Get Mystery Box with random crypto!

ደብረ ሰላም በዓለ እግዚአብሔር ቤተ-ክርስቲያን - ባሕር ዳር

የቴሌግራም ቻናል አርማ debreselambealeegziabhier — ደብረ ሰላም በዓለ እግዚአብሔር ቤተ-ክርስቲያን - ባሕር ዳር
የቴሌግራም ቻናል አርማ debreselambealeegziabhier — ደብረ ሰላም በዓለ እግዚአብሔር ቤተ-ክርስቲያን - ባሕር ዳር
የሰርጥ አድራሻ: @debreselambealeegziabhier
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.05K
የሰርጥ መግለጫ

✝️ በሰ/ት/ቤቱ የተከፈተ ገጽ ሲሆን ፤ በደብሩ የሚከናወኑ መረጃዎችን እና ማስተዋወቂያዎችን በውስጡ ያገኛሉ።
👉 Facebook fb.me/debreselambealeegziabhier
👉 YouTube
youtube.com/c/debreselambealeegziabhier
የመወያያ ግሩፕ ➩ @DebreSelam
💡ለጥያቄ እና አስተያየት 👇
▹ @BealeEgziContact

Ratings & Reviews

3.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-20 22:26:40
ደብረ ታቦር 
(ቡሔ) 
‹‹ታቦር እና አርሞንየም በስምህ ደስ
ይላቸወዋል››መዝ 89፤12
የደ/ሰ/በዓለ እግዚአብሔር ቤተ
ክርስቲያን ሰ/ት/ቤት እንኳን ለደብረታቦር
በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ በዓሉን
ትውፊት ለማሳዎቅ እና ተጠብቆ እንዲኖር
ለማድረግ ይሔንን ፅሁፍ
አዘጋጅቷል፡፡
የደብረታቦር በዓል የሚከበርበት
ምክንያት ጌታችን በድሓኒታችን እየሱስ
ክርስቶስ በታቦር ተራራ ላይ ብርሃነ
መለኮቱን መግለፁን በማሰ፣ልከት ነው፡፡
የዚህ በዓል መሠረት የክርስቲያን እምነት ሲሆን፣ ደብረ ታቦር በግዕዝ የታቦር ተራራ ማለት ነው፡፡ የታቦር ተራራ የሚገኘው አሁን ፍልስጥኤም ተብሎ በሚጠራው ሀገር ነው፡፡ ደብረ ታቦር ወይንም የታቦር ተራራ ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስት ደቀመዛሙርቱን ይዞ ወደ ተራራው የወጣበትና ፊቱ እንደፀሐይ የበራበት ልብሱም እንደብርሃን ነጭ የሆነበት ቦታ ነው፡፡ ይህ ቦታ ጌታ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት ተራራ ነው።

የማቴዎስ ወንገል ምዕራፍ ፲፯፦ ቁጥር ፩ እስከ ፭ " ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው። በፊታቸውም ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ። እነሆም፥ ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው። ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ አለ። እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፥ እነሆም፥ ከደመናው። በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ።" በእለቱን አድምቀውት ከሚውሉት ትውፊቶች መሓል ጅራፍ፣ችቦ፣ሙልሙል ዳቦ ዋነኞቹ ናቸው፡፡
325 views19:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 11:49:37 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን


መንፈሳዊ ጉባኤ

እንሆ የደ/ሰ/በዓለ እግዚአብሔር ሰ/ት/ቤት የፊታችን እሑድ ነሐሴ 15/2014 በአይነቱ ልዩ የሆነ "የህይወት ልምድ ልውውጥ" መርሐግብር አዘጋጅቶ ይጠብቅዎታል።
በእለቱም፦ ወጣትነታቸውን በአገልግሎት ያሳለፉ፤ አሁንም በአገልግሎት ላይ ያሉ፤ በአለማዊውም ስኬታማ የሆኑ ደክተር እህት ወንድሞቻችን ተጋብዘዋል።

እርስዎም በዕለቱ በመገኘት የመርሐ ግብራችን ተካፋይ ይሆኑ ዘንድ በልዑል እግዚአብሔር ስም ጠርተንዎታል፡፡

➤ ቀን ፡ ነገ እሑድ ነሐሴ 15/2014
➤ ሰዓት፡ ከቀኑ 8:00
➤ ቦታ ፡ በደ/ሰ/በዓለ እግዚአብሔር ሰ/ት/ቤት አዳራሽ

አዘጋጅ ፡ የደ/ሰ/በዓለ እግዚአብሔር ሰ/ት/ቤት

በሰ/ት/ቤቱ የተከፈቱ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ተቀላቅለው ይከታተሉ ፤ ለሌሎች ኦርቶዶክሳውያንም ይላኩ...

