Get Mystery Box with random crypto!

አራስ ልጁንና የ5 ወር ልጇን የገደለው ... በዎላይታ ዞን ቦዲቲ ከተማ አንድ አባት የራሱን ህይ | Daily News 🇪🇹

አራስ ልጁንና የ5 ወር ልጇን የገደለው ...

በዎላይታ ዞን ቦዲቲ ከተማ አንድ አባት የራሱን ህይወት ጨምሮ የሶስት ሰው ህይወት ማጥፋቱን ፖሊስ ገልጿል። ግለሰቡ የራሱን፣ የልጁንና የልጅ ልጁን ህይወት ማጥፋቱን ነው የከተማው ፖሊስ ጽህፈት ቤት አዛዥ ምክትል ኢንስፔክተር ወልዴ ጊሊሶ የገለጹት።

አቶ አምዴ ሙሳ የተባለው ይኸው ግለሰብ ከዚህ ቀደም አልፎ አልፎ ከባለቤታቸው ጋር አለመግባባትና ግጭት ይፈጥር እንደነበር መረጃዎች እንደምጠቁሙ አዛዡ አስረድተዋል።

ድርጊቱ የተፈጸመው 17/01/2015 ዓ.ም ረፋድ ላይ ሲሆን ወልዳ እቤት ውስጥ የተኛች የ28 ዓመት አራስ ልጁንና የ5 ወር ልጇን ገድሎ  ሲወጣ ግቢ ውስጥ ባለው ውሃ በትልቅ የውሃ ገንዳ ውስጥ በመግባቱ የግለሰቡ ህይወትም ማለፍ መቻሉን ተናግረዋል።

የወንጀሉን ምክንያት ፖሊስ በማጣራት ላይ እንደሚገኝም ምክትል ኢንስፔክተር ወልዴ ጊሊሶ ለዎላይታ ታይምስ ሚዲያ በስልክ አስረድተዋል።

ምንጭ: https://wolaitatimes.com/
@dailyNews_et @dailyNews_et