2022-05-28 16:45:25
+++++የብረሃን እናት+++++
(አጭር መጸሐፋዊ ቅኝት)(የንባብ ጥቆማ)
"ብርሃንሽም ከፀሐይ ብርሃን ይበልጣል"
መምህር ሄኖክ ኃይሌ የብርሃን እናት ብሎ ያዘጋጀው መጸሐፍ ሥነ ጽሑፉዊ ውበቱ የተጠበቀለትና በተለይ በተመስጦ ሊነበብ እና ሊያስተምር የሚችል አገላለጾችና የአጻጻፍ ስልቶች ያየሉበት ይመስለኛል ለአብነትም ጥቂቱን የመጸሐፉን ጠንካራ ጎን በተረዳውበት መስክ ልግለጥ።
፩:-አንባቢውን የትምህርቱ መአከል ማድረግ
እግዚአብሔር በቃለ መጻሕፍት ብዙ ይናገራል። ዓለሙን ሁሉ ብታተርፍ ነፍስህን ግን ብታጎድል ምን ይረበሐል ሚለውን የመጸሐፍ ቃል ተጠቀመው የመነኑ ስንቶች ናቸው። ለዚህም ነው የትኛውም አይነት መንፈሳዊ ድርሰት አማኙ የሚገለጥበት አንባቢው በሕይወቱ የሚተርጉምበት የእግዚአብሔር ማስተማርያ መንገድ ነው የምንለው። የብርሃን እናት የተሰኘው መጸሐፍ አንድ አንድድ ቦታ ላይ ትንታኔውን ገታ እያደረግ አንባቢው ወደ ራሱ እንዲመለከት እድል ይሰጣል። ምክንያቱም የመጻሕፍት ዓላማ ሕይወት መሆን ጭምር እንጂ ማቀበል ብቻ አይደለም። የብዙ አበው ታሪክ በመጸሐፍ ሰፍሮልን የምናገኘው እንደው እነርሱን ለማወቅ ብቻ ሳይሆን በእነርሱ መወደቅና መነሳት ውስጥ ራሳችንን እንድናይ መሆኑን ልብ እንበል። በዚህም ረገድ መምህር ሄኖክ ኃይሌ በጽሑፎቹ ውስጥ አንባቢው እኔስ የሚል ጥያቄ እንዲፈጥር የሚያደርጉ አገላለጾችን ይጠቀማል። አንባቢውን መአከል የሚያደርገውም በጥያቄም በምክር ሊሆን ይችላል። ለምሳሌ አንዱን ለመጥቀስ ከሔዋን ጋር ሲነጋገር ስለነበረው ስለ ዕባብና ስለ ዕጸ በለስ ከተነተነ በኋላ እንዲህ ይላል።
"ወዳጄ ይህን መጸሐፍ ማንበብህን ቆም አድርገህ የአንተን እባብ የአንተን ዕፀ በለስ ለይተህ አስብ በፍጹም በየትኛውም መንገድ በእኔ ሕይወት እባብ መጥቶ በጭራሽ አያውቅም ካልከኝ ደግሞ ትንሽ ዞር ዞር በልና አንተነትህን ከዚሁ ታሪክ ውስጥ አብረን እንፈልገው።........"
