Get Mystery Box with random crypto!

ትምህርተ ተዋህዶ

የቴሌግራም ቻናል አርማ dnhailat — ትምህርተ ተዋህዶ
የቴሌግራም ቻናል አርማ dnhailat — ትምህርተ ተዋህዶ
የሰርጥ አድራሻ: @dnhailat
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 447
የሰርጥ መግለጫ

በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ ቤ/ክ ትምህርቶች ይተላለፉበታል።
" አንተ ግን በተማርህበትና በተረዳህበት ነገር ጸንተህ ኑር፥ ከማን እንደ ተማርኸው ታውቃለህና፤"
(2ኛጢሞ 3፥14)
ለማንኛውም ጥያቄና አስተያየት👇👇👇
👉 @DnHaile ወይም
👉 @DnHaileBot ላይ ያስቀምጡልን

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-04 20:53:49 ይህንን ያውቁ ኖሯል?
እንደምን ዋልክ ወንድሜ?!

ጥያቄ አለኝ
አሁን ሰግደት ላይ አብዛኞቻችን ስንሰግድ(በተለይ ኪርያላይሶን ላይ)ትከሻችንን እና ጭንን እንነካለን ምንን ነው የሚያመለክተው?አልያም ትርጉማቸው?
ያው ስግደት ሁለት ዓይነት ነው ተብለን የምንማረው ለዛ ነው፤

መልስ
.በመጀመሪያ እጃችን በ ምልክት ትከሻችን ላይ ማመሳቀላችን 5500 ዘመን በሲዖል በዲያብሎስ መታሰራችንን ሲያመለክት፤
በሁለተኛ ደግሞ የተመሳቀለውን እጃችንን ነጣጥለን ትከሻችንን መንካታችን በጌታችን መታሠር እኛ መፈታታችን ያመለክታል።
ጉልበታችንን መንካታችን ከዲያብሎስ ባርነት ነጻ አውጥተህ በደምህ ገዝተኸናልና በነፍስ በሥጋ ለአንተ እንገዛለን ስንል ነው።
መሬት(አፈሩን) በግንባራችን (በአፍጢማችን-በአፍና በጢም) ነክተን መነሳታችን
1. ከዚህ (ከአፈር) አንስተህ የፈጠርከን ስንል
2. በኃጢአት ብንወድቅ በንስሐ አነሳኸን ስንል
3. በሥጋ ብንሞት በትንሣኤ ዘጉባኤ ታስነሳናለህ ሞተን በስብሰን አንቀርም ስንል ነው።
ስግደት ሦስት ዐይነት ነው
1, የአምልኮት ለእግዚአብሔር ብቻ
2, የጸጋ ለቅዱሳን
3, የአክብሮት ለነገሥታት፤ ለካህናት፤ ለትልልቅ ሰዎች።

Haila Ze Dingil
ሰኔ 27/2012

ትምህርተ ተዋህዶ
በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ ቤ/ክ ትምህርቶች ይተላለፉበታል።
" አንተ ግን በተማርህበትና በተረዳህበት ነገር ጸንተህ ኑር፥ ከማን እንደ ተማርኸው ታውቃለህና፤"
(2ኛጢሞ 3፥14)
ለማንኛውም ጥያቄና አስተያየት
@DnHaile ወይም
@DnHaileBot ላይ ያስቀምጡልን
https://t.me/DnHailat
469 views▂▃▄▅▆▇█▓▒░Hailat Ze Dingil░▒▓█▇▆▅▄▃▂, edited  17:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-19 12:14:30
በትሕትናው ልዕልናን ላገኘ፣ ለፍጥረታት ባለው ርኅራኄ የአምላክ እናትን ለሚመስል፣ የተቸገሩትን ፈጥኖ መርዳት ልማዱ ላደረገው፣ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ፣ ደግ እና ሰውን ወዳጅ ለሆነው መልአክ ለቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ በዓል እንኳን በሰላም አደረሰን።

ቅዱሳን መላእክት በአንድ ኃጢአተኛ ወደ እግዚአብሔር መመለስ የሚደሰቱትን ያህል፣ ባልተመለሰው ኃጢአተኛ ደግሞ እንዲሁ ያዝናሉ። በአንዱ ኃጢአተኛ መመለስ የተሰማቸውን ደስታ ፈጣሪያቸውን በማመስገን እንደሚገልጹ፣ ባልተመለሰው ኃጥእ የተሰማቸውን ኃዘን ደግሞ አምላካቸውን "ማረው፣ ይቅር በለው" ብለው በመለመን ያሳያሉ። (ያዕ 5፥13) ቅዱስ ሚካኤል አሁን እንዴት እንደ ሆንን አይቶ ይዘንልን፣ አዝኖም ይለምንልን፣ ለምኖም ያስምረን!!!

"እነሆ ሚካኤል መልአካችሁ ምሕረትን ይለምንላችሁ"

እንኳን አደረሰን!!!

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
https://t.me/Dnabel
abelzebahiran@gmail.com
129 views▂▃▄▅▆▇█▓▒░Hailat Ze Dingil░▒▓█▇▆▅▄▃▂, 09:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 14:59:52
እግዚአብሔር አሕዛብ ያለ ሐዋርያት ስብከት በሥላሴ ማመን እንደማይችሉ፣ ሐዋርያትም ያለ መንፈስ ቅዱስ መውረድ በየአገሩ ቋንቋዎች ሁሉ መስበክ እንደማይችሉ ዐወቀ፡፡ ስለዚህም በሰናዖር ሜዳ የተበተኑትን የዓለምን ቋንቋዎች በሐዋርያት አንደበት ሰብስቦ ያኖር ዘንድ ቅዱስ መንፈሱን ላከ፡፡ የተላከውም መንፈስ ያለ አንድ ቋንቋ የማይናገረውን የሐዋርያቱን አንደበት በቅጽበት አሰለጠነው። በእውነት እንደ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ያለ አስማሪ ማን ነው?! በዚህችም እለት ሐዋርያቱ በዓለም ሁሉ ቋንቋዎች ተሞልተው ከእርሷ የወጡባት የጽዮን አዳራሽ (ጽርሐ ጽዮን) እንደ ምን ያለች ትምህናት ቤት ናት?! መንፈስ ቅዱስ ከዚያም በፊት ከዚያም በኋላ ታይታ የማትታወቅ ሐዋርያቱ በቅጽበት የዓለም ቋንቋ ተምረው የተመረቁባት ልዩ ትምህርት ቤት አደረጋት፡፡

