Get Mystery Box with random crypto!

በመሰረቱ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውለታ የሌለበት ኢዮጵያዊ ዜጋ የለም:: ሙስሊሙም 'ነብያችን'ብ | Daniel Tomas ኢትዮጵያዊ

በመሰረቱ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውለታ የሌለበት ኢዮጵያዊ ዜጋ የለም:: ሙስሊሙም "ነብያችን"ብሎ ሲጽፍ ከቤተክርስቲያን በተገኘ የፊደል ጥበብ ነው! ፕሮቴስታንቱ "ኢየሱስ .." ብሎ ሲጽፍ ከዝች ቤተክርስቲያን በተገኘ የጽህፈት ጥበብ ነው! ፊደልና ጽህፈት ብቻ አይደለም:: ከማህበራዊ ስነምግባር ጀምሮ እስከ ወዘተ...ለአገር ብዙ ውለታ የዋለች ቤተክርስቲያን ናት:: ታላላቆቻችንን ዝቅ ብለን ጉልበት እንድንስም ያሰተማረች ቤተክርስቲያን ናት!
በማህበራዊም በኢኮኖሚያዊም በፖለቲካዊም በታሪካዊም ሆነ በባህላዊ... በሁሉም ዘርፍ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አሻራ ያላረፈበት የኢትዮጵያ ተብሎ የሚገለጽ ነገር የለም!
በጥቅሉ ከዚች ቤተክርስቲያን በየዘርፉ ያልተጠቀመ ኢትዮጵያዊ ዜጋ የለም!
በዓላቱዋ የቱሪስት መስህቦች ናቸው!ባህሎቹዋ የጋራ እሴት ተብለው የተመዘገቡ ናቸው!
በየዘርፉ ጠለቅ ብለን ብንመረምር መላው ኢትዮጵያዊ ዜጋ የዚች ቤተክርስቲያን ውለታ ያለበት ነው! ዛሬ ቀን አግኝተው በቤተክርስቲያን ላይ አፋቸውን የሚከፍቱት ሳይቀሩ አንደበታቸውን አላቅቀው አፋቸውን ከፍተው እንዲናገሩና መልዕክታቸውን እንዲያስተላልፉ ያደረገች ቤተክርስቲያን ናት! ተናጋሪውም ከቤተክርስቲያን ባገኘው ጥበብ ይናገራል ሰሚውም ከቤተክርስቲያን ባገኘው ጥበብ ይሰማልና!
ይህ ስለሆነ ጉዳዩ የሐይማኖቱ ተከታዮች ብቻ ሳይሆን የመላው ዜጋ የጋራ ጉዳይ መሆኑ መታወቅ አለበት ለማለት ነው::
በዚህ የማይስማማ የሌላ ሐይማኖት ተከታይ ካለ ደግሞ...ብልጽግና ጸረ ሐይማኖት የሆነ መንግስታዊ ማኑፌስቶ ያለው ስለሆነ ዛሬ በኦርቶዶክስ ላይ የተፈጸጸው አስጸያፊ ድርጊት ነገ በሌላው እንደሚሆን ተገንዝቦ በጋራ ቢቆም ያዋጣዋል!
በመጨረሻ ለዚህ ገጽ ተከታዮች...."የዓለም ቅርስ ጥበቃ ድርጅት ተልዕኮው...መጠነ ሰፊ በጀቱ..... የባህል ወረራ...." "ትግራይና አማራ እንዳይታረቁ አድርጎ ማሽመድመድ...የጋራ እሴቶቻቸውን የጋራ እንዳይሆኑ ማድረግ.... በጥቅሉ ሰሜኑን የኢትዮጵያ ክፍል የትርምስ ቀጠና አድርጎ ማስቀጠል...አምሐራን በወኪል ፓርቲው በኩል.....ማፍረክረክ.... በመጨረሻም...." የሚሉትን ገጾች ለማስታወስ እወዳለሁ::