Get Mystery Box with random crypto!

ጾመ ፍልሰታ ፍጹም ያላደፉ ~ እንከን አልባ ገጾች ከበረድ የነጹ ~ ጸአዳ ፍጥረቶች በቤትህ ሊፈሱ | አድኅነነ እግዚኦ እስመ ሃልቀ ሔር

ጾመ ፍልሰታ

ፍጹም ያላደፉ ~ እንከን አልባ ገጾች
ከበረድ የነጹ ~ ጸአዳ ፍጥረቶች
በቤትህ ሊፈሱ ~ ከመቅደሱ ደጆች
ይኸው ከዋዜማው~ ታዩ የአንተ መልኮች

አይገርም ፍልሰታ ~ ለእነሱ የተባለች
በአዋጅ ተደንግጋ ~ ተሰድራ ያለች
የሆነች ይመስል ~ ወላጅ ቀርቶ ኋላ
እነሱ ፊት ናቸው ~ ከኪዳኗ ጥላ

እንኳንም ግን መጡ ~ ይሙሉ በመቅደሱ
በልማድ ባልሆነ ~ በዕውቀት ይታደሱ

ከወዲሁ እንኳን አደረሰን ልጆቻችን ብቻ ሳይሆኑ እኛም የምንከብርበት ከነፍስ ሞት የምናመልጥበት የጾም ሳምንታት ይሁንልን

የጾም ጊዜውን የበረከት የጸሎት የስገደት ከአምላካችን ጋር የምንነጋገርበት የምንሻውን የምናገኝበት ችግራችን የምፈታበት ከኃጢአት ውጭ የልባችን መሻት የምናገኝበት ግዜ እንዲሆንልን የእረሱ መልካም ፈቃድ ይሁንልን


አግዚአብሔር አምላክ በሰላም አስጀምሮ በሰላም በደስታ ያስፈጽመን
የእሜቤታችን ፍቅሯ በረከት ረድኤቷ አይለየን