Get Mystery Box with random crypto!

ዳግም ምጽዓት

የቴሌግራም ቻናል አርማ dagmele19 — ዳግም ምጽዓት
የቴሌግራም ቻናል አርማ dagmele19 — ዳግም ምጽዓት
የሰርጥ አድራሻ: @dagmele19
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 366
የሰርጥ መግለጫ

It's you find new Orthodox new
#ልጄ_ሆይ_እንዳትሆን_መናፍቅ_ሐይማኖትህን_እወቅ።
በዚህ ቻናል የእትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
መዝሙሮች እና ትምህርቶች ይገኛሉ።
ለሌሎች ሼር ያድርጉ
👉ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር👈
👇click & Share it 👇
@Dagmele19
🚷Leaveአትበሉችግርካለአሳውቁኝ
➛ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት
በ @Dagmele19_Bot

Ratings & Reviews

1.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2021-10-30 21:37:38 ✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

✞✞✞ ጥቅምት 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ✞✞✞

✞✞✞ እግዝእትነ ማርያም ✞✞✞

+እመቤታችን ድንግል ማርያም የወልደ እግዚአብሔር
እናቱ ናትና ሁሉን ትችላለች:: እርሱን ከሃሊ (ሁሉን ቻይ)
ካልን እርሷን "ከሃሊት" ልንላት ይገባል:: ልክ ልጇ ሁሉን
ማድረግ ሲችል በትእግስት ዝም እንደሚለው እመ
ብርሃንም ስንት ነገር እየተደረገ: በእርሷ ላይም አንዳንዶቹ
ስንት ነገርን ሲናገሩ እንደማትሰማ ዝም ትላለች::

+እኛ ኃጥአን ንስሃ እስክንገባ ድረስም "ልጄ! የዛሬን
ታገሣቸው?" እያለች ትለምንልናለች:: ቸሩ ልጇም ሊምረን
እንጂ ሊያጠፋን አይሻምና "እሺ እናቴ!" እያለ ይኼው
በዚህ ሁሉ ክፋታችን እስከ ዛሬ ድረስ አላጠፋንም::
*ቸር ነው
*መሐሪ ነው
*ይቅር ባይ ነው
*ታጋሽ ነው
*ርሕሩሕ ነው
*ቂምም የለውም:: በንስሃ ካልተመለስን ግን አንድ ቀን
መፍረዱ አይቀርምና ወገኖቼ ንስሃ እንግባ: ወደ እርሱም
እንቅረብ::

+ይህቺ ዕለት ለእመቤታችን እሥረኞችን የምትፈታባት
ናት:: የሰው ልጅ በ3 ወገን እሥረኛ ሊሆን ይችላል::
በሥጋዊው:- አጥፍቶም ሆነ ሳያጠፋ ሊታሠር ይችላል::
በመንፈሳዊው ግን ሰው በኃጢአት ማሠሪያ የሚታሠረው
በጥፋቱ ብቻ ነው::

+ሌላኛው ማሠሪያ ደግሞ ማዕሠረ ደዌ (በደዌ ዳኝነት)
መታሠር ነው:: መታመም የኃጢአተኛነት መገለጫ
አይደለም:: ምክንያቱም ከቅዱሳን ወገን ከ80 %
(ፐርሰንቱ) በላይ ድውያን ነበሩና::

+ታዲያ በዚህች ዕለት እመ በርሃን 3ቱንም ማሠሪያዎች
እንደምትፈታ እናምናለን:: በእሥር ቤትም: በኃጢአትም
ሆነ በደዌ ማሠሪያ የታሠርን ሁላችን በዚሁ ዕለት
እንድትፈታን የአምላክ እናትን እንለምናት::

+በ3ቱም ማሠሪያዎች የታሠሩ ወገኖቻችንንም እያሰብን
"ይባእ ቅድሜከ ገዐሮሙ ለሙቁሐን-የእሥረኞች ጩኸት
ወደ አንተ ይድረስ" እያልን (መዝ. 78:11) ልንጸልይ
ይገባል::

