Get Mystery Box with random crypto!

ፈለገ ጥበባት +++: የብላክ ፖንተረሷ ዋካንዳ ማን ናት? - ይህ የስልጣኔ ከተማ ለምን እና እንዴ | ደሸት777.... (፯፯፯)

ፈለገ ጥበባት +++:
የብላክ ፖንተረሷ ዋካንዳ ማን ናት?
- ይህ የስልጣኔ ከተማ ለምን እና እንዴት የትስ  ይገነባል እዉነታዉ  በምን ተረጋገጠ? ማስረጃወስ
- ብዙ የተነገረላት ምናባዊቷ ዋካንዳ አስፈሪው የኢትዮጵያ መነሳት ጋር የሚያገናኘው ነገር
- የህይወትን ዛፍ ፍለጋ የሚደረግ ትንቅንቅ



ዋካንዳ በምስራቅ አፍሪካ ውስጥ ያለ ምናባዊ አገር ነው።[2]  ከሰሃራ በታች ባሉ አፍሪካ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን የልዕለ ኃይሉ ብላክ ፓንተር መኖሪያ ነው። 


ይህም አለምን በአንድ ድምፅ ያነቃነቀዉ  የሆሊዉዱ ፊልም ሪኮርድ ከያዙት ጥቂት ፊልሞች አንዱ የሆነዉ ዘ ብላክ ፓንተረስ ከፍተኛ የሆነ የ ኮፒ ራይት ስተት አለበት ምክኒያቱም ይህ ፉልም የታሪክ ምንጭ አንድምታዉን በመሸፈን የዛች ሉአላዊት ሀገር ማግኘት የሚገባትን  ዋጋ እንዲሰጣት አላደረገምና፡፡

ደግሞስ ይህ አለምን ያነቃነቀ ፊልም የታሪክ ባለቤቷ ኢትዮጵያ ናት ብለዉ ለመቀበል ይቅርና ማስብ አይፈለጉም፡፡
እዉነታዉ ግን ይህ ነዉ በምናባዊ ፊልማቸዉ ለመደበቅ የፈለጓት ዋካንዳ ኢትዮጵያ ናት ፡፡
ይህ ፊል ሲጀምር እንዲህ ይላል  አባቱን ታሪክ እንዲነግረዉ ልጁ ይጠይቀዋል፤አባቱም ታሪክ ለልጁ መናገሩን ይቀጥላል ፤"በዛች ዋካንዳ በምትባል ሀገር ቫይብሬንየም የተባለ ዉድ ማእድን እንዳለና ለቴክኖሎጂ እድገት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለዉ ይህንንም ትልቅ ሀይል ያለዉ ማእድን ከዉጭ ሀገራት ስረቆት ለመጠበቅ መሬት ስር ተቀብሮ እንደሚገኝ" ለልጁ ታሪክን ይነግረዋል  ልጁም ይቀጥላል "ይህ ዛሬም ድረስ መሬት ስር እንደተቀበረ ነዉ?" ብሎ አባቱን ይጠይቃል አባቱም መልሰ አዉን ይሆናል፡፡
ይህንን የተመለከተ አንድ እንግሊዛዊ ተመራማሪ እንዲህ ይላል " the postion between Ethiopia and south sudan it should be pointed out that wakanda was concealed using a cloacking device (እፀ መሰዉር). Wakanda is very isolated and works to remani that way,almost completely untoched by outside influences". በማለት ከፊልሙ ጋ ያለዉን ምረምራዊ ግኝት ያስታረቀዋል ዋካንዳም ኢትዮጵያ እንደሆነች ያስረዳል፡፡
  በደቡብ ሱዳን እና በኢትየጵያ አካባቢ አሉ ሰለሚባሉት  መሬት ዉስጥ ስለተሰዉሩት ሚስጥራዊ ቅዱሳን መካናት በሌላ ጊዜ በሰፊዉ እንመለከታለን፡፡
ለመሆኑ ለሰወች ግለፅ እንዳይሆኑ ተደረገዉ በፊልሙ ላይ ብዙ ቦታ ላይ የዋካንዳ ሀሳብ መነሻ ኢትዮጵያ መሆኑን  አሳይተዋል፡፡
ማስረጃወችን ከዚህ እንደሚከተለዉ አቀረብላችኀለሁ፡፡
በፊልሙ ላይ የሚታየው የሰዉየዉ body modification የሙርሲ ባህላዊ ሰዉነት የማስዋቢያ ዘዴ ይታያል፡፡

