Get Mystery Box with random crypto!

የአልዛይመር በሽታ ምክንያቱ በሽታውን የሚያመጣው ዋናው ምክንያት በግልጽ የታወቀ አይደለም። ይ | Doctor M nursing Home care

የአልዛይመር በሽታ

ምክንያቱ

በሽታውን የሚያመጣው ዋናው ምክንያት በግልጽ የታወቀ አይደለም።

ይህ በሽታ የሚጀምርበት ጊዜ መቼ እንደሆነ እና ለምን እንደሚጀመር አሁንም አይታወቅም።

በአብዛኛው ጊዜ ይህ በሽታ ያለባቸው ሰዎች በአንጎላቸው ላይ ልዩ የሆነ ልማም [አማይሎይድ ፕላክና ታው ታንግል (amyloid plaques and tau tangles )] ተጠራቅሞ ይገኛል።

በአንጎል ላይ የሚገኘው ልማም (amyloid plaques) አዕምሮን በመጥፎ ሁኔታ ለመቀየር ይጀምራል።

ከጊዜ በኋላም ጤንነት ያላቸው የአንጎል ሴሎች (cells) ቀልጣፋነታቸውን ያጣሉ፣ ቀጥለውም እርስ በራስ ያላቸው ግንኙነት ይቀንሳል፣ እናም በመጨረሻም ይሞታሉ።

ከዚያም በሽታው ትዝታን ለማከማቸት አስፈላጊ ወደሆነው ሒፖካምፐስ (hippocampus) ወደሚባለው የአንጎል ክፍል ይደርሳል።
ተጨማሪ የአዕምሮ ክፍሎች ሲሞቱም፣ የአዕእምሮ መጠን እየቀነሰ ይሄዳል።

በሽተኞቹ ወደ ሞት ሲቀርቡም፣ የአዕሞራቸው መጠን በጣም የተቀነሰ ይሆናል።

ይህ በሽታ ያለባቸው ሰዎች የትዝታና የአስተያየት መሳት ምልክቶችን ማሳየት እስከሚጀምሩ ድረስ፣ ለብዙ አመታት የበሽታው ምልክቶች አይገኝባቸውም።

ምልክቶቹ

የአልዛይመር በሽታ አካሄድ ለሁሉም ሰው አንድ አይነት አይደለም።
ነገር ግን፣ በአብዛኛው ጊዜ በሽተኞቹ የተመሳሰሉ ምልክቶችን ያሳያሉ።
የበሽታው ምልክቶች እየተባባሱ የሚመጡበት ፍጥነት ከአንድ ሰው ሌላ የተለያዩ ናቸው።
የበሽታ ምልክቶቹ በሶስት ደረጃዎች የተካፈሉ ናቸው፥

የመጀመሪያ ደረጃ ምልክቶች

የማስታወስ ችግር፣ በልዩም በቅርብ የደረሱትን ነገሮች መርሳት

ትክክለኛ ቃላቶችን አለማስታወስ እና መጥፎ ውሳኔዎችን ማድረግ

በቀላል መምታታት እና ሀሳቦችን ለማደራጀት ችግር ላይ መዋል

መሀከለኛ ደረጃ ምልክቶች (በአብዛኛው ጊዜ የበሽታው የምርመራ ውጤት በዚህ ደረጃ ይታወቃል)

የሚሄዱበትን ወይም ከየት እንደመጡ መርሳት

የገንዘብ በመቆጣጠር ችግር

ጥያቄዎችን በተደጋጋሚ መጠየቅ

የመናገርና የመጻፍ ችሎታ መቀነስ (አንዳንዴም መጥፋት)

አስቀድሞ የነበረው ጸባይና ስሜት መለወጥ

የመጨረሻ ደረጃ ምልክቶች (በዚህ ደረጃ ቋንቋን፣ ማስተዋልን፣ ሕዋሳትን፣ እና ሆን ብሎ ማሰቢያን የሚቆጣጠረው የአንጎል ክፍሎች ተጎድተዋል)