ሐዋርያቱም በመንፈስ ቅዱስ ተሟሙቀው በሰበኩት በመጀመሪያ ዕለት ስበከት ብዙዎችን አሳምነው አጠመቁ። በዚህ የመከር በዓል አይሁድ ከአዲሱ እህል ለእግዚአብሔር ቁርባን ሲያቀርቡ፣ ሐዋርያቱ ግን የክርስቶስ አካል ለሆነችው ለሐዲሲቷ ቤተ ክርስቲያን ከእህል ቁርባን ይልቅ የሚወደዱ ምዕመናንን ስጦታ አድርገው አቀረቡ። በአይሁድ የመከር በዓል ቀን በሐዋርያቱ በተሰጠ ትምህርት የእግዚአብሔር እርሻ የሆኑ ምዕመናን በዝተው አብበው ተገኙ። እውነትም የመከር በዓል!!!

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
abelzebahiran@gmail.com
https://t.me/Dnabel
603 views▂▃▄▅▆▇█▓▒░Hailat Ze Dingil░▒▓█▇▆▅▄▃▂, 11:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 13:42:16 ለማንም እንዳትናገር!

መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ የአንድን ዲዳና ደንቆሮ አንደበት ‘ተከፈት’ ብሎ በአምላካዊ ኃይሉ ከፈተ፡፡ ይህንን ካደረገ በኋላ ግን ‘ለማንም አትንገሩ ብሎ አዘዛቸው እነርሱ ግን ባዘዛቸውም መጠን ይልቅ እጅግ አወሩት’’ (ማር 7:36)
‘አትንገር ብዬ ብነግረው አትንገር ብሎ ነገረው’ ይሏል እንግዲህ ይኼንን ነው፡፡

የመልካም ሰውነት አንዱ መለኪያ ምሥጢር ጠባቂነት ነው፡፡ እውነተኛ ባልንጀርነትም ምሥጢርን መስማት ሳይሆን የሰሙትን ጠብቆ መያዝ ነው፡፡ ይህ የሚሆንላቸው ሰዎች በማኅበረሰቡ ዘንድ ይከበራሉ በፈጣሪም ዘንድ ዋጋቸው ከፍ ያለ ነው፡፡ በምድርም ቢሆን ለከፍተኛ ሓላፊነት የሚታጩትና ከፍ ያለ ክብር የሚሰጣቸው ሰዎች በማሰቃያ ሥፍራ ሳይቀር እየተንገላቱ ምሥጢር የሚጠብቁ ሰዎች ናቸው፡፡

አንዳንድ ሰው ግን የሰማውን ምሥጢር ለሌላ ሰው ለማዝረክረክ ማሰቃያ አያስፈልገውም፡፡ አትንገር የተባለውን እስኪናገር ድረስ ሆዱን ይቆርጠዋል፡፡ እግሩን እሾህ የወጋው ሰው እስኪነቀልለት ድረስ እንደሚንገበገብ ይህ ዓይነት ዓመል የተጠናወተውም ሰው ምሥጢሩን ለሌላ ሰው እስኪያሰማ ድረስ ይንቆራጠጣል፡፡ ‘ቀሊል ሰው’ ይለዋል ጠቢቡ ሲራክ

ምሥጢር ጠባቂነት ለወታደር የሞት ሽረት ጉዳይ ነው፡፡ በኮድ ማውራት ግድ የሆነውም ለዚህ ነው፡፡ ለሐኪም የሙያ ቃል ኪዳን ነው፡፡ ለጠበቃ የጥብቅና ፈቃድን ላለማጣት የሚጠበቅ ሕግ ነው፡፡ ለካህናት የንስሓ ልጆችን የመጠበቅ ሰማያዊ ቃልኪዳን ነው፡፡ ዓለም የምትናወጸው በዚህ መርሕ ኖረው ምሥጢር በማይጠብቁ ሰዎች ነው ማለት ይቀልላል፡፡

ጌታችን ያደረገው ፈውስ ቢሆንም ማስታወቂያ ሥሩልኝ ግን አላለም:: እንዳይናገሩ አዝዛቸው:: ከዚህም የምንማረው ብዙ ነው:: የሰውን መልካም ነገርም ቢሆን ምሥጢር መጠበቅ የግድ ነው፡፡ ለዚያ ሰው ሥራ እንቅፋት ላለመሆን ሲባል ዝም ማለት እርዳታ ነው:: የሰውን ኃጢአትና ነውር መደበቅ ደግሞ "ከባቴ አበሳ" (በደልን ሸፋኝ) አስብሎ በፈጣሪ ክብር ያስገኛል::

ሙሴን ወደ ስደት የዳረገው ምሥጢር መቋጠር የማይችል እስራኤላዊ ነበር፡፡ ሙሴ ለእርሱ አግዞ ግብጻዊውን ገድሎ ቢቀብርና ነጻ ቢያወጣው ‘አመስጋኝ አማሳኝ’ /አመስጋኝ አጥፊ/ እንዲሉ ሔዶ ወሬውን ነዛው፡፡ ወሬው በአጭር ጊዜ ተዳርሶ እስከ ፈር ኦን እልፍኝ ደረሰ፡፡ በአንድ መቋጠር በማይችል ወንፊት ሰው ምክንያት ሙሴ ከቤተ መንግሥት ወጥቶ የዱር ስደተኛ ሆነ፡፡

ጌታችን በዚህች ምድር ሲመላለስ ተአምራቱን እንዳይናገሩ ያደርግ የነበረው ተአምራቱ ቢነገሩ የሚጎዱ ሆነው አልነበረም፡፡ በአንድ ወገን መከራ ከፊቱ አስቀምጦ ክብርን መፈላለግ እንደማይገባ ሲያስተምረን ሲሆን በሌላ በኩል ግን ከጊዜው በፊት መከራን ሊያደርሱበት እንዳይነሳሱና የመጣበትን ዓላማ ቅድሚያ መፈጸም እንደሚገባው ሲያስረዳ ነበር፡፡

