Get Mystery Box with random crypto!

የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ _ Commandos and Airborne Command

የቴሌግራም ቻናል አርማ commandoandairbornecommand — የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ _ Commandos and Airborne Command
የቴሌግራም ቻናል አርማ commandoandairbornecommand — የኮማንዶና አየር ወለድ ዕዝ _ Commandos and Airborne Command
የሰርጥ አድራሻ: @commandoandairbornecommand
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.60K
የሰርጥ መግለጫ

Addis abeba Ethiopia

Ratings & Reviews

2.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

2


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-04-20 07:42:34 ሐሙስ ማለዳ! ሚያዝያ 12/2015 ዓ.ም ዐበይት ዜናዎች

1፤ መከላከያ ሠራዊት ትናንት ዲሽቃ፣ ሞርታርና ሌሎች የቡድን ጦር መሳሪያዎችን ከሕወሃት መረከብ መጀመሩን ፋና ብሮድካስት ዘግቧል። የቡድን ጦር መሳሪያዎቹ ልዩ ስሙ ደንጎላት በተባለ ቦታ ላይ የተሰበሰቡ እንደኾኑ ዘገባው ጠቅሷል። የቡድን መሳሪያዎች ርክክብ እስከ ሚያዝያ 16 ይቀጥላል መባሉን ዘገባው ጠቅሷል። ሠራዊቱ በመጀመሪያው ዙር ከባድ የጦር መሳሪያዎችንና በሁለተኛው ዙር የአየር ኃይል መሳሪያዎችን ከሕወሃት ኃይሎች መረከቡ ይታወሳል።

2፤ የቡድን 7 አገራት ውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች የኢትዮጵያ መንግሥት ለሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት የጀመረው የሽግግር ፍትህ ሂደት እንዲጠናከር፣ ተጠያቂነት እንዲሠፍንና የሰብዓዊ መብት ጥሰት ተቆጣጣሪዎች በነጻነት እንዲንቀሳቀሱ ባወጡት መግለጫ አሳስበዋል። ውጭ ጉዳይ ሚንስትሮቹ፣ አፍሪካ ኅብረት በኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥትና በሕወሃት መካከል የሰላም ስምምነት እንዲደፈረም ያደረገውን አዎንታዊ ጥረት በመግለጫቸው አድንቀዋል። የቡድን-7 ውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች ይህን ያሉት፣ በጃፓን ሒሮሺማ ከተማ ባደረጉት ስብሰባ ላይ ባወጡት መግለጫ ነው።

3፤ የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ትግራይን እንዳይጎበኙ የኢትዮጵያ መንግሥት አግዷቸዋል ተብሎ ስለወጣው መረጃ ቃል አቀባያቸው ስቲፋኒ ዱጃሪች ትናንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተጠይቀው ነበር። ኾኖም ዱጃሪች ጥያቄውን በቀጥታ በመመለስ ፋንታ፣ ጉተሬዝ ወደ ኢትዮጵያ በሄዱበት ወቅት ወደ ትግራይ እንዳልሄዱ በወቅቱ ግልጽ አድርገናል በማለት መልሰዋል። ጉተሬዝ  ባለፈው የካቲት በአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ወደ ኢትዮጵያ በተጓዙበት ወቅት፣ ትግራይን እንዳይጎበኙ መንግሥት እንደከለከላቸው ዋሽንግተን ፖስት ከአሜሪካ መንግሥት ያፈተለኩ የስለላ መረጃዎችን ጠቅሶ ትናንት ዘግቦ ነበር።

4፤ የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ የሱዳኑ ግጭት ዓለማቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ሕግጋት የሚጣሱበት ደረጃ ላይ ደርሷል ሲሉ በማለት ተናግረዋል። ሩቶ፣ የሱዳን ጀኔራሎች ግጭቱ ከአገሪቱ ድንበር አልፎ የቀጠናው ስጋት እንዲኾን የሚያደርግ ኹኔታ ፈጥረዋል አስጠንቅቀዋል።.ካርቱም ውስጥ ሕዝብ በሚኖርባቸው መንደሮች ውጊያ እየተካሄደ መኾኑንና በውጭ ዲፕሎማቲክ አካላት ላይ የተፈጸሙ ጥቃቶችን ሩቶ በአስረጅነት ጠቅሰዋል። ሩቶ እና የጅቡቲውና የደቡብ ሱዳኑ አቻቸው ለግጭቱ ሰላማዊ መፍትሄ ለመፈለግ ትናንት ካርቱም ለመሄድ ይዘውት የነበረው ዕቅድ ሳይሳካ ቀርቷል።

5፤ የሱዳን ጦር ሠራዊትና ፈጥኖ ደራሽ ሠራዊት ለ24 ሰዓት ተኩስ አቁም ለማድረግ ትናንት ምሽት ላይ ለሁለተኛ ጊዜ በተናጥል የደረሱበት ስምምነት በድጋሚ እንደተጣሰ የውጭ ዜና ምንጮች ዘግበዋል። የ24 ሰዓታት ተኩስ አቁም ለማድረግ ቀድሞ ዝግጁነቱን የገለጠው ፈጥኖ ደራሽ ሠራዊት ሲሆን፣ ጦር ሠራዊቱም ዘግየት ብሎ ፍቃደኛነቱን አሳውቆ ነበር። #ሼር በማድረግ ተባበሩን


ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ

https://t.me/CommandoAndAirborneCommand

YouTube


172 viewsedited  04:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 22:44:18
#ሰበር_ዜና
https://www.youtube.com/@theredtigers_4034
201 views19:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