Get Mystery Box with random crypto!

፨፨፨ጸሎት፨፨፨ ወልደ ዳዊት ወልደ አብርሃም ኢየሱስ ክርስቶስ ወልደ እግዚአ | ቀሲስ መልአኩ ይፍሩ ዘውሉደ ብርሃን

፨፨፨ጸሎት፨፨፨
ወልደ ዳዊት ወልደ አብርሃም ኢየሱስ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር ሕያው በእንተ ቅዱስ አባ ኖብ ሰማዕት ወበእንተ ቅዱሳን ሰማዕታት ማኅበራኒሁ ለአባ ኖብ ወበእንተ ቅዱስ ስምዖን ሊቀ ጳጳሳት ዘእስክንድርያ ወበእንተ ኲሎሙ ቅዱሳን እለኮነ ተዝካረ በዓሎሙ በይእቲ እለት መሐረነ ለነ ለአበስያን አግብርቲከ ወአእማቲከ አሜን።

እግዚኦ ተዘከር ኪዳን ዘወሀብኮሙ ለቅዱሳን አግብርቲከ ወአእማቲከ እለ አስመሩ ኪያከ፣ ወሶበ ተዘከርከ ዘንተ ተዘከር ከመ መሬት ንሕነ አባስያን አግብርቲከ ወአእማቲከ፣ ኢታርእየነ ሙስናሃ ለቅድስት ሀገሪትነ ኢትዮጵያ ወለቅድስት ቤተ ክርስቲያን። ኢታጥፍአነ ተዘኪረከ ዘትካት፣ ፍጡነ ይርከበነ ሳህልከ እግዚኦ።

※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※※

የዳዊት ልጅ የአብርሃም ልጅ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፣ ስለ ቅዱስ ሰማዕት አባ ኖብ እና ስለ ማኅበርተኞቹ ቅዱሳን ሰማዕታት፣ ስለ ቅዱስ ስምዖን ሊቀ ጳጳሳት ዘእስክንድርያ ብለህ፣ በዚህችም እለት ዝክረ በዓላቸው ስለ ኾነ ስለ ሌሎቹም ኹሉ ቅዱሳን ብለህ እኛን በደለኛ የወንድና የሴት አገልጋዮችህን ማረን።

ጌታ ሆይ አንተን ደስ ላሰኙህ ቅዱሳን የገባህላቸውን ቃልኪዳን አስብ፣ ይህንም ባሰብህ ጊዜ ደግሞ እኛ በደለኞች የሴትና የወንድ አገልጋዮችህ አፈር ትቢያ መኾናችንን አስብ፣ የቅድስት ሀገራችን ኢትዮጵያን እና የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ጥፋት ፈጽሞ አታሳየን። የቀደመውን (በደላችንን) አስበህብን አታጥፋብ፣ አቤቱ ምሕረትህ ፈጥኖ ያግኘን እንጂ።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።

በቴሌግራም፥ @deaconmelakuyifru
በዩቲዩብ፥ https://www.youtube.com/channel/UCP-sKuhsHg_4HrWtcJx2r8Q

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር አሜን።