Get Mystery Box with random crypto!

እረኛዬዬዬ ከ100 በጎቹ መሀል 1 ብትጠፋበት ዘጠና ዘጠኙን ትቶ የጠፋችውን ፍለጋ ወጣ እረኛው | ደሸት777.... (፯፯፯)

እረኛዬዬዬ

ከ100 በጎቹ መሀል 1 ብትጠፋበት ዘጠና ዘጠኙን ትቶ የጠፋችውን ፍለጋ ወጣ

እረኛው በጉ ሲጠፋበት አይወድም

እረኛዬ እናናዬ ስለ አንድዋ በግሽ መታረድ ፣ ገደል መግባት ግድ አለሽ የበጎችሽ ጉዳት ልብሽን ቢነካው ለምን አይሆንም በጌን መጠሪያዬን አትንኩብኝ አልሽ

ስለበጎችሽ ዝቅ ብለሽ ፣  ስለ ወንድሞችሽ ፣ ስለ ቤተሰብ መንደሩ ብለሽ እራስሽን ሰዋሽ በፍቅር አንቀልባ ከፍ ብለሽ በልባቸው ታዘልሽ

ቢንቁሽ አንቺ ግን ከእረኛም አልፈሽ የመስዋት በግ ሁነሽ ከሰው በላይ ከፍ አልሽ እረኛዋ የኢትዮጵያ ልጅ ኢትዮጱያ ተባልሽ

እስኪ ልጠይቅሽ እረኛዬ መስዋእትነት እንዴት ነው ናናዬ? 

ደሞ እኮ ፣ አስተዋይ ስብእናሽ ፣ ለሌላው አሳቢነትሽ ፣  ታዛዥነትሽ ፣ የምታቂውን ለማሳወቅ አለመቆጠብሽ ፣ .. ባለሽ እውቀት ሙያ መንደርሽን ወገንሽን ልታገለግይ ልባዊ ፍቃድሽ ስስ ከሆነች በፎጣ የምትሸፈን ፈገግታሽ ጋር በትህትትና ስትገለፅ  ..

እማዬን ሀገሬን ስትጠብቂያት አሳየሽኝ አንቺ ደግ እረኛ ቤቴ ድረስ መተሽ ተጠየቅ አንተ ሰው አልሽኝ ..

ሀገርህ ሀገር ሁና ከፍ እንድትል አንተ በሰፈርህ በመንደርህ በሰዎች አይን  ብትታይ እንዴት ነህ አልሽኝ?  እረኛዬ? እኔ ለሀገሬ ምን አደረኩላት ብለህ እራስክን ጠይቅ አልሽኝ? 

ልጆች በፍቅር እንዲቦርቁባት ፣ እውነት እና እውቀት እንዲዘልቅላት እንዲበረታባት ፣ በስብእና በምግባር እውነት ሁነህ ፣  ሰው መሆን እንዲቀድምባት ደግ ደጉ እንዲበዛላት .. ከስሜታዊነት ይልቅ አንተ ምን የፍቅር ዋጋ ከፈልክላት ? ተጠየቅ አለችኝ ያቺ ምስኪን እረኛዬ እናናዬ

እናናዬ እረኛዬ ደገመችው ሰላም እድገት ብርታት እንዲያድግ በፍቅር ፣ በደግነት ፣ በምግባር ፣ .. ሁሉ ውብ ነገር ሀገርህን የሚመጥን ለልጆችዋ  የሚበጅን ልታረግ ዋጋ ልትከፍል መስዋት ልትሆን እንደ እናናዬ ቃል ትገባለህ ?

እስኪ ተጠየቅ
እንጠየቅ
ልጠየቅ  

እናናዬ  ለእናትሽ እንደሆንሽ፣  በእረኝነትሽ በጎችሽን በፍቅር እንደጠበቅሽ ለቤተሰቡ ለመንደሩ ለሀገሬው ፍቅር ስትይ እራስሽን ሰዋሽ አንቺ ደግ እረኛ ነብስሽ ትለምልም