Get Mystery Box with random crypto!

☞ ከ3 ቢሊየን ብር በላይ የሚፈጅው #የቅዱስ_ያሬድ ግዙፍ ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ። . ቅዱስ ያሬድ | አድኅነነ እግዚኦ እስመ ሃልቀ ሔር

☞ ከ3 ቢሊየን ብር በላይ የሚፈጅው #የቅዱስ_ያሬድ ግዙፍ ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ።
.
ቅዱስ ያሬድ የምድሪቱ የዜማ ሊቅ የመጀመሪያው ደራሲ እና የዕውቀት ሊቅ መሆኑ ይታወቃል። ይሁን እንጂ ይህ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ሊቅ እንደስሙ እና እንዳበረከተው አስተዋፅዖ ቋሚ የሆነ ማስታወሻ የለውም፡፡ ስለሆነም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዕውቅና የተሰጠው የደብረ ሐዊ ቅዱስ ያሬድ አንድነት ገዳም ህንፃ አሰሪ ኮሚቴ የቅዱስ ያሬድን ግዙፍ ፕሮጀክት ይፋ አድርጓል።
.
ኮሚቴው ፕሮጀክቱን በማስመልከት ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ የቅዱስ ያሬድን ግዙፍ ፕሮጀክት ከ3 ቢሊየን ብር በላይ እንደሚፈጅ በውስጡም የቅዱስ ያሬድ #የጥናትና ምርምር እና #የቱሪዝም ማዕከል ለመገንባት የሚያስችል መሆኑን በመግለጫው ተነግሯል፡፡ ይህ ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ ለኢትዮጵያ ምልክት የሆነውንና ኢትዮጵያዊነትን
በጥበብ ያነጸ ሊቅ አስተምህሮን ከማስረጽ ባሻገር የኢትዮጵያን መጻዒ ዕድል ለመወሰን በሚያስችሉ ዐበይት ጉዳዮች ላይ ትውልድ ግንዛቤ የሚጨብጥበት እንደሚሆን ይታመናል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ውለታዋ ዋጋ አግኝቶ በትውልዱ የሚዘከርበትንና ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት የሚቀነቀንበትን ወርቃማ ዘመን ለመዋጀት እንደሚረዳም በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡
.
በተጨማሪም ለጥበብ ሥራዎቹ የሚመጥንና ለሌሎቹ አብያተ ክርስቲያናት ናሙና ሊሆን የሚችል ይዘትና ቅርጽ ያለው #ቤተ_ክርስቲያን በስሙ ይታነጻል፡፡ እንዲሁም የቅዱስ ያሬድ አምስቱን ጸዋትወ ዜማና ድርሰቶቹን ጨምሮ አጠቃላይ ስራዎቹን መሠረት አድርጎ የታሪክ፣ የፍልስፍና፣ የስነ ውበትና ክዋኔ ጥበብ ጥናትና ምርምር ሊካሄድበት የሚችል የልህቀት ማዕከል ይገነባል ተብሏል። የአምስቱ ጸዋትዋ ዜማ ምስክር ቤት፣ የቅዱስ ያሬድ ሥራዎች የወግ ቁሶችና ቅርሶች እንክብካቤ የሚደረግበት የሚጠበቅበትና ለጥናትና ምርምር የሚውሉ #ሙዚየም እና #ቤተመጽሐፍት እንደሚገነባም ተገልጿል፡፡
.
#ሰኔ 19 ቀን 2014 ዓ.ም #በኤሊያና ሆቴል ይፋዊ የፕሮጀክት ማስተዋወቅ እና #የገቢ_ማሰባሰቢያ መርሐግብር እንደሚያካሂድ ኮሚቴው አስታውቋል፡፡
……
https://t.me/dnhayilemikael