2023-03-04 16:08:06
እሁድ የካቲት 26 ከቀኑ 9 ሰአት ጀምሮ
በኮሜድያን እሸቱ አማካኝነት በዶንኪ ትዩብ በቀጥታ
#Ethiopia | መቄዶንያ ያስጀመረውን የአረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን ህንጻ ለማጠናቀቅ የ1 ሚልዮን ዶላር ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር ማዘጋጀቱን ገለጸ
መቄዶንያ የአረጋውያን እና የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል በጅምር ላይ ያለውን ህንጻ በማጠናቀቅ ወደ ስራ እንዲገባ ለማድረግ የ1 ሚልዮን ዶላር ማሰባሰቢያ መርሀ ግብር ማዘጋጀቱን የማእከሉ መስራች የክብር ዶክተር ቢንያም ለጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አሳውቀዋል።
በመግለጫው እሁድ የካቲት 26 ከቀኑ 9 ሰአት ጀምሮ በኮሜድያን እሸቱ አማካኝነት በዶንኪ ትዩብ በቀጥታ ስርጭት የገቢ ማሰባሰቢያ እንደሚደረግ ተገልጿል።
የገቢ ማሰባሰቢያው ዋና አላማ በመጠናቀቅ ላይ ያለውን ህንጻ በርና መስኮት ለመግጠም ከሚያስፈልገው 3.5 ሚልዮን ዶላር ላይ 1ሚልዮን ዶላር ለመሰብሰብና ህንጻውን በማጠናቀቅ ማዕከሉ እየሰጠ ያለውን አገልግሎት አድማሱን በማስፋት ለብዙኃን መድረስ መሆኑ ተነግሯል።
ከ2.3 ቢልዮን ብር በላይ የሚፈጀው G+12 ዘመናዊ ሆስፒታልና የአረጋውያን መኖሪያ ህንጻ በተጀመረ በ3 ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ ግንባታው 70% መጠናቀቁ ተገልጻል።
ከ7,500 በላይ አረጋውያንና የአዕምሮ ህሙማንን በውስጡ በመያዝ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው ማዕከሉ በቀጣይ 20 ሺህ ለማድረስ የታቀደ መሆኑ የተነገረ ሲሆን በቀን አንድ ሚልዮን ብር ወጪ እንዳለው በመጠቆም በዕለቱ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በመሳተፍ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ተጠይቋል።
15.3K views13:08