ምሥጢር መጠበቅ በጎ ዕቅድንም ይጨምራል፡፡ ያለ ጊዜው የወጣ በጎ ዜናም ሆነ ዕቅድ በአፍ ይቀራል፡፡ ሳይሠራ ፈተና ይበዛበታል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሳይሠሩ ቀድሞ ‘እሠራለሁ’’ ብሎ ነጋሪት መጎሰም ለጠላት ማንቂያ ደወል ነው፡፡ አበው ‘የሰይጣን ጆሮ አይስማ’ የሚሉት ለሰይጣን ብቻ አይደለም፡፡ አንዳንድ ነገር ሳይሠራ ተወርቶ ይዳረሳል፡፡ ክፋቱ በጣም ያወራከው ነገር የሰራኸው የሚመስልህ ነገር ነው፡፡ ብዙ ካወራህ በኋላ ያወራኸውን ከሰራኸው ለመለየት መቸገርህ አይቀርም፡፡ ዝም ብሎ መሥራትን የመሰለ ደግሞ ምንም ነገር የለም፡፡ ችግሩ ‘አሣ ሳትይዝ አሣ እጠብሳለሁ አትበል’ እንደሚባለው ከሥራ ማኒፌስቶው መቅደም የለበትም::

አንዳንዴ ደግሞ "በምሥጢር እየሥራ" መሆኑን የሚያወራም ሰው አለ:: ጳውሎስ ኞኞ በጻፈው አሁን የማላስታውሰው ጽሑፍ ላይ በድሮ ዘመን ደረታቸው ላይ "የምሥጢር ፖሊስ" የሚል ጽሑፍ የተለጠፈባቸው ሰላዮች ነበሩ ይባላል:: ምሥጢሩም እንዳይቀር ጉራውም እንዳይቀር ነው ነገሩ:: እንዲህ ያለ ነገር ስንት ሥራ አበላሽቶአል መሰላችሁ?!

ዝም ማለት የቻለ ተቋም ወይም ግለሰብ ባይሠራ እንኳን ዝምታው ግርማ ይሆነዋል፡፡ ‘ሬሳ የሚፈራው ለምንድር ነው? ቢሉ ዝም ስለሚል’’ ይባላል፡፡ ዝም የሚል ወገን ባይሠራ እንኳን ‘ዝም ያለው ምን እየሠራ ነው?’’ ያሰኛል፡፡ መረዳት ከቻልን ውስጥ ውስጡን የልባቸውን እየሠሩ ፣ በፈለጉት ቦታ የፈለጉትን እያስቀመጡ ፣ ንብረት እያፈሩ ፣ እየተደራጁ ጸጥ የሚሉ እንዳሉ ሁሉ ላይ ላዩን ደግሞ እያወሩ ምንም የማይሠሩ ዓለምን ሞልተዋታል፡፡

ሥጋትንህንም ሁሉ መደበቅ አንድ ብልህነት ነው፡፡ አንዱን ሰውዬ ዘራፊዎች አግኝተው ቅጥቅጥ አደረጉት ይባላል፡፡ ኪሱን ሲፈትሹ ግን ያገኙት አምስት ብር ብቻ ነው፡፡ ብስጭት ብለው ‘’አንተ ለ አምስት ብር ብለህ ልትሞት ነበር እንዴ?’’ ሲሉት ‘አይ እኔማ ካልሲዬ ውስጥ የደበቅኩትን አምስት መቶ ብር ትወስዱብኛላችሁ ብዬ ፈርቼ ነው’ ብሎ አረፈው፡፡

በዚህ ዘመን አንደበትን ያለመሰብሰብ ችግር እንደዚህ ሰውዬ እየጎዳንም ነው፡፡ እንዲህ ሊያደርጉ ነው ፣ እንዲህ ሊሠሩ ነው ወዘተ በሚል ጥቆማ ተበረታትተው ብዙ ክፉ የሠሩና የሚሠሩ ዘራፊዎች አሉ፡፡ አንዳንዴም እንደ ባለ አምስት መቶ ብሩ ሰውዬ ያላሰቡትን ያሳሰብናቸው ቀማኞች አሉ፡፡ የማይተዋወቁትን ሰዎች ሳናውቅ አብረን ሰድበን አንድ ያደረግናቸው ፣ የማይታወቁትን ሰዎች በነቀፋ ጀግና ያደረግናቸው ብዙ ናቸው፡፡
የዚህ ዘመን መሻገሪያ ወርቃማ ሕግ አንደበትን መቆጠብ ፤ የቻለ ድምጽ አጥፍቶ በጎ መሥራት ፣ ያልቻለም የሚሠሩ ሥራዎችን በአንዳንድ ነጋሪቶች አለማደናቀፍ ነው፡፡

‘ኢየሱስም ያዩትን እንዳይናገሩ አዘዛቸው’’

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ ጸልዩ! ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like እና Share ያድርጉ
FB: https://www.facebook.com/officialHenokhaile/
Telegram: https://t.me/deaconhenokhaile
Instagram: https://www.instagram.com/p/CBnMF0nnhcQ/?igshid=549jvl607bv4
Youtube: https://www.youtube.com/channel/UCOaVsWC05aUjeqIEW3fWj7g
349 views▂▃▄▅▆▇█▓▒░Hailat Ze Dingil░▒▓█▇▆▅▄▃▂, 10:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-08 10:47:32 ‹እስክ ዛሬ ያላወቅነው›› ❖❖
( ሊቀ ሊቃውንት ስምዐኮነ መልአክ )
በዚህ ዓለም ካሉ ነገሮች ውስጥ በጣም የምታውቀው ማንን ነው? ተብለህ ብትጠየቅ መጀመሪያ ወደ አእምሮህ የሚመጣው መልስ ምንድን ነው? ‹‹ራሴን ነዋ!›› አትልም; ብዙ ሰው በጣም እርግጠኛ ሆኖ ከሚያውቃቸው ነገሮች ውስጥ የመጀመሪያው ራሱን እንደ ሆነ ሊያስብ ይችላል፡፡ በርግጥ ላንተ ከአንተ የተሻለ አንተን የሚቀርብ ሌላ አካል የለም፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ከራስህ ጋር ያለህ ቀረቤታ ራስህን ለማወቅህ ማስረጃ ሆኖ ሊቀርብ አይችልም፡፡ ለዓይን ከቅድብ የቀረበ ምን አለ? ነገር ግን በመስታወት ካልታገዘ በቀር ዓይናችን አንድም ቀን ቅንድቡን አይቶት አያውቅም፡፡

