Get Mystery Box with random crypto!

#ኮምፒውተራችሁ_እየተንቀራፈፈ_ተቸግራችኋል? ኮምፒውተራችሁን በምትከፍቱት እና በምትጠቀሙበት ሰአ | Dotcom TV Show🇪🇹🇪🇹

#ኮምፒውተራችሁ_እየተንቀራፈፈ_ተቸግራችኋል?

ኮምፒውተራችሁን በምትከፍቱት እና በምትጠቀሙበት ሰአት እየተንቀራፈፈ አማሯችዋል ?

እንግዲያውስ ፍጥነቱን ሊጨምሩ የሚችሉ ነገሮችን እናያለን ።

1. Power option
Start menu ላይ power option ብላቹ ፈልጉ ከሚመጣላቹ window ውስጥ high performance የሚለውን ምረጡ

2.Disable unwanted start up programs

ይሄ ኮምፒዩተራችንን በምንከፍትበት ጊዜ ያለ እኛ ፍቃድ ፕሮግራሞችን እየከፈተ ፍጥነቱን ከሚቀንሱ ነገሮች አንዱ ነው። ይሄን ለመከላከል

Task manager ላይ መግባት (ይሄን ለማግኘት start menu ላይ right click አድርጎ ማግኘት ይቻላል አልያም Ctrl Alt እና delete የሚለውን አንድ ላይ መጫን) ከሚመጣው window ውስጥ start up ላይ በማድረግ የማትፈልጉትን ፕሮግራሞች disable ማድረግ።

እዚህ ጋር impact የሚለው high ከሆነ disable ባታረጉ ይመረጣል።

3.Defragment and optimize drive Start menu search bar ላይ defragment ብሎ መፈለግ
Window ሲመጣላቹ የምትፈልጉትን driver መርጣቹ optimize ማድረግ

4. Delete unnecessary temporary file Start menu ላይ right click አድርጎ run የሚለውን መምረጥ አልያም window key እና R ን ከ ኪቦርዳችን ላይ አንድ ላይ መጫን
%temp% ብሎ ጽፎ enter መጫን የሚመጣላቹ folder ላይ ያሉ ፋይሎችንctrl + A ተጭነን ሁሉንም ሲመርጥልን ማጥፋት
ድጋሚ run ቦክሱን ከፍታቹ temp ብሎ መጻፍ ከሚመጣላቹ folder ውስጥ ያሉ ፋይሎችን ሁሉ ማጥፋት አሁንም ለ ሶስተኛ ጊዜ run ቦክስ ላይ prefetch ብሎ መጻፍ የሚመጣላቹ folder ውስጥ የሚገኙ ፋይሎችን ማጥፋት።

እነዚህን የምናጠፋበት ምክንያት ጊዜያዊ እና space የያዙ ፋይሎች ስለሆኑ ነው። ምንም አይነት ችግር አያመጡም።

5. Clean up Memory
This pc ውስጥ ገብታቹ የምፈልጉት local ዲስክ ላይ right click በማድረግ property መምረጥ Disk clean up የምትለውን icon click ማድረግ
የሚመጣውን የ warning box ok ማድረግ እዚህ ጋ recycle bin ውስጥ ያሉ ፋይሎች ሳይቀሩ ነው የሚጠፉት

6. Reduce run time service
Run box ከፍታቹ msconfig ብሎ መጻፍ ቀጥሎ ከሚመጣው window service የሚለውን መጫን በመቀጠል hide all microsoft service የሚለውን tick ማድረግ በመቀጠል disable የምትለዋን icon click ማድረግ

7. Registry tweaks
Run box መክፈት(window key + R) regedit ብሎ መጻፍ
Hkey -current user Control panel Mouse Mouse hover time valueን ወደ 10 መቀየር
እዛው folder ላይ desktop መምረጥ Menu show delay
Valueን ወደ 10 መቀየር

8. visual effects
Start menu ላይ System ብሎ መፈለግ Advanced system setting መምረጥ
Advance ውስጥ በመግባት setting መምረጥ Adjust for best performance መምረጥ
ቀጥሎ የምትፈልጉት ነገር ካለ ቲክ በማድረግ መምረጥ በመጨረሻም ከላይ ያሉትን ከጨረስን በኋላ ኮምፒዩተራችንን Restart ማድረግ

#share_please

የዩቲዩብ ቻነሌን ይቀላቀሉ

https://m.youtube.com/channel/UCPeUyORyXZ9tLL7okpkmETQ
https://m.youtube.com/channel/UCPeUyORyXZ9tLL7okpkmETQ