Get Mystery Box with random crypto!

​አንድ ወጣት ድምፁን ከፍ አድርጎ ድንግል ማርያም አታማልድም አታማልድም እያለ በአደባባይ ይጮሃል: | ዳግም ምጽዓት

​አንድ ወጣት ድምፁን ከፍ አድርጎ ድንግል ማርያም አታማልድም አታማልድም እያለ በአደባባይ ይጮሃል:: ከዛ ድንገት እያለፉ የነበሩ አንድ አባት ድምጽ ይስሙና ወደ ወጣቱ ጠጋ ብለው ልጄ አንዴ ላስቸግርህ ከዛ ፊት ለፊት ካለው ሱቅ 1 ኪሎ ብርትኳን አምጣልኝ አሉት ወጣቱም እሽታውን ገለፀላቸው አባትም ብርትኳኑን አንዳችም ሳያስቀሩ ከበሉ በኃላ ልጄ ብርትኳኑ እንዴት ነው? ይጣፍጣል አይደል ?አሉት ወጣቱም አንዴ ሰውዬ ያምዎታል እንዴ ብርትኳኑን እኮ ብቻወትን ነው የበሉት እና እንዴት ጣሙን ላውቅ እችላለሁ አላቸው በተረጋጋ አንደበት አባም አየህ ልጄ ልክ እንደዚህ ብርትኳን የድንግል ማርያም ጣዕሟ አልገባህም ስለዚህ ልጄ ወደ ቤቷ ግባ ጣዕሟንም ቅመሰው ያኔ የድንግል ጣዕም ይገባሃል አሉት ይባላል፡፡



እኛስ ተመርጠን ምልጃዋን ተቸርን፣ ረድኤቷን ቀመስን ክብር ምስጋና ይግባት።