በተለይ የኖርንበት ማኅበረሰብ እና ያደግንበት ባሕል ‹‹ራስን ስለ ማወቅ›› ያለው ግንዛቤ ትንሽ ያልጠራ ይመስላል፡፡ ለምሳሌ አንድ ሰው እድሜው ከፍ እያለ ሲመጣ ‹‹ዐዋቂ›› ተብሎ ይጠራል፡፡ ‹‹ዐዋቂ›› የሚለው ስያሜ ተምሮ በያዘው ዲግሪ፣ ዲፕሎማ፣ ወይም ባደረገው አንዳች ማኅበራዊ አስተዋጽዎ ምክንያት የተሰጠው አይደለም፡፡ ‹‹ራሱን የሚያውቅ›› ለማለት ነው፡፡ ሌላው ጠንከር ያለ ወቀሳና ምክር የደረሰበትም ሰው ከሚዘንብበት ትችት ለማምለጥ የሚጠቀምባት አመክንዮ ‹‹እኔ ልጅ አይደለሁም፤ ራሴን ዐውቃለሁ›› የምትል ነች፡፡ ወይ ራስን ማወቅ!

ራስን ማወቅ እንዲህ እንደምናስበው በቀላሉ የሚደረስበት ነገር አይደለም፡፡ ትክክለኛው ማንነታችንን ለማየት መጀመሪያ መውጣት የሚጠበቅብን አድካሚ የሆነ የትሕትና ዳገት አለ፡፡ ከእኛ ውጭ ያለን ሌላ ቁስ ለማየት የቻልነው እርሱ በቆመበት ቦታ ላይ ስላልቆምን ነው፡፡ ራሳችንንም መመልከት ከፈለግን መጀመሪያ እኛ የሌለንበትን ተቃራኒ አቅጣጫ ፈልገን ማግኘት አለብን፡፡ ይህ ራሳችንን ቆመን የምናይበት ትክክለኛው እና እኛ የሌለንበት ተቃራኒ አቅጣጫ ደግሞ ትሕትና ነው፡፡ እርሱ ላይ ስንቆም ራሳችንን እያየን መታዘብ እንጀምራለን፡፡ ‹‹አሁን እንዲህ ማድረግ ትክክል ነው?›› እያልን ራሳችንን እንጠይቃለን፣ እንወቅሳለን፣ እናርማለን፡፡

ለሰው ራስን ማወቅ ምን ያህል እንደሚከብደው የምንረዳው በሌሎች ላይ ሲፈርድ ስናይ ነው፡፡ እንደ ግንድ ተሸክሞት ያጎበጠው ኃጢአቱን ትቶ የሌሎችን ስህተት ቀና ብሎ ሲመረምር፣ እንደ ግመል ገዝፎ በዓይኑ ፊት የቆመው የገዛ ድክመቱን ውጦ እንደ ትንኝ ያነሰውን የወንድሙን ጥፋት ሲያጠራ ማየት ‹‹ሰው ምን ያህል ራሱን ባያውቅ ነው?›› ያሰኛል፡፡ ጌታም በወንጌል ‹‹እናንተ እውሮች መሪዎች፤ ትንኝን የምታጠሩ ግመልንም የምትውጡ›› ሲል የገሰጻቸው እንዲህ ዓይነቱን ጠባይ የተላበሱ ፈሪሳውያንን ነው፡፡(ማቴ 23፡24) በመጽሐፈ መነኮሳት እንደ ተጻፈ አንድ ወጣኒ መነኩሴ ወደ አረጋዊ አባት መጥቶ ‹‹ለምንድር ነው ሁል ጊዜ በሌሎች ላይ የምፈርደው?›› ሲል ቢጠይቃቸው፣ ‹‹እስከ ዛሬ ራስህን ስላላወቅህ ነው›› ብለው መልሰውለታል፡፡ ስለዚህ ራሱን እያጸደቀ የወንድሞቹን ስህተት ነቃሽ ለሆነ ኃጢአተኛ ሰው ፍቱን መድኃኒቱ ‹ራሱን ማወቁ› ነው፡፡

ሰዎች ራሳቸውን ሳያውቁ የሚቀሩት ስላልቻሉ ብቻ አይደለም፡፡ ራስን ማወቅ ስለማይፈልጉም ጭምር ሊሆን ይችላል፡፡ ምክንያቱም ‹ራስን ማወቅ› ይዞ የሚያመጣው ጊዜያዊ ሕመም ወይም ትንሽ ስቃይ አለ፡፡ ወደ ራሳችን መመልከት ስንጀምር የማንፈልገውን ‹‹እኛነት›› በውስጣችን ልናገኘው እንችላለን፡፡ በዚህም መረበሽ፣ መቆጨት፣ ኃፍረት ይሰማን ይሆናል፡፡ ነገር ግን ከዚህ ስሜት ለማምለጥ ብለን ቅዠታዊ ዓለም ይሄድ ዘንድ ለራሳችን ልንፈቅድለት አይገባም፡፡ ለእኛ ከማንም በላይ ጠላት የሚሆንብን ይህ በውስጣችን የተደበቀውና ማወቅ የማንፈልገው ‹‹ስውር እኛነታችን›› ነው፡፡ ስለዚህም በጊዜ ራስን መርምሮ አፋጣኝ መልስ መስጠት ያስፈልጋል፡፡

