Get Mystery Box with random crypto!

#BorisJhonson • ጠ/ሚ ቦሪስ ጆንሰን በገዛ ፍቃዳቸው የጠቅላይ ሚኒስትርነት ስልጣናቸውን | የኮማንዶና አየር ወለድ ኃይሎች የጦር ሜዳ ውሎዎች - Commando and Air Borne Battleships

#BorisJhonson

• ጠ/ሚ ቦሪስ ጆንሰን በገዛ ፍቃዳቸው የጠቅላይ ሚኒስትርነት ስልጣናቸውን ለቀቁ።

• አዲስ ጠ/ሚ እስኪሰየም ቦሪስ ጆንሰን ቦታው ላይ ይቆያሉ።

ከምክር ቤት እና ከካቢኔ ሚኒስትሮቻቸው ድጋፍ ማግኘት ያልቻሉት የብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስተር ቦሪስ ጆንሰን ከወግ አጥባቂ ፓርቲያቸው መሪነት እንዲሁም ከጠ/ሚ ስልጣናቸው ለቀቁ።

ለፓርቲው መሪነት የሚደረገው ፉክክር በቅርቡ የሚደረግ ሲሆን በቀጣይ ዓመት ጥቅምት ወር ላይ ደግሞ አዲስ ጠቅላይ ሚኒስተር ይሰየማል ተብሏል።

አስከዚያው ድረስ ግን ቦሪስ ጆንሰን በአገሪቱ የጠቅላይ ሚኒስትር መንበር ላይ ይቀጥላሉ።

ጆንሰን በአመራራቸው ላይ በርካታ ትችቶች ሲቀርብባቸው ቆይቶ በርካታ ባለሥልጣኖቻቸው በፈቃዳቸው ሥልጣናቸውን ከለቀቁ በኋላ ነው ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሱት።

ቻንስለር ናዲም ዛሃዊን ጨምሮ ከፍተኛ ካቢኔ አባሎቻቸው “ በክብር የሥልጣን መንበራቸውን እንዲለቁ ” ለጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ጥያቄ አቅርበው ነበር።

ቦሪስ ጆንሰን ሥልጣን እንዲለቁ የቀረበላቸውን ጥያቄ እስከ ሐሙስ ረፋድ ድረስ ሳይቀበሉት ቆይተው ነበር ፤ ነገር ግን የፓርላማ አባሎቻቸውን ድጋፍ ማግኘት ሳይችሉ በመቅረታቸው በመጨረሻ ወስነዋል።

ሚኒስትሮቻቸው በገዛ ፈቃዳቸው ስልጣን በመልቀቃቸው እና የሚያስፈልጋቸውን ድጋፍ ከፓርላማ አባላት ማግኘት ያልቻሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ከፓርቲ መሪነትና ከጠ/ሚ የስልጣን መንበራቸው በፍቃዳቸው መልቀቃቸውን በይፋዊ ጋዜጣዊ መግለጫ አሳውቀዋል።

ከወራት በኋላ የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ቦታ ያስረክባሉ።

#SkyNews #BBC
ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም፦ #ሼር #join
https://t.me/Commando_and_AirBorne_Battleship