Get Mystery Box with random crypto!

'ብዙ ዋጋ የከፈልኩበት ስራዬ፣ የተሰደብኩበት ስራዬ፣ ራሴን ዝቅ አድርጌ የሰራሁት ስራዬን እንደ ቀ | Deepdriod

"ብዙ ዋጋ የከፈልኩበት ስራዬ፣ የተሰደብኩበት ስራዬ፣ ራሴን ዝቅ አድርጌ የሰራሁት ስራዬን እንደ ቀላል ጠፋ ተባልኩ።"

በህይወታችሁ ለእናንተ ወሳኝ የሆነን ነገር እንደ ተራ እቃ ጠፋ ወይም የለም ብትባሉ ምን ይሰማችኋል? ብዙ ዋጋ የከፈልኩበት ስራዬ የተሰደብኩበት ስራዬ ራሴን ዝቅ አድርጌ የሰራሁት ስራዬን እንደ ቀላል ጠፋ ተባልኩ። ለዛውም የራሴ የምለው ሰው ነው እንደዛ ያለኝ። ከመኪናው ውስጥ እንደተወሰደበት ነው በሰው ደውሎ የነገረኝ።

አምና ከሀዋሳ ጀምሮ የፕሪምየር ሊጉ ፎቶ የዘንድሮ የባህር ዳርን ጨምሮ የሰራሁት ፋይል።

ሁለት ሰርጎች ቪድዮ ኤዲት ተደርገው ከ2000 ፎቶ ጋር

ከአንድ ድርጅት ጋር ተፈራርሜ ኢትዮጵያ ቡናን ፎቶ ሹትና ቪድዮ የሰራሁት ሙሉ ፋይል

የሚስቴ ቤቢ ሻወር ፎቶ ፋይል

የልጄ ከተወለደችበት ቀን ጀምሮ እስከ ስምንት ወሯ ያነሳናት ፎቶ ፋይል

የኳሱን ፎቶ ሳነሳ ከህመሜ ጋር እየታገልኩ ፀሐይ አቧራ ዝናብ እየደበደበኝ በተለይ ባህር ዳር ከአምስት የሚበልጡ ጨዋታዎች ዝናብ እላዬ ላይ ነበር ያለቀው ፎቶ ሳነሳ

እነዚህን ሁሉ የያዘ ላፕቶፕና ሀርድ ዲስክ ከአስር ከሚበልጡ ፋይል ከያዙ ሚሞሪዎች ጋር እንደ ቀላል ነገር ጠፋ አለኝ።

ወዳጆቼ ይሄን ስሰማ ሁሉም ነገር ነው የጨለመብኝ የማደርገው ጠፋኝ ያለማቋረጥ አለቀስኩ በቃ ተሳስቼም የጅል ስራ ልሰራ ነበር የልጄ አምላክ አትርፎኛል።

እባካችሁ በርካታ የእግር ኳስ ፎቶዎችን ላፕቶፕ እና የያዘ ሃርድ ዲስኮች ከፍላሽ ጋር እጃችሁ ላይ የደረሰ ሰዎች እባካችሁ እባካችሁ ከፍዬ ወስዳለሁ ስጡኝ ከሃዘን ስሜት አውጡኝ የልፋቴ ውጤት ባዶ እንዳይሆን እርዱኝ።

0912415689
አገኘሁ ተፈራ (Aku sport image)

እባካችሁ ሼር አድርጉለት ድንገት አንዱ ጋር ሊደርስ ይችላል! ሼር