ራስን ዐውቆ፣ ከራስ ጋር ተዋውቆ፣ ለንስሐ አባት ድክመትን አሳውቆ፣ የፈጣሪ ጸጋ እና ረድኤቱን እየጠየቁ በትሕትና ለመኖር ያብቃን!
255 views▂▃▄▅▆▇█▓▒░Hailat Ze Dingil░▒▓█▇▆▅▄▃▂, 07:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-04 10:55:01 + አልፋና ኦሜጋ ክርስቶስ +

መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ ‘አልፋና ኦሜጋ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ’ አለ:: A እና Ω የግሪክ የመጀመሪያና የመጨረሻ ፊደላት ናቸው፡፡ ጌታችን መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ ሲል ከዓለም መፈጠር በፊት የነበርሁ ዓለምንም አሳልፌ ለዘላለም የምኖር እኔ ነኝ ሲል ነው፡፡

ወደ ጥልቁ መለኮታዊ ዘላለማዊነት ሳንገባ ያለንባትን የምድርን ታሪክ ይዘን ብቻ እንዲሁ ካየነው ክርስቶስ መጀመሪያም መጨረሻም ነው፡፡ ‘እግዚአብሔር ‘በመጀመሪያ’ ሰማይና ምድርን ፈጠረ’ ተብሎ እንደተጻፈ እግዚአብሔር አብ ‘መጀመሪያ’ በተባለው በልጁ በክርስቶስ ሰማይንና ምድርን ፈጥሮአል፡፡ ስለዚህ ክርስቶስ የሁሉ መጀመሪያ ነው፡፡ ይህችን ምድር በግርማው መጥቶ የሚያሳልፋትም እርሱ ነው፡፡ ስለዚህ ለምድርም መጀመሪያዋና መጨረሻዋ ክርስቶስ ነው፡፡

መቼም እኛም ከምድር ተፈጥረናልና ይህ ነገር እኛንም ሳይመለከተን አይቀርም፡፡ ነቢዩ ከእናቴ ሆድ ጀምሮ አንተ አምላኬ ነህ እንዳለ በእናታችን ማሕፀን የሳለንና በኋላም ለእኛ ምጽዓት በሆነችው የሞታችን ዕለት ነፍሳችንን ወደ እርሱ የሚወስዳት መጀመሪያችንና መጨረሻችን እርሱ ክርስቶስ ነው፡፡
ይህ ግን ለሁሉ የማይቀር ነው፡፡ ወዳጄ ክርስቶስን አልፋና ኦሜጋ መጀመሪያና መጨረሻ መሆኑን ታምናለህ፡፡ በአንተ ሕይወት ውስጥ ግን ክርስቶስ እውነት መጀመሪያና መጨረሻ ነው?

ለአንዳንዶች ክርስቶስ መጀመሪያቸው ነበር፡፡ ዴማስ ለክርስቶስ አልፋ ብሎ ዘምሮለት ነበር፡፡ ከጳውሎስ ጋር ሆኖ ለፊልሞና ሰላምታ ሲልክም ነበረ፡፡ በኋላ ግን ዓይኑ በተሰሎንቄ ውበት ተማረከ፡፡ የአሁኑን ዓለም ወደደና ከሐዋርያት ጋር ማገልገሉን ተወ፡፡ ክርስቶስ ለእርሱ መጀመሪያ እንጂ መጨረሻ አልሆነም፡፡

‘ሰውን ፍጻሜውን ሳታይ አታመስግነው’ የሚለውን ቃል ዘንግተን ያመሰገንናቸው እንደ ሰማልያል አብርተው ጀምረው እንደ ሰይጣን ጨልመው የጨረሱ ብዙዎች ናቸው፡፡ ‘የዛሬን አያድርገውና እንዲህ እንዲህ ነበርሁ’ ብለው የሚተርኩ መነሻዬ ቤተ ክርስቲያን ነበረ የሚሉ መዳረሻቸው ሌላ የሆኑ በመንፈስ ጀምረው በሥጋ የጨረሱ ብዙዎች ናቸው፡፡ ክርስቶስ ግን መነሻም መድረሻም እኔ ነኝ ይላል፡፡ ክርስቶስ የማጣት ጊዜ አምላክህ የማግኘት ጊዜ ትዝታህ አይደለም፡፡ በማግኘትህ ውስጥም እግሩን አትልቀቀው፡፡ በደጅ ጥናትህ ጊዜ ጌታዬ ካልከው ስትሾምም አትርሳው፡፡

ቀንህን ስትጀምር ስሙን ጠርተህ ከጀመርህ ወደ ሥራህ ቦታም ስትሔድ ቤትህ አስቀምጠኸው አትውጣ፡፡ እርሱ አልፋና ኦሜጋ ነውና በእርሱ የጀመርከውን ቀንህን ከእርሱ ጋር ጨርሰው፡፡ ሰው በሥራ ቦታው በንግዱ ብዙ ወንጀል የሚሠራው ፈጣሪውን ሥራ ማስጀመሪያ ብቻ ሲያደርገው ነው፡፡

እግዚአብሔር መፍጠር የጀመረባትን የሳምንቱን መጀመሪያ እሑድ ዕለትን አሐዱ ብለን በቤተ ክርስቲያን ከክርስቶስ ጋር እንጀምራለን፡፡ በማግሥቱ ወደ ሥራና ማኅበራዊ ሕይወታችን ስንገባ ግን ክርስትናችን ይጠፋል፡፡ ሳምንቱን አልፋ ብለን የጀመርንበት አምላክ ኦሜጋ ሆኖ አብሮን እንዳይሰነብት እናደርገዋለን፡፡ ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ ማደሪያው እንጂ መቃብሩ አይደለችም፡፡ እርሱ በቤተ ክርስቲያን በረድኤት ቢገለጥም በሁሉ ቦታም የሞላ አምላክ ነው፡፡

ክርስቶስን የምናስበው እሑድ ብቻ ከሆነና በሌሎቹ ቀናት በምንውልበት ሥፍራ የማናስበው ከሆነ ፤ ‘’ሥራ ሌላ ክርስትና ሌላ’’ ብለን የምንገድበው ከሆነ ትንሣኤውን ሳይሰሙ እሑድ ዕለት በመቃብሩ ሽቱ ሊቀቡ እንደሔዱት ቅዱሳት ሴቶች በእኛ ልብ ውስጥ ክርስቶስ ገና አልተነሣም ማለት ነው፡፡ ‘ከቤተ ክርስቲያን ስትወጣ ክርስቶስን ከረሳኸው ክርስቶስ ለአንተ አልተነሣም ማለት ነው’ ይላል ቅዱስ አምብሮስ፡፡

