠኝ ላይ አተኩሬ እሰራለሁ።" ብላ በተለቀቀው ቪዲዮ የተሸማቀቀችው ሊዚ ቪዲዮዎች እየሰራች ራሷ መልቀቅ ጀመረች። "ሰዎች ሲያዩኝ ምን ይላሉ?" ብላ በሀፍረት ቤት ትውል የነበረችው ሊዚ ብዙ ሰው በተሰበሰበበት ንግግር ማድረግ ጀመረች።

ሊዚ ቬላስኬዝ አሁን ታሪኳን በመናገር ለሚሊዮኖችን ተስፋ፣ ጥንካሬ እና ፅናትን እያስተማረች ነው። እንደሊዚ አይነት ህመም ያለባቸው ሰዎች በጣት የሚቆጠሩ ይሁኑ እንጂ ሁሉም ሰው ድክመትና ጉድለት እንዳለው ሁሉ ዩዴሞኒያም አለው። በአካባቢው ያሉ ሰው ሰዎች ድክመቱ ላይ እንዲያተኩር ቢገፋፉትም ግለሰቡ ግን ጥንካሬና እምቅ ችሎታው ላይ የማተኮር ምርጫ አለው።

ዩዴሞኒያ ለሁላችንም!