+እመ ብርሃንንም እንደ ሊቃውንቱ:-
"እማእሠረ ጌጋይ ፍትሕኒ ወላዲተ ክርስቶስ አምላክ:
እምነ ሙቃሔ ጽኑዕ ወእማዕሠር ድሩክ:
ከመ ፈታሕኪዮ ዮም ለማትያስ ላዕክ::" እንበላት::

+" ቅዱስ አልዓዛር ሐዋርያ "+

+ቅዱስ አልዓዛር በሃገረ ቢታንያ ከእህቶቹ ማርያና ማርታ
ጋር ይኖር ነበር:: ሦስቱም ድንግልናቸውን ጠብቅው
ጌታችንን ያገለግሉት ነበርና አልዓዛርን ከ72ቱ አርድእት
ማርያና ማርታን ደግሞ ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት
ቆጥሯቸዋል::

+በወንጌል ጌታችን ይወዳቸው እንደነበር ተገልጧል::
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሲወድ የሚያበላልጥ ሆኖ
አይደለም:: ይልቁኑ በምሥጢር እነርሱ ተወዳጅ
የሚያደርጋቸውን ሥራ ይሠሩ እንደነበር ሲነግረን ነው
እንጂ::

+ቅዱስ መጽሐፍ እንደነገረን ጌታችን በነአልዓዛር ቤት
በእንግድነት ይስተናገድ ነበር:: በመጨረሻዋ ምሴተ
ሐሙስም ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለሐዋርያቱ
ያቀበላቸው በእነዚህ ቅዱሳን ቤት ውስጥ ነው::

+ቅዱስ አልዓዛር በጽኑዕ ታሞ አርፏል:: ቅዱሳት እህቶቹ
ማርያና ማርታ ከታላቅ ለቅሶ ጋር ዕለቱኑ ቀብረውታል::
(ዮሐ.11)

ቸር ጌታችን ክርስቶስ ከ4 ቀናት በኋላ ሊያስነሳው
ይመጣል::

+ለስም አጠራሩ ስግደት: ክብር: ጌትነት ይድረሰውና
አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ አልዓዛር ባረፈ በአራተኛው
ቀን ወደ ቢታንያ ደረሰ:: ማርታ ቀድማ ወጥታ ከእንባ ጋር
ተቀበለችው::

+'አዳም ወዴት ነህ' ያለ (ዘፍ. 3) የአዳም ፈጣሪ
'አልዓዛርን ወዴት ቀበራችሁት' አለ:: ቸርነቱ: ባሕርዩ
ያራራዋልና ማርያም ስታለቅስ ባያት ጊዜ አብሮ አለቀሰ::

+ከዚያም በባሕርይ ስልጣኑ "አልዓዛር አልዓዛር" ብሎ
አልዓዛርን አስነሳው:: ይሕች ተአምርም በአይሁድ ዘንድ
ግርምት ሆነች:: ለጌታም የሞት ምክንያት አደረጉዋት::
ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት አድርጋ
እንዲህ ታስተምራለች:: (ዮሐ. 11:1-ፍጻሜው)

+ቅዱስ አልዓዛር ጌታችን ካስነሳው በኋላ በበዓለ ሃምሳ
መንፈስ ቅዱስን ተቀብሎ (ቁጥሩ ከ72ቱ አርድእት
ነውና): ለ40 ዓመታት ወንጌልን አስተምሮ: በ74 ዓ/ም
አካባቢ ቆዽሮስ ውስጥ አርፏል::

+" ፍልሠት "+

+ይህቺ ዕለት ለቅዱሱ ሐዋርያ በዓለ ፍልሠቱ ስትሆን ይህ
የተደረገውም በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው:: ቅዱሱ
ያረፈው ቆዽሮስ ውስጥ ነው:: ግን ባልታወቀ ጊዜና
ምክንያት ወደ ኢየሩሳሌም ሒዷል::

+አንድ ቀንም በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ኢየሩሳሌም
ውስጥ ሲቆፍሩ አንድ አንድ ሳጥን አገኙ:: በላዩ ላይ
ደግሞ "ይህ የጌታ ወዳጅ የአልዓዛር ሥጋ ነው" የሚል
ጽሑፍ አግኝተው ደስ ተሰኝተዋል:: በታላቅ ዝማሬና
ፍስሐም ከኢየሩሳሌም ወደ ቁስጥንጥንያ አፍልሠውታል::
+የጌታችን ቸርነቱ: የአልዓዛር በረከቱ ይድረሰን::