ሐዋርያት ጌታ በምድር ሲመላለስ በነበረ ጊዜ ሁሉን ትተው የተከተሉት መጀመሪያቸው እርሱ ነበር፡፡ ዐርብ ዕለት ግን ከመካከላቸው ይሁዳ ክርስቶስን ክዶ ኮበለለ፡፡ እነርሱም መከራ ፈርተው ተበተኑ፡፡ ዮሐንስ ብቻ የወደደውን እስከ መጨረሻው ወድዶ ተከተለው፡፡ እርግጥ ነው የቀሩት ወንድሞቹም ከትንሣኤው ወዲያ በንስሓ ተመልሰው መጀመሪያቸውን ክርስቶስ መጨረሻቸው አደረጉት፡፡

ክርስቶስን ከማንም በላይ መጀመሪያዋም መጨረሻዋም ያደረገችው አልፋና ኦሜጋ የተጻፈባት ድንግል ማርያም ነበረች፡፡ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን ለዓለም ሊሠጥ ሲፈቅድ ዓለምን ወክላ የተቀበለችው ድንግል አልፋ ክርስቶስ በማሕፀንዋ ተጽፎባት በቤተልሔም ግርግም በእቅፍዋ ነበረ፡፡ ከመስቀሉ ሥርም ቆማ ቃሉን ትሰማ ነበር፡፡ ያለ ምጥ የወለደችው ድንግል አርብ ዕለት በልጅዋ ሥቃይ ተሰቃይታ ስታምጥ ምጥ ካለ ልጅ መኖሩ አይቀርምና ‘እነሆ ልጅሽ’ ብሎ ዮሐንስን ሠጣት፡፡ በእርስዋ ሕይወት ክርስቶስ አልፋና ኦሜጋ ነበረ፡፡

ወዳጆች ሆይ ዛሬ የእግዚአብሔር ልጆች ነን ፤ ነገ ምን እንደምንሆን ገና አልተገለጠም፡፡ አልክድህም ብለን እንዳንዝት ሦስቴ እንዳንክደው እንፈራለን፡፡ መጀመሪያችን የሆነው አምላክ መጨረሻችን እንዲሆን ግን ‘እስከ መጨረሻይቱ ሕቅታ ድረስ አንድነት ሦስትነትህን በማመን አጽናን’ እያልን ከቤተ ክርስቲያን ጋር እንጸልያለን፡፡

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጥቅምት 14 2013 ዓ.ም.
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ዘንድ ጸልዩ! ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like እና Share ያድርጉ
FB: https://www.facebook.com/officialHenokhaile/
Telegram: https://t.me/deaconhenokhaile
Instagram: https://www.instagram.com/p/CBnMF0nnhcQ/?igshid=549jvl607bv4
Youtube: https://www.youtube.com/channel/UCOaVsWC05aUjeqIEW3fWj7g
411 views▂▃▄▅▆▇█▓▒░Hailat Ze Dingil░▒▓█▇▆▅▄▃▂, 07:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 09:33:38 + ዘኬዎስ አጭር ባይሆን +

ዘኬዎስ በማጠሩ ምክንያት በኢያሪኮ እያለፈ ያለውን ክርስቶስን ለማየት ተቸገረ:: ሕዝቡ ብዙ ነውና የቆሙት ሁሉ ጌታን ከማየት ከለሉት:: የሾላ ዛፍ ላይ ወጥቶ ጌታን ለማየት ሲሞክር ጌታ አሻቅቦ አየው::

እሱ ዛፍ ላይ ጌታን ሊያይ እንጂ ሊታይ አልወጣም:: ጌታ ሊታዩ ከሚሞክሩ ይልቅ ሊያዩት የሚሹትን ይወዳልና ዘኬዎስን ጠራው::

ከምድር ቆመን ዓይናችንን አንጋጥጠን ማረን የምንለው ጌታ ዘኬዎስን ከምድር ሆኖ ወደ ላይ እያየ ና ልማርህ አለው:: "ዛሬ በቤትህ እውል ዘንድ ይገባኛል" አለው:: ጌታ ወደ ቤቱ ገባ:: ለዘኬዎስ ቤት መዳን ሆነለት::

ዘኬዎስ አጭር ባይሆን ኖሮ ከሰዎች ጋር እየተጋፋ ጌታን ያይ ይሆናል እንጂ በጌታው ዓይን ለመታየት የሚያበቃ ትጋት አያሳይም ነበር:: ምናልባትም ሰዎችን ገለል በሉ እያለ በኩራት ሲጋፋ ከአንዱ ጋር ሲጣላ ሊቆይ ይችል ነበር::

ዘኬዎስ አጭር ባይሆን ከዛፍ ላይ አይወጣም ነበር::
ዘኬዎስ አጭር ባይሆን የሠራዊት አምላክ ወደ ቤቱ አይገባም ነበር:: በኪሩቤል ላይ የሚቀመጠው ንጉሥ በቤቱ ወንበሮች ላይ የተቀመጠው ዘኬዎስ በማጠሩ ምክንያት ነው:: የዘኬዎስ ነፍስ የዳነው በቁመቱ ማጠር ነበር:: እግዚአብሔር የመዳኑን ቀን የቆረጠለት ቁመቱን ሲያሳንሰው ነበር:: በምድር በመጽሐፍ ቅዱስ በሰማይ በሕይወት መዝገብ ስሙ የተጻፈው ዘኬዎስ አጭር በመሆኑ ነው::

ስለ ቁመት የማወራ እንዳይመስልህ:: እግዚአብሔር ለነፍሳችን መዳን የሚያሳጥርብን ብዙ ነገር አለ::
እንደ ዘኬዎስ ቁመትህ አጭር ባይሆን የሚያጥርህ ነገር ግን አይጠፋም::