፪:-ርእሰ ጉዳዮችን በጥያቄ መልክ ማስተላለፍ
ሐሳቦችን በጥያቄ መልክ መግለጽ በተለይ በጥንት ሊቃውንት አጻጻፍ ውስጥ የተለመደ ይመስላል። በተለይ ለመደነቅና ለአንክሮ የሚጠቀሙበት ስልትም ነው። እግዚአብሔር እና ሥራውን ሌሎች ሃይማኖታዊ ክንዋኔዎችን አልያም አስደናቂ ክስተቶች ላይ በጥቅሉ ከቃል በላይ ለሆኑ ነገሮች ይህንን የአጻጻፍ ስልት አሁን ላይ በስፋት ባንመለከተውም መጠቀም የተለመደ ይመስለኛል። የብርሃን እናት መጸሐፍም በየንዑስ ርእሶች ውስጥ ተደንቆ አንባቢውን ወደመደነቅ የሚያደርስበትን በጥያቄ ምልክት የተዘጉ ትንታኔዎች አሉት። ይህ ጥያቄ የታሪኩን ባለቤት ጭምር ነክቶ ያልፉል። ለምሳሌ ሔዋንና አዳምን ገጽ ለገጽ እንደሚያናግር ሰው ስለምን በደላችሁን እያለ ፍቅራዊ ወቀሳ ሲያቀርብላቸው የምናቀው ቅዱስ አትናቴዎስን ነው። በዚህ መጸሐፍ ላይም አዳምና ሔዋንን ፍቅራዊ ጥያቄ ሲጠይቅ እንመለከታለን። በሌሎች ክፍሎች ላይ እንደተነሳበት አንባቢው ልቦና ላይ ወይ መደነቅ አልያም ልንጠይቃቸው የሚገቡትን ሁሉ እየቀደመ ይጠይቃል። ለአብነትም ሔዋንን በመጀመርያ ምዕራፉ ብዙ ያናግራታል አንድም ያነሳሳታል ስለእርሷ ሚገባውን ሁሉ ይገልጻል ቆየት ብሎ ደግሞ የትውልዱን ጥያቄ ያነሳል።
"አምላክነትን የሚያስመኝ ገዢ ሆነሽ በተፈጠርሽበት ዓለም የጎደለብሽ ምን ነገር ነበር? ገነት ውስጥ እየኖርሽ የምኖርበት ቦታዬ ይበቃኛል ማለትን እንዴት አልቻልሽም? የሰው ልጆች ሁሉ እናት የመሆን ክብር ተሠጥቶሽ ሳለ ለልጅ ልጆችሽ ሕመምና ሞትን ያወረስሽን ለምንድር ነው? ገነት ከምታህል ርስት ወጥተሽ በተረገመች ምድር የወለድሽንስ ስለምንድነው? የሚል የብዙ ትውልድ ጩኽት በሕሊናው የሚጮኽባት ሔዋን ብቻ ነች"
፫:-ርእስ የንባብ በር ነው
ለጽሑፎች የሚሰጡ ርእሶች አሁን ላይ በጣም ወሳኝነት አላቸው። እጅግ የለመድናቸውን ታሪኮች ምን አልባት ርእሳቸው ስቦን እንደ አዲስ ተመስጠን ምናነብባቸው ጊዜ አለ። ለምሳሌ ዲ/ን ሄኖክ ኃይሌ የሕማማት መጸሐፉን ጨምሮ አሁን ያለው የብርሃን እናት የተሰኘው መጸሐፍ ላይ ይህንን ርእስ አሰጣጥ ሲያስለምደን እናየዋለን። ርእሶቹ ለንባብ የሚገፋፉ እና እጅግ ሳቢዎች ናቸው። የወደቀው መልአክ በሚለው ፈንታ የሰማዩ ይሁዳ በሚል ስለ ፈታኝ ዲያቢሎስና ተዛምዷዊ ሀሳቦችን ያነሳል። አዳምና ሔዋን ነጻ ፈቃድ አላቸውን? ከሚለው ይልቅ የነጻነት እስረኞች በሚል የተተካ ብዙ ጥያቄዎች የተመለሰቦት አስተማሪ ምሳሌዎች ያሉበት ክፍል አለ። ብሥራተ ገብርኤል አልያም አብሳሪው መልአክ ከሚለው ይልቅ የሰማዩ ንስር በሚል እመቤታችንን በቅዱስ ገብርኤል አንጻር ይናገርላታል ። መጥምቁ ዮሐንስ በማኅጸን ሆኖ ስለሰጠው ክብር የሚያነሳውን ሐተታ ደግሞ "ያልተወለደው ባለቅኔ" በማለት ይዞታል። ዘመኑ መጸሐፍ ሲያነብ መጀመርያ ማውጫውን ከዛን ደግሞ ከጀርባ የተሰጡ አስተያየቶችን ይመለከታል። ስለዚህ አይቶ የሚዘጋውን ርእስ ከመስጠት አይቶ ምን ማለት ይሆን ብሎ ለማንበብ የሚጥርበትን ሳቢ ርእስ መስጠት ለአንባቢ ተደራሽ መሆን ነው ብዬ አስባለው።
