Get Mystery Box with random crypto!

የኮ/ቻ ደብረ ሲና ቅ/ሚ ቤ/ን ሰ/ት ቤት

የቴሌግራም ቻናል አርማ debrecina — የኮ/ቻ ደብረ ሲና ቅ/ሚ ቤ/ን ሰ/ት ቤት
የቴሌግራም ቻናል አርማ debrecina — የኮ/ቻ ደብረ ሲና ቅ/ሚ ቤ/ን ሰ/ት ቤት
የሰርጥ አድራሻ: @debrecina
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 421
የሰርጥ መግለጫ

ከሲና ተራራ ጫማውን አውልቆ በፅናት የመጣ መንግስቱን ወራሽ ነው የሚደርሰው ዕጣ።

Ratings & Reviews

3.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

2

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-07-19 09:31:55
68 views06:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 20:39:33 #ከመ_ትባርከነ

ከመ ትባርከነ በመስቀልከ /ዘወርቅ/(፪)
ተዋነይ በጽድቅ(፬)ሚካኤል ሐመልማል ወርቅ
#ትርጉም:-
የወርቅ ሐመልማል ሚካኤል ሆይ በወርቅ መስቀልህ ትባርከን ዘንድ በእውነት በመካከላችን ተገኝ

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@debrecina
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
161 views17:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 20:39:33 #ዓይኑ_ዘርግብ

ዓይኑ ዘርግብ ልብሱ ዘመብረቅ
ሚካኤል ሐመልማለ ወርቅ(፪)
#ትርጉም
ሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ዓይኑ የርግብ ልብሶቹም የመብረቅ ነው።

╭══•|❀:✧๑♡๑✧❀|: ══╮
@debrecina
╰══•ೋ•✧๑♡๑✧• ══╯
154 views17:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 20:39:32 #ናና_ሚካኤል_ናና

ናና ሚካኤል ናና /2/
አዝኛለሁ እና በአንተ ልጽናና
ናና ሚካኤል ናና

የረዳህ አፎምያን ሚካኤል ናና
ሰይጣን ሲፈትናት ሚካኤል ናና
አንተነህ ያዳንከው ሚካኤል ናና
ባሕራንን ከሞት ሚካኤል ናና
ለእነርሱ እንደመጣህ ሚካኤል ናና
እኔንም ተራዳኝ ሚካኤል ናና
ሚካኤል ደግፈህ ሚካኤል ናና
ለመንግሥቱ አብቃኝ ሚካኤል ናና
ናና ሚካኤል ናና /2/
አዝኛለሁ እና በአንተ ልጽናና

አዝ-------------

ናና ገብርኤል ናና /2/
አዝኛለሁ እና በአንተ ልጽናና
ናና ገብርኤል ናና

ዘመኑ ሲፈፀም ገብርኤል ናና
አምላክ መምጫው ሲደርስ ገብርኤል ናና
ገብርኤል አንተ ነህ ገብርኤል ናና
ያልካት ደስ ይበልሽ ገብርኤል ናና
ድምጽህን አሰማኝ ገብርኤል ናና
ነፍሴ ጽድቅን ትልበስ ገብርኤል ናና
አዝኛለሁ እና በአንተ ልጽናና
ናና ገብርኤል ናና

አዝ-------------

ናና ዑራኤል ናና /2/
አዝኛለሁ እና በአንተ ልጽናና
ናና ዑራኤል ናና

ቆመህ ጽዋ ይዘህ ዑራኤል ናና
ለእዝራ ሱቱኤል ዑራኤል ናና
ጥበብ አጠጥተህ ዑራኤል ናና
ዕውቀት ስታድል ዑራኤል ናና
ተገለጠ ክብርህ ዑራኤል ናና
መልአኩ ዑራኤል ዑራኤል ናና
ድኜ በፀበልህ ዑራኤል ናና
በአውደ ምህረትህ ላይ ዑራኤል ናና
እኔም ዘመርኩልህ ዑራኤል ናና
አዝኛለሁ እና በአንተ ልጽናና
ናና ዑራኤል ናና

@debrecina
@debrecina
@debrecina
138 views17:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 20:39:32 ​​ አማላጅ ነው