ይሄ ጎደለኝ የምትለው ከሰዎች አነስኩበት የምትለው ነገር አንዳች ነገር የለም? እሱን ማለቴ ነው::
ይሄ ይጎድለኛል ከሰው አንሳለሁ እያልክ አትማረር::
እጥረትህ መክበሪያህ ነው:: ጉድለትህም መዳኛህ ነው::

እግዚአብሔር ያጎደለብህ የመሰለህ ነገር ወደ ዛፍ እንድትወጣ ምክንያትህ ይሁን:: በጉድለትህ እንደ ዘኬዎስ ከፍ በልበት:: ያኔ ሰዎች አንተን አንጋጠው ከማየት ውጪ አማራጭ አይኖራቸውም::
ፈጣሪ በፍቅሩ ይይህ እንጂ ሰዎች ወዳንተ ያዘነብላሉ:: በቤትህ መዳን ይሆንልሃል:: ከዚያም ስላጠረህ ስለጎደለህ ነገር ፈጣሪህን ስታመሰግነው ትኖራለህ::

እመነኝ አንዳንድ ጉድለቶች እድሎች ናቸው::
ዘኬዎስ አጭር ባይሆን ይሄኔ በሾላው ዛፍ ጥርሱን እየፋቀ ይቀር ነበር::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ግንቦት 23 2014
አዲስ አበባ

ፎቶ :- ኢያሪኮ "የዘኬዎስ ዛፍ" የነበረበት ሥፍራ

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን አጥብቃችሁ ስለ እኔ ጸልዩልኝ!
በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ዋጋን በምድር የሚያስቀር ውዳሴም ሆነ ሌላ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)

ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like, Subscribe እና Share ያድርጉ :-

የፌስቡክ ገጽ :- https://www.facebook.com/officialHenokhaile/
የቴሌግራም ቻናል : https://t.me/deaconhenokhaile
የዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/channel/UCOaVsWC05aUjeqIEW3fWj7g
178 views▂▃▄▅▆▇█▓▒░Hailat Ze Dingil░▒▓█▇▆▅▄▃▂, 06:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-29 10:15:22 “ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ እንዲህ አለ:-

በቅድስና ውበት ስለተሞላችው ንጽሕት ትሕት እናገር ዘንድ አንደበቴ ብቁ አይደለም፡፡ ... የተራ ቀለማት
መዋሐድ ለማይመጥኗት ለዚህች እጅግ ክብርት እንዴት ያለ ሥዕልን ልሣል? ውበትዋ ከእኔ መጠበብ በላይ ነው ፤ አእምሮዬም እንዲሥላት አልፈቅድለትም፡፡

የድንግል ማርያምን ክብርዋን ከመግለጥ ፀሐይን ከነብርሃንዋና ከነሙቀትዋ መሣል ይቀልላል፡፡ ምናልባት የፀሐይ ጨረር በሥዕል ሊቀመጥ ይችል ይሆናል፡፡ ስለ እርስዋ የሚነገረውን ነገር ግን አሟልቶ ለመስበክ አይቻልም፡፡

እርስዋን ከነማን ጋር መመደብ ይቻላል? ከደናግል ጋር? ከቅዱሳን ጋር? ከንጹሐን ጋር? ካገቡ ሴቶች ጋር? ከእናቶች ጋር? ከአገልጋዮች ጋር? እነሆ የድንግልናን ማኅተም ከወተት ጋር የያዘ ሰውነትዋን እዩ! መውለድዋንም ከታተመ ማኅፀንዋ ጋር እዩ! ከደናግል መካከል ናት ስል ሕፃን ይዛ ስታጠባ አያታለሁ! ከዮሴፍ ጋር ትኖራለች ስል በጋብቻ ቃልኪዳን እንዳልታሠረች አያለሁ!

ስለ እርስዋ እንድናገር ፍቅር ያስገድደኛል ፤
የክብርዋ ከፍታ ግን ያስቸግረኛል፡፡ ከቶ ምን ባደርግ
ይሻለኛል? ስለ እርስዋ ለመናገር ብቁ እንዳልሆንሁ
በግልፅ እናገራለሁ፡፡ ከፍቅር የተነሣ ግን ተመልሼ
መናገር ያምረኛል፡፡...

ሱራፌል ከእሳቱ የሚሸሸጉለትን የእርሱን ከንፈሮች በቡሩካን ከነፈሮችዋ የሳመች እርስዋ የተባረከች ናት! ዓለማት ሕይወትን የጠጡበትን ምንጭ እርሱን ያጠባች እርስዋ የተባረከች ነች’

(የብርሃን እናት ገፅ 352)
508 views▂▃▄▅▆▇█▓▒░Hailat Ze Dingil░▒▓█▇▆▅▄▃▂, 07:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-30 07:16:38 በሚያዝያ 27/ 2014 ዓ.ም. ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ በደብረ ምጥማቅ ሰአሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም ወቅድስት ክርስቶስ ሠምራ ቤተ ክርስቲያን ፈጽሞ አይቀርም።
“ንትቀበላ ንዑ ለወለተ ዳዊት ዘይሁዳ መጽአት ነዋ ሕቡረ ምስለ ወልዳ ናንፈርዕጽ ቅድመ ሥዕላ እንዘ ንሁብ ጋዳ”
(የይሁዳ ነገድ የዳዊት ብላቴና እንቀበላት ዘንድ ኑ። እነሆ ከልጇ ጋር በአንድ ላይ መጣች፤ እጅ መንሻ እየሰጠን በሥዕሏ ፊት እናሸብሽብ) (መልክአ ሥዕል)

በጉባኤው ላይ፡-
ዐይንን ያበራችው ደምን ሲፈሳት ተሥላ የምትታየው ገባሪተ ተአምራት ወመንክራት የእመቤታችን ሥዕል ትመጣለች፡፡ እጅግ ደማቅ አቀባበል ይደረግላታል፡፡
"ሰላም ለሥዕልኪ ቦ ጊዜ ዘትትናገር ወቦ ጊዜ ዘትክዑ ደመ ተአምር" (የምትናገርበት ጊዜ አለ፤ አንዳንዴ የተአምርን ደምን የምታፈስ ለኾነች ለሥዕልሽ ሰላምታ ይገባል) (መልክአ ሥዕል)

