Get Mystery Box with random crypto!

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ 'ሀ' የ2013 ውድድር በዛሬው እለት ተጠናቀቀ *********** | Dessie City Football Club

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ምድብ "ሀ" የ2013 ውድድር በዛሬው እለት ተጠናቀቀ
***********************************
የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የ2013 ምድብ "ሀ" ውድድር ዛሬ ሚያዚያ 17 ቀን 2013 ዓ.ም በሐዋሳ ከተማ በተደረጉ ጨዋታዎች ተጠናቋል።

በ2013 ዓ.ም የውድድር መርሃ ግብር በሐዋሳ ከተማ በ9 ክለቦች (በመከላከያ፣ በሰሜን ሸዋ ደብረብርሃን ፣ በገላን ከተማ ፣ በለገጣፎ ለገዳዲ ፣ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ፣በወሎ ኮምቦልቻ፣ በፌዴራል ፖሊስ ፣ በደሴ ከተማ እና በወልዲያ ከተማ ) መካከል በተደረጉ ጨዋታዎች ሲስተናገድ የቆየው የምድብ "ሀ" የከፍተኛ ሊግ ውድድር ዛሬ ሚያዚያ 17 ቀን 2013 ዓ.ም ተጠናቋል። የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል እና የከፍተኛ ሊግ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ አሊሚራህ መሐመድ ፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ባሕሩ ጥላሁን ፣ የመከላከያ ሚኒስቴር የኮንስትራክሽን ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ እና የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ፍሰሐ ወ/ሰንበት ፣ ሜጀር ጀነራል መሐመድ ተሰማ የመከላከያ ኢንዶክትርኔሽን ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተርና የስፖርት ክለቡ የቦርድ አመራር፣የኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን የትምህርትና ስልጠና ውድድር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ አበባ አማረ ፣ የሲዳማ ክልል እግር ኳስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አንበሳው አበበ ፣ እንዲሁም ከፍተኛ የስፖርት ባለሙያዎች እና ኃላፊዎች በሐዋሳ ከተማ ሰውስራሽ ሳር በተነጠፈበት ስታዲየም በመገኘት ውድድሩን በመከታተል ለተሸላሚዎች የኮቪድ ፕሮቶኮል በጠበቀ መልኩ የሽልማት ስነስርዓት ተካሂዷል።

የማጠቃለያ ውድድሩን መከላከያ እግር ኳስ ክለብ ሻምፒዮን በመሆን የዋንጫ እና የወርቅ መዳሊያ ተሸላሚ ሲሆን ኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ 2ኛ እና ገላን ከተማ 3ኛ በመሆን የብርና የንሀስ ሜዳሊያ ተሸላሚ በመሆን ውድድሩን አጠናቀዋል።

የእለቱን ጨዋታ የመሩ አመራሮች ኮሚሽነር መለሰ ባህሩ ፌደራል ዋና ዳኛ ሚካኣል ጣዕመ
1ኛ ረዳት ፌደራል ዳኛ አብይ አበበ
2ኛ ረዳት ፌደራል ዳኛ ዮሴፍ ማስረሻ
4ኛ ዳኛ ፌደራል ዳኛ ኤፍሬም ደበሌ የወርቅ መዳሊያ ተሸላሚ ሆነዋል።

በእለቱ በተደረገው የመዝጊያ ጨዋታ የመከላከያ ግብ ጠባቂ ጃፏር ደሊል እና የለገጣፎ ለገዳዲ ግብ ጠባቂ በሽር ደሊል ወንድማቾች መሆናቸው የጨዋታው ልዩ ክስተት ሲሆን ውድድሩ በድምቀት ተጠናቋል።

@dessiecityfootballclub