ኢየሱስ ማነው? የኢየሱስን ማንነት የሚመለከት ጥያቄ እያንዳንዱን ድርጊቱን ተከትሎ ይከሰት ነበር። ፈውሱን (ሉቃ. 5፥21፤ ዮሐ 5፥12)፣ በተፈጥሮ ላይ ያለውን የበላይነት (ማር 4፥41)፣ የኀጢአት ይቅርታ መስጠቱን (ማር 2፥7፤ ሉቃ 7፥49) የተመለከቱ ሁሉ “ይህ ሰው ማነው?” በማለት ጠይቀዋል። ደቀ መዛሙርቱ (ማር 4፥41)፣ በሥልጣኑ ላይ ጥያቄ ያነሡቱ (ማር 11፥28፤ ዮሐ 8፥25)፣ ሄሮድስ (ሉቃ 9፥9)፣ ሊቀ ካህናቱ (ማር 15፥2)፣ ... ይህንኑ ጥያቄ አንሥተዋል። ኢየሱስም “ሰዎች እኔን ማን ይላሉ?” ሲል ጠይቆ ነበር (ማር 8፥27)። ታዲያ ኢየሱስ ማነው? ... ለመሆኑ እርስዎስ የፊታችን እሁድ በሚካሄደው “የእግዚአብሔር ልጅ” መጽሐፍ ምረቃ ላይ አይገኙም? ... ሁላችንም ተጋብዛችኋል! እሁድ 9:00 ሰዓት በየተቀባ የእግዚአብሔር ቃል ቤተክርስቲያን እንገናኝ --- @nazrawi_tube 853 views18:56