በፍጡራንና ፈጣሪ መካከል
ድርሻ የተሰጠው ሰውን ለማገልገል
ተራዳኢው መልአክ ጠባቂ የእስራኤል
የመላእክት አለቃ ስሙ ነው ሚካኤል

አማላጅ ነው ሚካኤል(፪)
የአምላክ ባለሟል
ለነሙሴ ለህዝበ እስራኤል

ፈርዖን እንደገና ልቡ ተጸጽቶ
ሲከታተላቸው ጦሩን አስከትቶ
ይመራቸው ጀመር ሚካኤል በፋና
ሌሊቱን በብርሃን ቀኑን በደመና
አዝ = = = = = =
ሙሴ እንደታዘዘው አነሳ በትሩን
እጆቹን ዘረጋ ገሠፀው ባህሩን
እንደ ግንብ ቆመ ባህረ ኤርትራ
በደረቅ አለፉ እስራኤል በተራ
አዝ = = = = = =
በአፎሚያ ላይ ሲፎክር ጠላት
ፈጥነህ የደረስከው ሊቀ መላእክት
እኛንም ጠብቀን ከክፉ መቅሰፍት
ፈጥነህ ድረስልን ሁነን እረዳት
አዝ = = = = = =
መልአኩ ሚካኤል አማላጃችን
እንለምንሃለን እንድትጠብቀን
አምላክ በፍርድ ቀን ጻድቃንን ሲጠራ
ዋስ ጠባቂ ሁነን ሚካኤል አደራ

መልካም በአል
"ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን
ተዋጉ ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር
ተዋጋ አልቻላቸውምም"
ራእ፲፪፥፯

@debrecina ይቀላቀሉን
93 views17:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 20:39:32 ​​✞ ይበራል በክንፉ ✞

ይበራል በክንፉ ምልጃውም ፈጣን ነው
የአምላክ ስም አለበት ስሙ ሚካኤል ነው
ያሳደገኝ መልአክ ዛሬም ከኔ ጋር ነው (2)

ከፊቴ ቀደመ ደመናን ዘርግቶ
እንዳልደናቀፍ ጉድባዎቼን ሞልቶ
ዛሬ ላለሁበት ብሩቱ ጉልበት ሆነኝ
ሰው ለመባል በቃሁ ሚካኤል ደገፈኝ

አዝ__________

በእናቴ እቅፍ ገብቼ መቅደሱ
አለሁ እስከዛሬ አጥሮኝ በመንፈሱ
የህይወቴን ሰልፎች አለፍኩ ከርሱ ጋራ
ተፅፏል በልቤ የሚካኤል ስራ

አዝ__________

በዙሪያዬ ተክሎ የእሳት ምሰሶውን
ፅድቅ እየመገበ ኣሳደገኝ ልጁን
የአምላኬን ምስጋና ዘውትር እያስጠናኝ
እርሱ ነው ሚካኤል በመዝሙር የሞላኝ

አዝ__________

ፊት ለፊት ተተክሎ ከታናሿ መንደር
ይስማኝ ነበረ ቅኔው ሲደረደር
ይወስደኛል ደጁ እየቀሰቀሰ
ታላቁት በረከት በውስጤ አፈሰሰ

አዝ__________

ሴኬምን እንዳላይ ክንፎቹን ጋረደ
መራኝ ወደ ህይወት መዳኔን ወደደ
የሞአብን ቋንቋ ከአፌ ላይ አጥፍቶ
በፀጋው ቃል ቃኘኝ በበረከት ሞልቶ

ሊቀ-መዘምራን
ዲያቆን ቴድሮስ ዮሴፍ
79 views17:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 20:39:31 #_ቅዱስ_ሚካኤል

ቅዱስ ሚካኤል/3/
ነብሴ ሲጨነቅ ሲዝል ስጋዬ
ፈጥነህ ተራዳኝ ዋስ ጠበቃዬ

አንተ ስለሆንክ ሚካኤል
የአምላክ ባለሟል ሚካኤል
ልመናቅ ፈጥኖ ሚካኤል
ካምላክ ይቀርባል ሚካኤል
የዋህ መልአክ ነህ አዛኝ ለሰው
ምልጃህ ፈጣን ነው ለምናምነው /2/

አዝ.......

ደዌ የጸናበት ሚካኤል
ባንተ ይድናል ሚካኤል
በአደባባይህ ሚካኤል
ምስክር ሆኗል ሚካኤል
ከቤትህ መጥቶ የተማፀነ
በቃል ኪዳንህ ህይወቱ ዳነ /2/

አዝ......

ካምላክ ተሰጥቶህ ሚካኤል
ክብርህ ያበራል ሚካኤል
ለጎስቋላው ሰው ሚካኤል
መጠጊያ ሆኗል ሚካኤል
ትንሽ ትልቁ ደሀው ሀብታሙ
ለምኖ አግኝቷል ካምላክ በስሙ /2/

አዝ......