+" አባ ዮሐንስ ዘኢየሩሳሌም "+

+እኒህ ጻድቅ ሰው ግብጻዊ ሲሆኑ በሰፊው የሚታወቁት
በኢትዮዽያና በኢየሩሳሌም ነበር:: ገና በወጣትነት
የጀመሩትን የተጋድሎ ሕይወት ገፍተው በበርሃ ሲኖሩ
የወቅቱ የግብጽ ሲኖዶስ ከበርሃ ጠርቶ የኢየሩሳሌም
ዻዻስ እንዳደረጋቸው ይነገራል::

+በቅድስት ሃገርም በንጽሕናና በመንኖ ጥሪት ወንጌልን
እየሰበኩ ኑረዋል:: አባ ዮሐንስ የነበሩበት ዘመን 14ኛው
መቶ ክ/ዘመን ሲሆን የወቅቱ የኢትዮዽያ ንጉሥ ደጉ አፄ
ዳዊት ነበሩ::

+ንጉሡ የግብጽ ክርስቲያኖችን ደም ለመበቀል (በወቅቱ
ከሊፋዎች ያሰቃዩዋቸው ነበር) እስከ ላይኛው ግብጽ
ወርደዋል::
በሃገር ውስጥ ያሉ ተንባላት አባሪዎቻቸውንም ቀጥተዋል::
በዚህ የተደናገጠው የግብጹ ሡልጣን 'አስታርቁኝ' ብሎ
ስለ ለመነ ለእርቅ የተመረጡ አባ ዮሐንስና አባ ሳዊሮስ
ዘምሥር ናቸው::

+እነዚህ አባቶች በ1390ዎቹ አካባቢ ወደ ኢትዮዽያ
ከመጡ በኋላ አልተመለሱም:: ምክንያቱም ደጉ አፄ
ዳዊት እጅግ ስለ ወደዷቸው 'አትሔዱም' ብለው
ስላስቀሯቸው ነው:: እንዲያውም ለግማደ መስቀሉ
መምጣት ትልቁን አስተዋጽኦ ያደረጉት አባ ዮሐንስ
ሳይሆኑ አይቀሩም:: ዛሬ የጻድቁ ዕረፍታቸው ነው::

+አምላከ ቅዱሳን ስለ ድንግል እናቱ ብሎ ከኃጢአት ሁሉ
ማሠሪያ ይፍታን:: የወዳጆቹን በረከትም አያርቅብን::

+ጥቅምት 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.እግዝእትነ ማርያም
2.ቅዱስ አልዓዛር ሐዋርያ
3.አባ ዮሐንስ ዘኢየሩሳሌም
4.ቅዱስ ኢዩኤል ነቢይ
5.ቅዱስ ማትያስ ረድእ

+" ጌታ ኢየሱስም 'ብታምኚስ የእግዚአብሔርን ክብር
እንድታዪ አልነገርሁሽምን?' አላት... ይሕንም ብሎ በታላቅ
ድምጽ 'አልዓዛር ሆይ ወደ ውጭ ና' ብሎ ጮኸ::
የሞተውም እጆቹና እግሮቹ በመግነዝ እንደ ተገነዙ ወጣ::
ፊቱም በጨርቅ እንደ ተጠመጠመ ነበረ:: ጌታ ኢየሱስም
'ፍቱትና ይሂድ ተውት' አላቸው::" (ዮሐ. 11:40-44)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
https://t.me/Dagmele19
475 views18:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-10-29 00:07:09 https://t.me/joinchat/VcP10SXJwkJZ8soW
327 views21:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-22 09:46:54
543 views ° ꧁༺𓅂𝓑𝓲𝓷𝓲𝔂𝓸𝓾 ༻꧂° , 06:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-22 09:44:57 Join us
ኦርቶዶክሳዊ ምስሎች
https://t.me/elohe_picture
507 views ° ꧁༺𓅂𝓑𝓲𝓷𝓲𝔂𝓸𝓾 ༻꧂° , 06:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-09-11 10:34:18 ወትባርክ አክሊለ ዓመተ ምሕረትከ
መዝ ፷፬ ፥ ፲፩