2)ላይ የሀመሮችን ባህላዊ መዋቢያ ከንፈራቸዉ ላይ ሸክላ የማስገባት ባህልን በአንድ ገፀ ባህሪ ላይ ይታያል፡፡
3) 22ኛዉ ደቂቃ 1በሌላኛዉ
ገፀ ባህሪ ላይ ስናስተዉ ወገቡ ላየ የታተቀዉ ሁሉም አይነት ኢትዮጵያን  ዉስጥ የሚገኙ መስቀሎች ይታያሉ
4) ከዚህ ቀደም በዚህዉ የቴሌግራም ገፅ ላይ እንደገለፀኩት የኢትዮጵያዉያን ብዙ ቅረሶች the british liibrarys Ethiopic Gezz

book ላይ በብሪታንያ እንደተወሰዱ እና እንዳሉ መግለፄ ይታወሳል፡፡ በዚህዉ ፊልም ላይም 35ኛዉ ደቂቃ 59 ሰከንደ ጀምሮ ስታዮት የዛችን ዋካንዳ የተባለች ሀገር  የጥንት ቅረሷን ለማስመለስ የብሪታኒያን ሙዜም ሰብረዉ በመግባት ሲወስዱት ይታያል፡፡
5) 1 ሰአት ከ11 ደቂቃ የላይ የሚታየዉ የቦታ አቀማመጥ የጭስ አባይ አካባቢን የቦታ አቀማመጥ ጋ ተመሳሳይ ነዉ
6) 1 ሰአት ከ 42 ደቂቃ ላይ ባህላዊዉ የሆነዉ የኢትየጵያ የሙዚቃ መሳሪያ የዋሽንት ድምፀ ይሰማል
7)በመጨረሻም 2 ኛዉ ሰአት ከ 06 ደቂቃ ላየ የሚታይ ነገረ አለ እሱም ከአሜሪካ ሰንደቃላማ በሰተቀኝ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማን ተሰቅሎ ይታያል፡፡


ኢትዮጵያ የትውልድ አገር የጥቁር ፓንተር ዋካንዳ ነች ይባላል  ። ከደማቅ ሀይቆች እስከ ጠበኛ እሳተ ገሞራዎች፣ የኢትዮጵያ ልዩ የሆነ ማንነት፣ ታሪክ እና አስደናቂ የተፈጥሮ ድንቆች በምድር ላይ ካሉት እጅግ ማራኪ ስፍራዎች አንዷ ያደርጋታል።
ኢትዮጵያ ከበረሃ፣ ደጋ እና እሳተ ገሞራዎች፣ የዱር እንስሳት ዝርያ ያላቸው የዱር እንስሳት፣ አስደናቂ የስነ-ህንፃ እና ሌሎችም መልክዓ ምድሮች መኖሪያ ነች።

በ Black Panther ውስጥ ከዋካንዳ ብሄረሰብ ጋር የሚጣጣም ቦታ እና ህዝብ ያላት አፍሪካዊ ሀገር ብትኖር ኖሮ ኢትዮጵያ ግልፅ ምርጫ ትሆን ነበር።


እንደሚታወቀው በሆሊውድ የፊልም ኢንድስትሪ  ውስጥ  ያለ ምክንያት የሚሰሩ  የፊልም ይዘትች የሉም። 
ሁሉም በእቅድና በስርአት በበርካታ ተመራማሪወች የታጀበ የእወቀትና የምርምር  ክምችት  ረብጣ ዶላሮች ተበጀቶ የሚሰሩ ዘመን ተሻጋሪ ሚስጥራዊ ሃሳቦችን የሚያስተላልፉበት እጂግ ግዙፍ ተቋም ነው።
በተለይ ታሪክ ነክ ዘወግ ያላቸው  የሆሊወድ ፊልሞች  በጥንት አፈ ታሪኮች በምድራችን ላይ የተከውኑ ሁነቶች ትንቢታዊ ንግርቶች የጥንታ ብራናዊ ክታቦች የአርኪይሎጂ መረጃወችን መሰረት ያደረጉ ናቸው።