ተጨማሪ የማስታወስ ችግር እና መምታታት

አንድስ ነገሮችን ለመማር አለመቻል

በአዲስ ነገሮች መበሳጨት

እራስን ለማልበስ መቸገር (መደረግ ካለበት ከአንድ ደረጃ በላይ ያለውን ስራ ለማከናወን ያስቸግራቸዋል)

ያለምክንያት መፍራት

የቁም ቅዥት

ያልሆነ ነገርን ማመን

የንግግር ችሎታ የተቀነሰ ይሆናል

ጡንቻዎች እና የመነቃነቅ ችሎታዎች በጣም ይቀነሳሉ፤ በሽተኛዎች የአልጋ ቁራኛ ይሆናሉ

በመጨረሻም፣ በሽተኞች እራሳቸውን መንከባከብ እና ሰገራን መቆጣጠር አይችሉም

ምርመራው

በአብዛኛው ጊዜ፣ የአልዛይመር በሽታን ለመመርመር እና የምርመራ ውጤትን በእርግጠኛነት ለማወቅ አስቸጋሪ ነው።

በዚህ ጊዜ ተቀባይነት ያለው ምርመራ ቢኖር፣ የመረዳት/የመገንዘብ ችሎታ ፈተና በመስጠት የበሽተኞችን አስተሳሰብ ለመመዘን በመሞከር ነው።

የአዕምሮ ምርመራ የሚቀጥሉትን ችሎታዎች ይመለከታል፥

የማስታወስ (ትዝታ) ችሎታ፣ የቋንቋ ችሎታ

የማስተዋል ችሎታ፣ በነገሮች ትኩረት የመስጠት ችሎታ

ነገሮችን ደረጃ በደረጃ የመገንባት ችሎታ፣ ቦታን ወይም አቅጣጫን የማወቅ ችሎታ

ለችግሮች መፍትሄ የማግኘት ችሎታ፣ ነገሮችን ለማከናወን ያለ ችሎታ

በሽተኞች ቀድሞ ከነበራቸው ጸባይ እና አስተያየት እንዴት እንደተለወጡ ለማወቅ፣ የበሽተኖችን ቤተሰብ አባላት በቃል ንግግር ለመጠየቅም ይቻላል።
በተጨማሪም፣ ከበሽተኞች ቀዳማዊ ዘመዶች መካከል እንደዚህ አይነት የአልዛይመር ምልክቶች ታይተው እንደነበሩም መጠየቅና ማጥናት ጠቃሚ የምርመራ ዘዴ ነው።

አልዛይመርን ከሌላ በሽታ ለይቶ ለማወቅ፣ ጥልቅ የሆነ የአዕምሮ ምርመራ፣ እንዲሁም የሚቻል ከሆነው የአከርካሪ ውስጥ የሚገኝን ፈሳሽ ምን ያህል ልማም [አማይሎይድና ታው ፕሮቲኖች (beta-amyloid or tau proteins)] እንደሚገኙ የሚታወቅበት ምርመራ ያስፈልገዋል።

መከላከያው

በዚህ ጊዜ, አልዛይመርን ለመከላከል ስኬታማ የሆነ ምንም መንገድ የለም።
በዚህ በሽታ ምን አይነት ለውጥ እንደሚያመጡ እርግጠኛ የሆኑ ውጤት ባይኖራቸውም፣ አንዳንድ በሀሳብ የሚቀርቡ መከላከያዎች የሚቀጥሉት ናቸው፥

የሚበላውን ጤንነትን የሚያበረታታ ምግብ አይነት መቆጣጠርና መከታተል

የልብ ጤንነትን መቆጣጠር

እንደ ማንበብ፣ ጨዋታዎችን መጫወት፣ የሙዚቃ መሳሪያዎችን መጫወት አይነት አዕሞርን የሚያሰላጥን ነገሮችን በየጊዜው ማድረግ።

@Doctormhomecare