Instagram + Facebook + Telegram
YouTube - www.youtube.com/c/DebreSelamBealeEgziabhier
315 viewsedited  08:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 21:26:51 ስንክሳር ዘወርኀ ነሐሴ ፲፫(13)

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ ዐሥራ ሦስት በዚች ቀን ክብር ይግባውና የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታላቅና ክቡር በዓል ነው።

በዚች ቀን መድኃኒታችን ሦስቱን ደቀ መዛሙርቶቹን ጴጥሮስ፣ ያዕቆብንና ዮሐንስን ይዞ ወደ ታቦር ተራራ ላይ አወጣቸው። መልኩም በፊታቸው ተለወጠ ልብሱም እንደ በረዶ ነጭ ሆነ። ስለ እነርሱም ጌታችን "የሰው ልጅ በጌትነቱ ሲመጣ እስከሚያዩት ድረስ በዚህ ከቆሙት መካከል ሞትን የማይቀምሱት አሉ" አለ።

ሰዎች ሁሉ እርሱ ለሙሴ ጌታውና ከሞት ያስነሣው እንደሆነ ለኤልያስም ፈጣሪው እንደሆነና ካሳረገበትም ያወረደው እርሱ እንደሆነ ያውቁ ዘንድ እነሆ ከጌታ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋራ እየተነጋገሩ ሙሴና ኤልያስ ወደርሱ መጡ።

ስለዚህም ጴጥሮስ ጌታችንን እንዲህ አለው "አቤቱ በዚህ ትኖር ዘንድ ትወዳለህን ሦስት ሰቀላዎችንም አንድ ለአንተ፣ አንድ ለሙሴ፣ አንድ ለኤልያስ እንሠራ ዘንድ"።

በዚህም ቃል የደካማነትና የትሕትና ምልክት አለበት።
ደካማነት የተባለ ጴጥሮስ ጌታችን ከሰማይ የወረደበትን ሥራ ትቶ በተራራ ላይ ይኖር ዘንድና እራሱን የሚሰውርበት ቤት ይሠራለት ዘንድ የተጋገረው ነገር ነው።
ትሕትና ያልነውም ጴጥሮስ ለራሱና ለባልንጀሮቹ ሐዋርያት ቤት ይሠራ ዘንድ ስለ አላሰበ ነው። እራሱንና ባልንጀሮቹን ሐዋርያት እንደ ባሮች ነቢያትን ደግሞ እንደ ጌቶች አድርጎ አስቧልና።

ስለ ሐዋርያትም የእውቀት ማነስ አታድንቅ በዚያ ጊዜ ፍፁማን አልሆኑምና።
እንዲህም በሚልበት ጊዜ ጌታችን በሰው እጅ የተሠራ ማደሪያን የማይሻ መሆኑን ለጴጥሮስ ያሳየው ዘንድ አነሆ ደመና ጋረዳቸው።

የጌታችንን ጌትነቱን የሚገልጽ በሐዋርያትም ልቡና እምነትን የሚያጸና እንዲህ የሚል ቃል ከደመና ውስጥ መጣ። "ይህ የምወደው በእርሱ ደስ የሚለኝ ልጄ ይህ ነው እርሱንም ስሙት"።

ሙሴና ኤልያስም ከእነርሱ ጋር ሲነጋገሩ ተሰሙ ስለ ርሱ መምጣት የተናገሩትን ትንቢታቸውንም በቸርነቱ አረጋገጠ። ወደ ተራራ ላይ በመውጣቱም ነቢያትና ሐዋርያት ደስ አላቸው።
ሁለተኛም የአብን ቃል በሰሙ ጊዜ ከእነርሱ ሥውር የነበረ የወልድ ዋሕድን በእውነት ሰው መሆን በዚያ ጊዜ ተረዱ ያን ጊዜ የጌትነቱ ክብር ተገልጦአልና። ሐዋርያትም ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው የሆነ እርሱ ሙሴን ከመቃብር ያስነሳው ኤልያስንም ያሳረገው አውርዶም ያወጣው እርሱ እንደሆነ አወቁ። ከእርሱ በቀር ማንም ማን የሙሴን መቃብር የሚያውቅ የለምና ከዐሳረገው ከእርሱ በቀር ማንም ማን ኤልያስ ያለበትን የሚያውቅ የለምና። በሰማይና በምድር ስልጣን ካለው ከሁሉ ጌታ በቀር ሙታንን አድኖ ሊአስነሣቸው ማንም አይችልም።