እንቋዕ አብጽሐክሙ አብጽሐነ እምዘመነ ማቴዎስ ኀበ ዘመነ ማርቆስ በሰላም በፍቅር ወበጥዒና ሠናይ በዓል ይኩን ለኲልክሙ።

እንኳን ከዘመነ ማቴዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ በሰላም በፍቅር እና በጤና አደረሳችሁ አደረሰን።


ሠናይ ሐዲስ ዓመት


https://t.me/Dagmele19
598 views ° ꧁༺𓅂𝓑𝓲𝓷𝓲𝔂𝓸𝓾 ༻꧂° , 07:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-12 03:11:08
995 views00:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-12 03:11:07 ቅዱስ ጳውሎስ

ጳውሎስ ማለት ንዋይ ህሩይ ማለት ነው። ሐዋ. ፱፡ ፲፭ (9፡15) አንድም ብርሃን ማለት ነው። ዘዳ.፲፬፡፪ አንድም መድቅዕ ማለት ነው። ቀዳሚ ስሙ ሳዖል ነው። ሳዖል ማለት ጸጋ እግዚአብሔር የበዛለት ማለት ነው። ትውልዱ ከነገደ ቢኒያም ነው። ፊሊ. ፫፡፭ አባቱ ዮስአስ ይባላል።

የተወለደው ጌታ በተወለደ በ፭ (5) ዓመት በጠርሴስ ነው። ከ፲፭ ዓመቱ ጀምሮ ኢየሩሳሌም በታላቅ እህቱ ቤት ተቀምጦ ከመምህር ገማልያል ሕገ ኦሪትን ተምሯል። በወንጌል ያመነው ጌታ ባረገ በ፰ኛው ዓመት ነበር። ጌታም በደማቆ መብረቅ ጥሎበት ሳኦል ሳኦል ስለምን ታሳደኛለህ ብሎ ታርቆታል። ከ፸፪ (72) አርድእት አንዱ የሆነው ሐናንያ ጌታ በራዕይ ታይቶት ጳውሎን አስተምረህ አሳምነህ አጥምቀው አለው። እርሱም በእጁ ገና አይኑ በዳሰሰው ጊዜ አይኑን አሳውሮት የነበረው እንደ ቅርፊት ወድቆለታል። ሐዋ.፱፡፩-፲፱ (9፡1¬-19)

ከዚያ በኋላ በክርስቶስ እመኑ እያለ አስተምሯል። ብዙዎችንም አስተምዎ አጥምቋል። ሐዋ. ፲፬፡፰-፲፰ ብዙውንም አሳምኗል። በወይኒም ታስሮ በነበረበት ወቅት ብዙ ሰዎችን አሳምኗል። ጳውሎስ ግን ተቸገረና ዘወር ብሎ መንፈሱ፤ ከእርስዋ እንድትወጣ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አዝሃለሁ አለው፤ በዚያም ሰዓት ወጣ።

ጌቶችዋም የትርፋቸው ተስፋ እንደ ወጣ ባዩ ጊዜ ጳውሎስንና ሲላስን ይዘው ወደ ገበያ በሹማምት ፊት ጐተቱአቸው፤ ወደ ገዢዎችም አቅርበው። እነዚህ ሰዎች አይሁድ ሆነው ከተማችንን እጅግ ያናውጣሉ። እኛም የሮሜ ሰዎች ሆነን እንቀበላቸውና እናደርጋቸው ዘንድ ያልተፈቀደልንን ልማዶች ይናገራሉ አሉ።

ሕዝቡም አብረው ተነሡባቸው፥ ገዢዎቹም ልብሳቸውን ገፈው በበትር ይመቱአቸው ዘንድ አዘዙ፤ በብዙም ከደበደቡአቸው በኋላ ወደ ወኅኒ ጣሉአቸው፥ የወኅኒውንም ጠባቂ ተጠንቅቆ እንዲጠብቃቸው አዘዙት። እርሱም የዚህን ዓይነት ትእዛዝ ተቀብሎ ወደ ውስጠኛው ወኅኒ ጣላቸው፥ እግራቸውንም በግንድ አጣብቆ ጠረቃቸው። በመንፈቀ ሌሊት ግን ጳውሎስና ሲላስ እየጸለዩ እግዚአብሔርን በዜማ ያመሰግኑ ነበር፥ እስረኞቹም ያደምጡአቸው ነበር ድንገትም የወኅኒው መሠረት እስኪናወጥ ድረስ ታላቅ የምድር መንቀጥቀጥ ሆነ፤ በዚያን ጊዜም ደጆቹ ሁሉ ተከፈቱ የሁሉም እስራት ተፈታ።

