Get Mystery Box with random crypto!

ሰላም ሰላም እንዴት ናችሁ የባህር ዳር ዲሽ ተከታታዮች ዛሬ ይዤላችሁ የመጣሁት #ዲሻችን_በየጊ | DAN® DI$H W°rክ & In£°

ሰላም ሰላም እንዴት ናችሁ የባህር ዳር ዲሽ ተከታታዮች ዛሬ ይዤላችሁ የመጣሁት
#ዲሻችን_በየጊዜው_እንዲበላሽ_የሚያደርጉ_ዋና_ዋና_ችግሮች እና #ምክኒያቶች_ምንድን ናቸው።

ይህ ለጀማሪ የዲሽ ባለሙያዎች ወሳኝ መረጃ ነዉ።

ይህ መረጃ ጠቃሚ ሁኖ ካገኙት ሸር ማድረግዎን እንዳይረሱ

1. #የዲሽ_መጠን_ማነስ

የዲሽ መጠን ሲያንስ #Signal የመሳብ መጠን ይቀንሳል ሆኖም ሀገራችን ውስጥ #ለምሳሌ ናይልሳት እና ኢትዮ ሳት ያለው ሽፋን ከፍተኛ ስለሆነ ባለ 60 Cm ዲሾችን ልንጠቀም እንችላለን ነገር ግን እንደ #Dstv #Amos 4W #Bein Sport የመሳሰሉት የተሻለ ኳሊቲ ለማግኘት 90CM እና ከዛ በላይ የዲሽ ሳህን ብንጠቀም ይመረጣል።

https://t.me/daneyy

2. #የዲሽ_ብሎኖች_ስፓናቶ_መሆን

በተደጋጋሚ በሚፈጠር ብልሽት ምክንያት ብሎኖች ሲታሰሩና ሲፈቱ ለዚህ የመላላት ችግር ይጋለጣሉ።

3. #የLNB_መድከም

ከተሰራበት ፋብሪካ አልያም ብዙ ጊዜ ከማገልገሉ የተነሳ የሚፈለገውን Quality ያለመስጠት ችግር።

4.#የዲሽ_ገመድ_(Cable)_መቆራረጥ

ገመድ በተቆራረጠ ቁጥር Strength ይቀንሳል። ካልተቻለ ከሁለት ጊዜ በላይ ባይቀጠል መልካም ነው።  ከዚህ በተጨማሪ ለዝገትም ያጋልጣቸዋል ።

5. #የኬብል_Connector

አካባቢ ዝገት የዝናብ ውሀ ስለሚያገኛቸው ለዝገት ይጋለጣሉ ከዛጉ ደግሞ Signal አያስተላልፋም።

6. #የዲሽ_ማስቀመጫ_ጣሪያ_ሁኔታ

የዲሽ ማስቀመጫ ጣሪያ በዚህ ስራ ከፍተኛ የሆነ ሚና አለው። ጣሪያ ከስር በርካታ አግዳሚዎች ከሌሉትና የቆርቆሮው ጌጅ ዝቅተኛ ከሆነ በቀላሉ ቦታውን ይለቃል።

7. #የአካባቢው_በዛፍ_(በግንብ) የመሸፈን ሁኔታ

ሳተላይት የሚመጣው አግድም ከሆነ በዛፍም ሆነ በግንብ በቀላሉ የመከለል ችግር ይገጥመዋል። የዲሹ አቅጣጫ ወደ ምዕራብ ከሆነ ዲግሪ እየቀነሰ ሲመጣ እንዲሁም የዲሹ አቅጣጫ ወደ ምስራቅ ከሆነ ዲግሪ እየጨመረ ሲመጣ።

8. #የዲሽ_ማስቀመጫ_ጣውላ_መበስበስ

አብዛኛው ተጠቃሚ የዲሽ ማስቀመጫው ጣውላ ስለሆነ ፀሐይና ዝናብ ሲፈራረቅበት ይበሰብሳል። ማያያዣ  ሚስማሮች መልቀቅና መነቃነቅ
ከጊዜ በኋላ ጣውላው ሲበሰብስ ሚስማሮች እየለቀቁ ሲሄዱ ዲሹ በትንሽ ነፋስ ስክራች ያደርጋል።


9. #የስዊች(ስፒሊተር) _መድከም/አለመስራት

Switch ለዝናብ ውሀ ከተጋለጡ ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል ይበላሻሉ።

10. #የአንዳንድ_ሳተላይቶች_Frequency_ደካማ_መሆን

የአንዳንድ ሳተላይቶች ፍሪኩየንሲ የማይጨበጥ አይነት ይሆናል፡፡
ለምሳሌ፦ ናይልሳት ላይ 11096 H እንዲሁም ያህሳት ላይ 12015 H እና 11785 H

11. #የዲሽ_ባለሙያው_ክህሎት_ችግር

አንዳንድ ባለሙያዎች ለስራው ጀማሪዎች በመሆናቸው ምክንያት በትክክል Quality ላይመጣላቸው ይችላል።

12. #የተጠቃሚው_ስህተት_ናቸው

በተለይ እዚህ ላይ ብዙ ጊዜ የሚስተዋለው ችግር ከሪሲቨሩ ጀርባ የሚሰካውን ኮኔክተር መነካካትና የአሉሚኒየሙን ከቀጫጭን ሽቦዎች ከመዳቡ ወፍራም ሽቦ ጋር ማገናኘት።

13. ህፃናት ባለማወቅ Menu ውስጥ በመግባት የማይነካኩ Settingኦችን የመነካካት ችግሮች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

════❁✿❁ ═══════

መረጃዉን ከወደዱት ሸር በማድረግ አብሮነታችሁን አሳዩን

https://t.me/daneyy