በፓርት ሳይድ ከእመቤታችን ሥዕል ላይ የሚፈሰው የተቀደሰ ቅብዕ ለመጡት ይሰጣል፡፡
"ሰላም ለሥዕልኪ ሐፈ ማሕየዌ በጼዴንያ ወግብጽ ዘአውሐዘት በኢሕሳዌ" (ያለማበል በእውነት ፈዋሽ ወዝን በጼዴንያና በግብጽ ላፈሰሰች ሥዕልሽ ሰላምታ ይገባል) (መልክአ ሥዕል)

በእመቤታችን አማላጅነት ከሕመማቸው የተፈወሱ ምስክርነታቸውን ይሰጣሉ፡፡
"አመ ተቀብዑ ማርያም እምሐፈ ሥዕልኪ ቅብዐ ናርዱ። በሕማም እኩይ እለ ደወዩ ወውሕዱ። ጽዑራነ ዓለም ጥዕዩ ወጥቀ ፈድፈዱ" (ማርያም እንደ ናርዱ ቅብዕ ከኾነ ከሥዕልሽ ወዝ በተቀቡ ጊዜ በክፉ ሕመም ታመው የተቸገሩ በዓለም የተጨነቁ ዳኑ በእጅጉ በዙ) (መልክአ ሥዕል)

ክብረ ቅድስት ድንግል ማርያምን አስመልክቶ በመጋቤ ሐዲስ ዶ/ር ሮዳስ ታደሰ ትምህርት ይሰጣል፡፡
"ኦ ርኅርኅተ ኅሊና ፍቅርኪ ያነድድ አማዑተ ከዊኖ እሳተ" (ኅሊናሽ የሚራራ እመቤታችን ሆይ ፍቅርሽ እሳትን ኾኖ አንጀትን ያቃጥላል) (መልክአ ሥዕል)

ብፁዓን አባቶች ይገኙበታል፡፡
"ተአምርኪ ብዙኅ ዘአልቦ ፍጻሜ፤ በርኅበ ዓለም ሰፈነ አምሳለ ደመና ወጊሜ" (ብዙና ፍጻሜ የሌለው ተአምርሽ እንደ ደመናና ጉም በዓለም ዳርቻዎች መላ) (መልክአ ሥዕል)

የእመቤታችን በረከትን በስፋት በሚገኝበት በዚኽ ጉባኤ የእመቤታችን ወዳጆቿ ኹሉ በሰአሊተ ምሕረት እመቤታችን ቤተ ክርስቲያን ይሰበሰባሉ፡፡
"ኦ ርኅርኅተ ሕሊና ዘሕገ ልማዳ ምሕረት ለኩሉ ፍጥረት፤ ንሳለማ ንዑ ለሥዕለ ማርያም ቡርክት" (ለፍጥረት ኹሉ የሕጓ ልማድ መራራት የኾነች ሕሊናዋ የምትራራ የቡርክት ማርያምን ሥዕል እንሳለማት ዘንድ ኑ) (መልክአ ሥዕል)

ሚያዝያ 27 ከቀኑ 9 ሰዓት ጀምሮ በጉርድ ሾላ አካባቢ በምትገኘው በደብረ ምጥማቅ ሰአሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም ወክርስቶስ ሠምራ
207 views▂▃▄▅▆▇█▓▒░Hailat Ze Dingil░▒▓█▇▆▅▄▃▂, 04:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-23 16:17:46 በሕማማተ መስቀል መጽሐፍ ላይ ፲፫ቱ ሕማማተ መስቀል የሚባሉት
፩ ተአስሮ ድኅሪት (የፊጥኝ መታሰር)
፪ ተስሕቦ በሐብል (በሠንሠለት መጎተት)
፫ ተጸፍዖ መልታሕት (በጥፊ መመታት)
፬ አክሊለ ሦክ (ከብረት የተሠራ የጋለ የእሾኽ አክሊል መድፋት)
፭ ተኮርዖተ ርእስ (ራስን በዘንግ መመታት)
፮ ተቀስፎ ዘባን (ጀርባን መገረፍ)
፯ ተገፍዖ ማዕከለ ዓምድ (ከምሰሶ ጋር መጋጨት)
፰ ጸዊረ መስቀል (መስቀል መሸከም)
፱ ወዲቀ ውስተ ምድር (መስቀል ተሸክሞ መውደቅ)
፲ ተከይዶ በእግረ አይሁድ (በአይሁድ እግር መረገጥ)
፲፩ ተቀንዎ ቅንዋት (በችንካር መቸንከር)
፲፪ ተሰቅሎ በዕጽ (በመስቀል መሰቀል)
፲፫ ሰሪበ ሐሞት (መራራ ሐሞትን መጠጣት)
ክርስቶስ አምላክነ ዘሐመ ወሞተ በእንቲአነ ወበሕማማቲሁ ቤዘወነ ንሰብሖ ወናልዕል ስሞ ኅቡረ እስመ ውእቱ ገብረ መድኃኒተ በብዝኃ ኂሩቱ።
(ስለኛ የታመመ የሞተ በሕማማቱም የተቤዠን አምላካችን ክርስቶስን በኅብረት እናመስግነው ስሙንም ከፍ ከፍ እናድርግ እርሱ በቸርነቱ ብዛት መድኃኒትን አድርጓልና።)
ትምህርተ ተዋህዶ
በዚህ ቻናል የኢ/ኦ/ተ ቤ/ክ ትምህርቶች ይተላለፉበታል።
" አንተ ግን በተማርህበትና በተረዳህበት ነገር ጸንተህ ኑር፥ ከማን እንደ ተማርኸው ታውቃለህና፤"
(2ኛጢሞ 3፥14)
ለማንኛውም ጥያቄና አስተያየት
@DnHaile ወይም
@DnHaileBot ላይ ያስቀምጡልን
https://t.me/DnHailat
602 views▂▃▄▅▆▇█▓▒░Hailat Ze Dingil░▒▓█▇▆▅▄▃▂, edited  13:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