Get Mystery Box with random crypto!

በምዕራብ ሸዋ ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ15 ሰዎች ህይወት አለፈ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸ | Daily News 🇪🇹

በምዕራብ ሸዋ ዞን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ15 ሰዎች ህይወት አለፈ

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን አደዓ በርጋ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ15 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

የትራፊክ አደጋው ከኢንጪኒ ከተማ ወደ ሽኖ ከተማ ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ የህዝባ ማመላለሻ አውቶብስ ከተሳቢ ጋር ተጋጭቶ መከሰቱ ተገልጿል፡፡

በአደጋውም የ15 ሰዎች ህይወት ወዲያውኑ ያለፈ ሲሆን፤ በ30 ሰዎች ላይ ከባድ እንዲሁም በኹሉት ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት መድረሱን ከወረዳው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

@dailyNews_et @dailyNews_et