Get Mystery Box with random crypto!

እናስተውል ዓለም ምን ያህል እንደወደቀች ተመልከቱ። ብልጭልጯ ዓለም ምን ያህል እንደረከሰች አስተ | ዲያቆን ሞገስ አብረሃም|moges abreham

እናስተውል

ዓለም ምን ያህል እንደወደቀች ተመልከቱ። ብልጭልጯ ዓለም ምን ያህል እንደረከሰች አስተውሉ። ይህች ለሰው ጊዝያዊ መኖርያ ሆና የተሰጠችው ምድር ሰይጣን በሚፈልገው መልክ እንዴት እንደ ሰራት ተመልከቱ? ዓለም በጨለማው ገዢ እጅ መውደቋን ከምናየው በላይ ምን ዓይነት ምስክርነት ማቅረብ ይቻለናል። መጸሐፍ ቅዱስን ተመልክተህ ከሆነ አንድ አንድ የዓለምን እውነታዎችን መረዳት ትችላለህ። በኖኅ ዘመን የነበሩ ሰዎች የፈላው ውኃ አንገታቸው ላይ እስኪደርስ ድረስ እግዚአብሔርን ሲገዳደሩ ተመልክተናል እጅግ የተዋበችና ያመረች ሰዶም በተባለች ሃገር ይኖሩ የነበሩ ሰዎች በተመሳሳይ ጾታ ሲገናኙ እግዚአብሔር በዲን እሳት እንዲጠፋቸው አንብበናል። የባቢሎን ሰዎች እግዚአብሔርን ወጋነው ብለው ክፉ ቃል ሲያወጡ ሰምተናል የእግዚአብሔር ልጆች ከሰው ልጆች ጋር ከተዋህዶ በኋላ ምን ያህል ለምድር የከበዱ ፍጡራን እንደተወለዱ አይተናል። ተመልከቱ እነዚህ ከብዙ ሺ አመታት በፊት የነበሩ ሰይጣን የተጠቀመባቸው ትውልዶች ናቸው። አሁን እነዚህን የሚያስንቅ ትውልድ አለ። በፊልሞቻቸው በዘፈናቸው ሰይጣናዊ ተከታዮችን ለመውለድ ጥረት የሚያደረጉ ኅብረቶች ተፈጥረዋል። እነዚህ ኅብረቶች በማወቅም ባለማወቅም ካለባበሳችን አንስቶ ሰይጣንን ወደማምለክ ዝንባሌ እያደረሱን ነው። ዓለም ከየትኛውም ጊዜ በላይ ሰልጥናለች ይህ ስልጣኔ ግን ለሰይጣን አምልኮ እንዲመቹ ተደረገው ተሰርተዋል። እጅግም ተጨንቃለች ከሕመም ይልቅ በሰው ሰራሽ ምክንያት በየቦታው ደሙ የሚፈሰው ለሰይጣን መስዋዕት ሆኖ ይቀርባል። ተወዳጆች ሆይ ከየትኛውም ጊዜ በላይ እምነታችን ሚፈተንበት ጊዜ አሁን ያለንበት ወቅት ነው። ከኖኅ ዘመን ከሰዶም እና ከባቢልን ሰዎች ታሪክ እንማር። እጅግ የሚያስጨንቅ ወሬ የሰማን እንደሆነ አብዝተን እንጸልይ። ይህች አሁን ያለችው የዓለም መሪዎች ሰይጣናዊ ጥንስስ በየቤታችን መድረሱ የማይቅረ ነውና። ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግንኙነት እናጠንከር። ለአንድ ቀንም ቢሆን ከቤቱ አንለይ። አሁን በፊት የምንወድቅበት ዘመን ነው።

ዲ/ን ሞገስ አብረሃም