Get Mystery Box with random crypto!

የ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ካሌንደር መከናወን ያለባቸው ዋና ዋና ተግባራት:- 1ኛ=ነሀሴ 23 | Debreselam Catholic School 9_1#

የ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ካሌንደር መከናወን ያለባቸው ዋና ዋና ተግባራት:-
1ኛ=ነሀሴ 23/2014 ዓ.ም መምህራን ትምህርት ቤቶቻቸው በመገኘት የቅደመ ዝግጅት ስራ መስራት አለባቸው
2ኛ=ከነሀሴ 23-ጳጉሜ 4/2014 ዓ.ም የተማሪ ምዝገባ ይካሄዳል (ከዚህ ቀደም የተማሪ ምዝገባ በየጊዜው ይራዘም የነበር ሲሆን በዚህ ዓመት ግን
ከተጠቀሱት ቀናቶች ውጪ ትምህርት ቢሮው ምዝገባ እንዳይከናወን ወስኗል።)
3ኛ=መስከረም 2/2015 ዓ.ም የአዲሱ ስርዐተ ትምህርት የማስተዋወቅ ስልጠና ኦረንቴሽን ይሰጣል
4ኛ= ከ03-6/2015 ዓ.ም ድረስ ለአንደኛ ደረጃ(ከ1-8ኛ ክፍል) መምህራን የአዲሱ ትምህርት ስርዐተ ትምህርት የማስተዋወቅ ስራ ይከናወናል ።ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መደበኛ ትምህርት የሚያስተምሩ ይሆናል።
5ኛ=መስከረም 9/2015 ዓ.ም በክፍል ውስጥ የደበኛ
ትምህርት(Day One Class One) የሚጀምርበት ሲሆን የሬዲዮ እና የቴሌቪዥን ስርጭት በዚሁ ዕለት የሚጀምርበት ይሆናል።
6ኛ= በትምህርትና ስልጠና ዩኒቨርሲቲ የሚቆዩ መምህራን የባከነ ክፍለ ጊዜ ከአለ? የሚያካክሱ ይሆናል
7ኛ=የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና እና የ8ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና የሚሰጡ ይሆናል።