፬:-የርእስና የሐተታ ተዛምዶ
አንድ መጸሐፍ እጅግ ጥሩ ርእስ ኖሮት ሐተታው ግን ደካማ ከሆነ ብዙ አመርቂ ላይሆን ይችላል። አንድ አንድ ጊዜ ለእያንድ አንዱ ክፍሎች የተሰጡ ርእሶችን ተመልክተን በጉጉት ወደሐተታ ስንገባ ወይ በድንብ አልተገለጸም አልያም ደግሞ የአጻጻፍ ስልቶ ቦዙ ግልጽ ላይሆን ይችላል። ትልቁ ነገር ሐተታ ከሚሰጠው ርእስ ጋር እኩል ውበት ሊኖረው ይገባል። መምህር ሄኖክ ኃይሌም በመጸሐፉ ለርእሱ ታማኝ መሆኑን ያሳየበት የአጻጻፍ ስልት ተጠቅሟል። ርእሱን ሚያጠናክሩ በዛ ያሉ ርእሰ ጉዳዮችን ቢዳስስም መደምደሚያው ግን የርእሱ ጭብጥ ሀሳብ ነው። በጥቅሉ ለመቃኘት ሳስብ ርእሱ ከሐተታው ጋር ደስ በሚያሰኝ ገለጻ ተዛምደዋል። ለምሳሌ ከፀሐይ አጠገብ የነበረው ኮኮብ በሚለው እጅግ ሳቢ ርእስ ውስጥ ብዙ ያልተነገረለት አረጋዊው ዮሴፍ ተጉግጿል። ርእሱ ዮሴፍንካሰተዋወቀበት ትንታኔ ጋር ያለውን ዝምድና ማውሳት ይቻላል።
፭:-ሊቃውንትንና መጻሕፍትን ማናገር
በየዘመኑ የተነሱ ከሀገር ውስጥም ውጪም ያሉ ሊቃውንት ያላስተማሩበትና ያልጻፉበት ርእስ ጉዳይ ማግኘት እጅግ ከባድ ነው። እነዚህን በእውቀትም በሕይወትም የበረቱ ሊቃውንትን አሁን ላለው አንባቢ በአንድም በሌላም አድርጎ ንግግራቸውን ማስነበብ ብልህነት ነው ትርጓሚያችንም ቢሆን ለሐተታው ማረጋገጫ "እንዲል" እያለ የመምህራንንና የመጻሕፍትን ማመሳከርያ ያቀርባል። የብርሃን እናትም ከሀገር ውስጥ ካሉት አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫን ጨምሮ በውጪ ካሉት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ቅዱስ ኤፍሬም ያዕቆብ ዘሥሩግ ቅዱስ ባስልዮስን እና እጅግ በዛ ያሉ ሊቃውንት ለእያንድ አንዱ ትንታኔው ማመሳከርያ አድርጎ አንጎራቿል። የትርጓሜ መጻሕፍትን እና ሌሎች ድርሳናትንም ሲያጣቅስ እንመለከተዋለን። እና ደግሞ የሊቃውንቱን አገላለጽ ስንመለከት ወደ ብዙ መደመም እንድንደርስ ያደርገናል። ምን አልባት መጸሐፉን ካደመቁት ነገሮች መካከል አንዱ ብዙ ጊዜ ያልሰማናቸው የሊቃውንተ ንግግሮችና እይታዎች አንደኞቹ ናቸው።
፮:-አንባብያንን ማያደክም የአጻጻፍ ስልት
184 viewsMoges abreham, 13:45