Get Mystery Box with random crypto!

የማይቆም ነው! ፨፨፨///////፨፨፨ የማያቆም የእውቀት ጥማት፣ የማያቆም ጥረት፣ የማያባራ ተጋድሎ | ስነ-ልቦናዊ መፍትሔ

የማይቆም ነው!
፨፨፨///////፨፨፨
የማያቆም የእውቀት ጥማት፣ የማያቆም ጥረት፣ የማያባራ ተጋድሎ፣ የማይሸበር ድፍረት፣ የማይረበሽ ፅናት፣ የሚሳሳት የሚታረም፣ የሚወድቅ የሚነሳ ማንነት ሁሌም በመንፈስ የጠነከረ በአካል የጎለበት ማንነት ነው። ትናንት ከትናንት ወዲያ ያወከው፣ የተረዳሀውና የገባህ ነገር መቼ እንደሚጠቅምህ አታውቅም፤ እስከ ዛሬ የተማመንክበት፣ ተስፋም ያደረከው አምላክህ የት እንደሚያደርስህ አታውቅም፤ ባለፈው ጊዜያት የጣርከው ጥረት፣ የለፋሀው ልፋት መቼ እንደሚከፍልህ አታውቅም። ጥረትህ ግን አያቆምም፣ ትግለህ አይገታም፣ ጉልበትህ ሸብረክ አይልም። በአዕምሮህ ትልቅ ነገር ይመላለሳል፤ በፅናትህ ልክ የምትደርስበት፣ በድፍረትህ መጠን የምትጋፈጠው፣ ታግለህለት፣ ወድቀህለት የምታሸንፈው፤ ተፈትነህ የምታልፍለት ድንቅ ሃሳብ አለህ።

አዎ! ጀግናዬ..! የማይቆም ነው! ለእውቀት ያለህ ፍላጎት፣ ለማወቅ የምታደርገው ጥረት የማይቆም ነው። ብዙ ባወክ ልክ ብዙ እንደምታድግ ገብቶሃል። የማትደራደርበት ፅኑ አቋም አለህ፤ ተስፋ ያለመቁረጥ፣ ያለማቆም ብርቱ አቋም። በሁለቱ ማንነት በስንፍናና በብርታቱ መሃከል ብትዋጥም ቀደሚው ምርጫህ ብርቱው፣ ጥንካሬው፣ ተስፈኛው፣ አላሚው፣ ሞካሪው፣ አድራጊው ነው። ፍላጎትህ እስካልቆመ ጥረትህ የሚቆምበት ምክንያት የለም። ግበዓት /resource / ቢያልቅም፣ የሰው ልጅ ፈጣሪነት /creativity / እንዳያልቅ ተደርጎ፣ መጨረሻ ሳይበጅለት ተሰቶናልና አውጥትህ ተጠቀመው።

አዎ! ክፍያውን አትወቅ፤ ድርሻህ አይታወቅ ጥረትህ ግን አያቆምም። እውነታውን ትቀበላለህ፤ የዛሬ ትግልህ ዛሬ አይከፍልህም፤ የዛሬ ልፋትህ ዛሬ አያሳርፍህም፤ የዛሬው ተጋድሎህ ውጤት ግዜያትን ይወስዳል። በልዩነት ማሰብ ትጀምራለህ፤ እንደ አብዛኛው ሰው በፈጣን ተግባር ፈጣን ውጤት ጠባቂ አይደለህም። ሂደቱ ይማርክሃል፤ በጥበቃ ውስጥ ታድጋለህ፤ በሰነከው ተስፋ በተማመንከው አምላክ፣ በታመንከው በእራስህ፣ ትልቅ ያልከው ቦታ ትደርሳለህ። ፍላጎትህ ጥራት ነው፤ ተግባርህ በየጊዜው እየተሻሻለ፣ እያደገ የሚሔድ ነው። በማያቋርጥ ጥረት አትደራደር፤ ለአፍታም ትግልህን እንዳታቆም፤ ለደቂቃ ከአቋምህ እንዳትመለስ፤ በጀመርከው መንገድ ህልምህን መኖር፣ ለአለማህ መታገልህን ቀጥል።
https://telegram.me/counselingA