Get Mystery Box with random crypto!

ለዉብ ቀን            በህይወት ውስጥ፤ ያሰብነው ሁሉ እንደጠበቅነው እናገኘዋለን ማለት | Emir consult

ለዉብ ቀን

          
በህይወት ውስጥ፤ ያሰብነው ሁሉ እንደጠበቅነው እናገኘዋለን ማለት አይደለም፡፡
…….
ምንም ልንሆን እንችላለን፤ ክብር ሲገባን ተገፍተን ይሆናል፤ በተራም ተወስደን ይሆናል፤ እውነቱ የቱንም ያክል ከምናገኘው ምላሽ ባይገናኝ እንኳ ከእውነት በላይ ስሜት የሰውን ልጅ አጠቃላይ ውሳኔና ሂደት ስለሚገዛ ያሸንፋል፡፡›
ስሜታዊ በመሆን ህመም ሳለን የምንለውም የምንደጋግመውም ብርሃንኑን እውነታ ይጋርዳል፤ ሰዎች ለኛ ያላቸውን ትክክለኛ አክብሮትና ስሜት ከቶም ማየት የማንችል እንድንሆን ይወይፈናል፡፡ ይልቁንም፤ ተራና ውልንፊስ ለውጥ መፍጠር የማንችል ሆነን ሙሉ ስእል እንፈጥርባቸውም ይሆናል፡፡
መፍረድ ከባድ ነው፤ ለምን እንዲህ ይሆናል ማለትም ልክ አይሆንም፡፡ የስሜትን ገሞራ ኃይል ካሰብነው ሁላችንም ደግ በዋሉልን ላይ የመረርንባቸው ብዙ ጊዜያት ይኖራሉ፤ የሰዎችን ስሜት መንከባከብ የቻለ እርሱ ለጥበብ ታድሟል፡፡ ሁለንተናዊ ሆኗል፡፡ 
ስሜት ባጠላበት ግንኙነት ውስጥ ሙሉ ህይወታችንን አሳልፈን ብንሰጥ እንኳ ውጤታማ አንሆንም፤  የብዙዎቻችን መውደቅና መሸነፍ ገሃድ ነው ነገሩን ካስተዋልነው…፡፡ የግድ ከስሜት ውሽንፍር እስኪረጉ መጠበቅና ብራውን ንጋትና የጥሞና ጊዜ በትዕግስት መጠበቅ ከሚሻለው መግባባት ይሆናል፡፡ 
https://t.me/consult_emir