የወኅኒውም ጠባቂ ከእንቅልፉ ነቅቶ የወኅኒው ደጆች ተከፍተው ባየ ጊዜ፥ እስረኞቹ ያመለጡ መስሎት ራሱን ይገድል ዘንድ አስቦ ሰይፉን መዘዘ። ጳውሎስ ግን በታላቅ ድምፅ ሁላችን ከዚህ አለንና በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ ብሎ ጮኸ። መብራትም ለምኖ ወደ ውስጥ ሮጠ፥ እየተንቀጠቀጠም ከጳውሎስና ከሲላስ ፊት ተደፋ፤ ወደ ውጭም አውጥቶ። ጌቶች ሆይ፥ እድን ዘንድ ምን ማድረግ ይገባኛል? ኣላቸው።
እነርሱም በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን አንተና ቤተ ሰዎችህ ትድናላችሁ አሉት።

ለእርሱና በቤቱም ላሉት ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ተናገሩአቸው። በሌሊትም በዚያች ሰዓት ወስዶ ቍስላቸውን አጠበላቸው፥ ያን ጊዜውንም እርሱ ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር ተጠመቀ፤ ወደ ቤቱም አውጥቶ ማዕድ አቀረበላቸው ፥ በእግዚአብሔርም ስላመነ ከቤተ ሰዎቹ ሁሉ ጋር ሐሤት አደረገ። ሐዋ. ፲፮፡፲፰-፴፬ (16፡18-34) ሕሙማንንም ሕሙም መስሎ አስተምሯል። ፩ቆሮ.፱፡፳፪ (1ቆሮ.9፡22) ፲፬ መልዕክታትንም ጽፏል።

ከዚህ በኋላ በ69 ዓ.ም ሮም ሲያስተምር ኔሮን ቄሣር አስጠሩት ሲል በንጉሱ ፊት ሲቀርብ መስቀሉን ይዞ ቀረበ። ንጉሱ ተቆጥቶ በሰይፍ ቅጡ አለ። በመጎናጸፊያም ሸፍኖ ሰይፎታል። ደሙም ሰማየ ሰማይ ወጥቶ ቀተሉኒ በዓመጻ እያለ ተካሷቸዋል። ሲያልፍም የ72 ዓመት አረጋዊ ነበር። ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር የሞቱት በአንድ ቦታ በአንድ ቀን ነበር። ይህም ሐምሌ ፭ ነው።

ምንጭ፡- ገድለ ሐዋርያት፣ ዜና ሐዋርያት፣ ነገረ ቅዱሳን ቁጥር ፪፣ መዝገበ ታሪክ

የእግዚአብሔር ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን መላእክት ተራዳኢነት፣ የጻድቃን፣ የሰማዕታት፣ የቅዱሳን ሐዋርያት፣ የቅዱሳን አበው መነኮሳት፣ የቅዱሳት አንስት፣ የደናግላንና የቅዱሳን ሁሉ ምልጃና ቃል-ኪዳናቸው ባለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን ይቆየን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ለዘበቅዱሳኒሁ ይሴባሕ ይእዜኒ ወዘልፈኒ ወለዓለም ዓለም አሜን፡፡ ወአሜን ለይኩን ለይኩን፡፡ አነሳስቶ ያስጀመረኝ አስጀምሮ ያስጨረሰኝ የቅዱሳን አባቶቻችን አምላክ ይክበር ይመስገን አሜን፡፡

ለወዳጅዎ ሼር ያድርጉ!
@dagmele19
@Dagmele19
990 views00:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-03 22:20:57
843 views19:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2021-07-03 22:20:57
795 views19:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