ብዙሀኑ እንደሚስማሙት ዋካንዳ በሚል  ርእስ የተሰጠው እጂግ አስደናቂው ፊልም ከፊልም በዘለለ  በአለም ላይ ገናና ስለምትሆን እጂግ አስደናቂ  የጥቁር አገር በሚስጥራዊ መልእክቱ እንዳስተላለፈ ይታመናል።  ብዙሃኑ እንደሚሉት ዋካንድ ከዚህ ቀደም ሃያል የነበረች  በትንቢታዊ ንግርት  ለዘመናት የምትጠበቅ እጂግ አስደናቂ  የጥቁሮች ከተማ የብላክ ፓንተር ዋካንዳ ነች።  ታዲያ ምናባዊቷ አገር ማን ናት ሲሉ ብዙሃኑ ይከራከራሉ? 
አስደናቂዋ ምናባዊት አገር ዋካንዳ ኢትዮጵያ መሆኗን   5 ምክንያቶች የሚከተሉት ናቸው።

1. ሚስጥራዊ ህዝብ


በታሪኳ በተለያዩ ጊዜያት ኢትዮጵያ ከውጪው ዓለም መገለሏን መርጣለች።
በእውነቱ፣ ኢትዮጵያ በጣም ሚስጥራዊ ስለነበረች ኢትዮጵያን በብልጽግና፣ እንግዳ ፍጥረታት እና ድንቅ ነገሮች የተሞላች ኃያል የክርስቲያን ሀገር እንደሆነች በግልጽ የሚያውቁትን የመጀመሪያዎቹን አውሮፓውያን ግራ እንድትጋቡ ነበር።

ፕረስተር ዮሐንስ የኢትዮጵያ ገዥ የሦስቱ ሰብአ ሰገል ዘር እና የሰፊ መንግሥት ገዥ ሁሉ ኃያል ገዥ ነው ብለው ይጠሩ ነበር።

የኢትዮጵያ ህዝብ ሚስጥሩን ወደ ልቡ የመጠበቅ እና ስውር የማታለል ዘዴዎችን በመጠቀም ትኩረትን ለመቀየር የተጋለጠ ነው።

በምሳሌነትም በመላ ሀገሪቱ በየቤተክርስቲያኑ የሚገኙት በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ “ታቦቶች” የዋናው የቃል ኪዳኑ ታቦት (10 ትዕዛዛት) ትክክለኛ ቅጂ ነው ተብሏል።

እንደዚህ ያሉ ጠቃሚ ምስጢሮችን የመጠበቅ ችሎታ ካለን ፣ ቀደም ሲል በሀገሪቱ ውስጥ ሜትሮ ወይም ቫይቨራኒም  ቢወድቅ ፣ ነዋሪዎቹ ይህንን ይገልጡ ነበር? በማለት ታሪክ ከዋቂወች  ይጠይቃሉ ... የዋካንዳውያን የሃይል ምንጭ ምናልባት ቪብራኒየም ወደ ኢትዮጵያ አምርቷል ከዚህም ምድርም እንደሚገኝ ይነገራል።

2. መሬት


የኢትዮጵያ የመሬት አቀማመጥ በጣም የተለያየ በመሆኑ በአለም ላይ ያሉ እያንዳንዱን ስነ-ምህዳሮች ጥቃቅን ውክልና አላት።

ከበረዶው ከተሸፈነው የራስ ዳሸን ተራሮች ጀምሮ እስከ ዳሎል ምድር ላይ ካሉት ሞቃታማ ቦታዎች እስከ አለም ረጅሙ ወንዝ እስከ ብሉ አባይ ድረስ የረቀቀ ህዝብ ምን የተሻለ ቦታ ይመርጣል?