ደብረ ታቦርም የቤተ ክርስቲያን አምሳል ሆነች ከብሉይ እና ከሐዲስ በውስጧ ሰብስባለችና።
የአብንም ቃል በሰሙ ጊዜ በግንባራቸው ፍግም ብለው በምድር ላይ ወደቁ እንደሙታን ሆኑ ከዓለም አስቀድሞ ከእርሱ ጋራ በህልውና እንዳለ ለልጁ አብ ምስክርን ሆነ ወዲያውኑ ሙሴ ወደ መቃብሩ ኤልያስ ወደ ቦታው ተመለሱ።

ሐዋርያትን በአነቃቸው ጊዜ ከብቻው ጌታችን በቀር ማንንም አላገኙም። ከባሕርያችን የደዋሐደና ሥጋችንን የለበሰ ፍጹም አምላክ እንደሆነ በዚህ ሐዋርያት አስተማሩ።

እንግዲህ እናስተውል ሰው ካልሆነ ቅዱስ ገብርኤል እመቤታችንን ድንግል ማርያም በአበሠራት ጊዜ "እግዚአብሔር ከአንቺ ጋራ ነው" እንዴት አላት።
አምላክ ካልሆነስ "ለመግሥቱ ፍጻሜ የለውም" እንዴት አላት።
ሰው ካልሆነ በበረት እንዴት አስተኙት። አምላክስ ካልሆነ መላእክት ከሰማይ ወርደው "ለእግዚአብሔር በሰማያት ምስጋና በምድርም ሰላም ለሰውም ግዕዛኑ ሊሰጠው" እያሉ እንዴት አመሰገኑ።

ሰው ካልሆነ ዮሐንስ በውሃ እንዴት አጠመቀው አምላክስ ካልሆ አልዓዛር ከመቃብር እንዴት ሊያስነሳው ቻለ።
ይህ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው አንድ ልጅ አካላዊ ቃል እግዚአብሔር እርሱ ያለ መለወጥ ያለመለየት አንድ አካል አንድ ባሕሪ በመሆን ፍጹም አምላክ ፍጹም ሰው እንደሆነ እናምንበታለን። እርሱም ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ሁልጊዜ አንድ ህላዌ ነው ዛሬ ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።

++++++++++++++++++++
ነሐሴ ፲፫(13) ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩. ደብረ ታቦር/ደበረ ምሥጢር/ ደብረ በረከት
፪. ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት(ልደቱ)
፫. ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ
፬. ቅዱሳን አበው ሐዋርያት
፭. አባ ጋልዮን መስተጋድል
፮. አቡነ ዓቢየ እግዚእ ጻድቅ(ልደታቸው)
፯. ቅደስት ኦፍራ ሰማዕት

ወርኀዊ በዓላት
፩. እግዚአብሔር አብ
፪. ቅዱስ ሩፋኤል ሊቀ መላእክት
፫. 99ኙ ነገደ መላእክት
፬. ቅዱስ አስከናፍር
፭. 13ቱ ግኁሳን አባቶች
፮. ቅዱስ አርሳንዮስ ጠቢብ ገዳማዊ
፯. አቡነ ዘርዐ ቡሩክ

++++++++++++++++++++
ታቦርና አርሞንዔም በስምህ ደስ ይላቸዋል። ክንድህ ከኃይልህ ጋር ነው፤ እጅህ በረታች፣ ቀኝህም ከፍ ከፍ አለች። (መዝ.88፥12)

++++++++++++++++++++
ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያዕቆብን ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው።
በፊታቸውም ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ።
እነሆም፥ ሙሴና ኤልያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው።
ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን፦
"ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ፣ አንዱንም ለሙሴ፣ አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ" አለ።
እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፥ እነሆም፥ ከደመናው፦ "በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት" የሚል ድምፅ መጣ።
ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው በፊታቸው ወደቁ እጅግም ፈርተው ነበር። ኢየሱስም ቀርቦ ዳሰሳቸውና። ተነሡ አትፍሩም አላቸው።
(ማቴ.17፥1 - 7)

በሰ/ት/ቤቱ የተከፈቱ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾቻችን ተቀላቅለው ይከታተሉ ፤ ለሌሎች ኦርቶዶክሳውያንም ይላኩ...

Instagram + Facebook + Telegram
YouTube - www.youtube.com/c/DebreSelamBealeEgziabhier
364 views18:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