በብሉይ ኪዳን ሚካኤል
ከአምላክ ተልከህ ሚካኤል
ሕዝበ እስራኤልን ሚካኤል
ነጻ ያወጣህ ሚካኤል
በአዲስ ኪዳንም ድንቅ ስራ አለህ
በተአምራትህ ትፈውሳለህ
69 views17:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 20:39:31 ሞገድ ሲመታኝ ማዕበሉ
ሞን ያድነዋል ሁሉም ሲሉ
በሰላም አለፍኩ በፀጥታ
ሁሉ ተችሎ በአንተ ጌታ(2)
………..አዝ……
በአንተስ ቁስል ተፈወስኩኝ
ጌታ በፍቅርህ ተማረኩኝ
ሞቴን ሽረኸው በአንተ ሞት
ይሄው አቆምከኝ በህይወት(2)
………..አዝ……
ደጅህ ስጠና ስማፀንህ
መቼ ጨከነ ጌታ ልብህ
እንደ ቀራጩ አጎነበስኩ
ምህረት ፀጋህን ከእጅህ ለበስኩ(2)
………..አዝ……
ዘወትር እልል ብል ብዘምር
ስለገባኝ ነው ያንተ ፍቅር
ጌታ ምጠራው ስምህን
ለውጠኸው ነው ታሪኬን(2)
………..አዝ……
አይኞቼ አያዩ ከአንተ በቀር
የምትወደድ የምትፈቀር
ዘመዴ በወገኔ ሆነኸኛል
እኔን የሚችል የት ይገኛል(2)
66 views17:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 20:39:31 ✞ የፍቅር እናት

የፍቅር እናት የሰላም /2/
ይናፍቀኛል ስምሽ ሳልጠራው ስቀር ማርያም

በሂወቴ ውስጥ በኑሮዬ
ቅደሚ ከፊት ከሀኅላዬ
ተደላደለ ልቤ
አንቺ አለሽና ካጠገቤ

ምኞቴም ይስመር ትልቅ ህልሜ
ልለፍ ወደፊት ተቋቁሜ
የጌታዬ እናት ነሽ
ሀይልን ያረጋል ፀሎትሽ

እንዴት ቀራለው ከመንገድ
አደራ እናቴ አስቢኝ
ከሚያስጨንቀኝ ጠላት
ለሚያሳድደኝ አትስጪኝ

ትላንትም ዛሬም አመስጋኝ ነኝ
የለም ለነገየሚያስፈራኝ
ሜዳይሆናል ተራራ
ልጅሽ ስላለ ከኔ ጋራ
@dnzema
64 views17:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-18 20:39:31 ኢትዮጵያ ሰላምሽ ይብዛ


ኢትዮጵያ ሠላምሽ ይብዛ
ተጠለይ በእግዚአብሔር ታዛ
ሐገሬ ሠላምሽ ይብዛ
ተጠለይ በእግዚአብሔር ታዛ/፪/

/አዝማች/
ከሚራራልን ፍቅር ከሆነው
ዘላቂ ሠላም ከእግዚአብሔር ነው
ይኽን እወቂ ይኽን ተረጂ
በልብሽ ጉልበት ለእርሱ ሥገጂ


/አዝማች/
በሠይፍ ያልቃሉ ሠይፍ የሚያነሱ
የሚራራልን ሲፈርድ ንጉሡ
በቀል የእርሱ ነው አይደለም የአንቺ
በጸጋው ታጥረሽ በጸሎት በርቺ


/አዝማች/
የውጣ ውረድ የጉስቁልናው
በእግዚአብሔር ነው መከራ ማብቂያው
ሠላም ይሁን ሲል ይሆናል ሠላም
የአሳየሽውን ፍቅር አይረሳም


/አዝማች/
ማራት ኢትዮጵያን ማራት ሐገሬን
በእየሄድሁበት መጠሪያ ሥሜን
ይብቃት ሌሊቱ ይውጣላት ጸሐይ
አሁን ይዘርጋ እጅኽ ከሠማይ


/አዝማች/
እድትፈራርስ ጠላት ሸምቋል
ብርቱውን ጉልበት ከአፈር ደባልቋል
ይኽን ግፍ አስብ ዘንበል በልላት
ከአንተ በስተቀር መሄጃ የላት


/አዝማች/
ማራት ኢትዮጵያን ማራት ሐገሬን
በእየሄዱሁበት መጠሪያ ሥሜን
ይብቃት ሌሊቱ ይውጣላት ጸሐይ
አሁን ይዘርጋ እጅኽ ከሠማይ

@dnzema
@dnzema
@dnzema
ሊቀ መዘምራን ቴድሮስ ዮሴፍ
63 views17:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