Get Mystery Box with random crypto!

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ማብራሪያ ዋና ዋና ነጥቦች የኢትዮጵያ ፖለቲከኞ | የኮማንዶና አየር ወለድ ኃይሎች የጦር ሜዳ ውሎዎች - Commando and Air Borne Battleships

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ማብራሪያ ዋና ዋና ነጥቦች

የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች አክቲቪስቶች ግድያ ሲፈጸም አየሩን ይሞሉታል፤ ፖሊስ እርምጃ ሲወስድ ህጋዊ ነገር ሲከበር ግን የሉም፤

ሸኔ የኦሮሞ ቀንደኛ ጠላት ነው፤ ሸኔ ለማንም የማይመለሱ አውሬዎች ናቸው፤

ለምንድን ነው አውሬ የሆኑት የሚለው ጥናት ይፈልጋል፤ የፖለቲካ አላማ ግን የላቸውም፤

የሸኔ ዓላማው አገር ማፍረስ ነው፤

ሁለት ልጆችህን አገር ሊታደጉ ዘምተዋል ተብለው አባት በሸኔ ተገድለዋል፤

የመከላከያ ሰራዊት አመራሮች ቤተሰቦች ተገድለዋል፤ በመቶ የሚቆጠሩ አመራሮች ተገድለዋል፤

ሸኔ የኦሮሞ ተወካይ አይደለም፤ ቀንደኛ ጠላት ነው፤ በሸኔ ምክንያት ወለጋ ውስጥ ልማት ቆማል፤

ይሄንን ጠላት የሁላችንም ጠላት ነው ብለን ከተነሳን እናጠፋዋለን፤

ለሸኔ የሚራራ የሚያዝን የተለየ ስሜት የለንም፤ እንደ ሸኔ ያሉ ኃይሎች ዋና ፍላጎታቸው ፓርላማው ሚዲያው ዓለም ስለእነሱ እንዲያወራ ነው፤

ለእናንተ ባንናገርም በእያንዳንዱ ደቂቃ እየተዋጋናቸው ነው፤

ሁሉም ኢትዮጵያዊ በእኩልነት የሚኖሩባት ኢትዮጵያን ለመመስረት ነው ፍላጎታችን እየሰራን ያለነወም ለዚያ ነው፤

ጽንፈኞች በየትኛው ሰፈር ይደራጁ ሁለት መርዝ አላቸው፤ አንደኛው የእኔ ብቻ ጥሩ ነው የሚለው ነው፤ ሁለተኛው በጣም የበዛ የራስ ሀዘኔታ፤ የነገሮች ሁሉ ማዕከል ራስን ብቻ ማድረግ ነው፤

ጽንፈኝነት ዓለምን አልጠቀመም ኢትዮጵያን አይጠቅምም፤ መግረፍና ማፈን ከብልጽግና ጋር አብሮ አይሄድም፤
ለጠላት ተገማች አንሁን፤
ተጨማሪ ይዘን እንመለሳለን

ቤተሰብ ይሁኑ!
ቴሌግራም፦ #ሼር #join
https://t.me/Commando_and_AirBorne_Battleship