Get Mystery Box with random crypto!

የበኩር ጥበብ 🗞

የቴሌግራም ቻናል አርማ christian_poem1 — የበኩር ጥበብ 🗞
የቴሌግራም ቻናል አርማ christian_poem1 — የበኩር ጥበብ 🗞
የሰርጥ አድራሻ: @christian_poem1
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 494
የሰርጥ መግለጫ

ይህ መንፈሳዊ የቴሌግራም አጋር channel ነው።
👉 @yebirihan_lijoch
መዝሙር ለማግኘት 👉 @Kabata_bot
https://youtube.com/channel/UCtp5XBjV0p6Mw0BX1Nmu81w
🌍 LOCATION 👉 ADOLA WOYU

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-03-24 22:00:12 መሪር
.......ክፍል 38......
ፀሀፊት አክሳን አዳነ



.........በይ የሆነ ነገር አለ ትፊያት አለኝ ። አንተ ያምሀል እንዴ ምን እያወራህ ነው ?
ሰው አይደለው እንዴ ፊልም አለ የጓደኞቼ ህይወት አለ ስንት ነገር አለ ።
ከሆነ ጥሩ ነው የዋሸሽኝ ነገር ካለ ግን ይቅር አልልሽም አለኝ ሆሆሆሆ ምን እያስቀባጠረህ ነው በል በል ደህና እደር ብዬው ወደ ታክሲ ገባሁ ።
ቀናቶች እየገፉ ግዜአት እየነጎዱ ነው ።
ኬቢ በጭራሽ ሊሰማኝ ፈቃደኛ አይደለም በጊዜአቸው መካከል ጣልቃ መግባት አልፈልግም ኬቢ ደግሞ እንደ እህቱ ስለሚያየኝ እሷ ፊት የሚያሳየው ሁኔታ ደስ አይልም ያው ሰው አይደለች እየደበራት ነው መሠለኝ ሰሞኑን ለእኔ ፊቷ ልክ አይደለም የፈራሁት ደረሰ በእኔ ምክኒያት ከሚከፋት እንደፍጥርጥሬ ስከፋ ብኖር ይሻለኝ ነበር ።
ፈተናም ጨርሰን አመቱም አልቆ ክረምቱን በድብርት እያሳለፍኩ ነው ።
ዛሬ ቀኑ ቅዳሜ ነበር በሬ በሀይል ተንኳኳ ማነው እያልኩ ስልኬን ሳይ 12:7ይላል አይኔን እያሻሸው ከአልጋዬ ወረድኩ ና ከፈትኩ ምሳሌ ነበረች ። አየሩ ቅዝቃዜ ነው ካፊያም አለ ስቅጥጥ አለኝ ወፍራም ኮፊያ ያለው ጃኬት ለብሳ ግንባሯን ቋጥራ እጇን ኪሷ ከታ ቆማለች ምነው ሚስ በማለዳ ሰላም አይደለም አልኳት ፈገግ አለች የፌዝ ሳቅ ኸረ ሞልቷል ሁሉ ሰላም ብቻ አደል አለችኝ ግቢ ብዬ የያዝኩትን በር ለቀኩት ገብታ ተቀመጠች ጃኬት ደርቤ ፊቴን ታጠብኩና ፊት ለፊቷ ተቀመጥኩ ትሰሚኛለሽ ሰላም እኔ ታሳዝኚኛለሽ ቤተሰብ ስለሌለሽ እንደ ቤተሰብ ነው የማቀርብሽ ውስጤ ተረበሸ ሁሉም ሰው ለመልካምሸ ለክፉም ሁሌ ብቸኝነቴን ያበስረኛል ። ቀጠለች አንቺ ግን በምላሹ ክፉ ነገር እየፈፀምሽብኝ ነው ።
ምን አደረኩ አልኳት ምን አደረኩ እያላገጥሽ ነው ከዚህ በላይ ምን ታረጊኝ ከውጪ ለሚያይ ሰው ኬብሮን የአንቺ ፍቅረኛ እንጂ የኔ አይመስልም ምናቹም አላማረኝም ። ታናሽ እህቴ ምናምን እያለ ከእኔ በላይ ለአንቺ ነው ጊዜ ያለው ሁኔታቹ የእህትና ወንድም አይመስል ደግሞስ በእናት ነው በአባት እህትና ወንድምነታችሁ በኬብሮን የሚመጣብኝ ሰው ጠላቴ ነው ጠላቴ አቀርቅሬ ከመስማት በቀር በምን አንደበቴ ምን ልናገር ሚስ በጣም ይቅርታ ለማስተካከል እሞክራለሁ አልኳት እሞክራለሁ በስነስርዓት ያወራሁሽ ኬቢ ለአንቺ ያለውን ቦታ ስለማውቅ ነው ።
እሱን በአንቺ ጉዳይ ልናገረው አልፈልግም አንቺ ግነ እንድትርቂው ነው ምፈልገው ተናግራኝ ወጣች እሷ እኮ ልክ ናት እውነት አላት በጣም ከፋኝ ።


@yebirihan_lijoch


ኸረ ጌታሆይ እሺ ምን ላድርግ ከእነዚህ ሰዎች ህይወት እንዴት ልውጣ ።
ሚስም እሱን ለማስቀናት ከሌሎች ጓደኞቿ ጋር ፎቶ ፖስት ታደርጋለች እሱ እንዲናደድ ከብዙ ወንዶች ጓደኞቿ ጋር ትሄዳለች ሱቅ ስንሄድ አብራቸው ናት ይሄ ሁሉ የእኔ ጦስ አይደል ምርርር አለኝ እንድርቀው ስታስጠነቅቀኝ እሱ ይበልጥ ይቀርበኛል ሁለቱም ያሳዝኑኛል ለእኔስ ማን ባዘነልኝ ።
ዛሬ በጠዋቱ ልብስ እያጠብኩ ኬቢ ደወለልኝ እንዴት ነህ ኬቢ አልኩት ደህና አይደለሁም የት ነሽ አለኝ እቤት ነኝ ምነው ምን ሆንክ አልኩት እሱን ስንገናኝ እቤት መጣሁ ሲለኝ አይ አይ አትምጣ እኔ ያለህበት መጣለሁ አልኩት ግራ ገባው መሠለኝ እ..ሺ እንደፈለግሽ ብሎ ስልኩን ዘጋሁት ደግሞ እዚ እያለ ሚስ ብትመጣና ቢጣሉስ ብዬ ፈራሁ ። የጨረስኩትን አሰጣሁና ትንሽ ነበር የቀረኝ እሱን መልሼ ልብሴን ቀያይሬ ወጣሁ ። ጊቢአቸውን አንኳክቼ ስገባ እንደ ልማዱ አበቦቹን ውሃ እያጠጣ ነው አንተ ልጅ እኮ ግብርና ያዋጣሀል ብዬ ፈገግ አልኩ ፊቱን ክስክስ አድርጎት ነው ብለሽ ነው አለኝ ። እስከዛሬ የደነገጥኳቸው ድንጋጤዎች ቢደመሩ የአሁኑን አይደርሱም እሱ ደግሞ ምን ሰምቶ ነው አልኩ ለራሴ ። ልቤ እየመታ ምን ሆነሀል አልኩት ከህይወቴ ውጪልኝ ብሎ የሚያመናጭቀኝ ምናምን እየመሠለኝ ነው እንዲ ፊቱን በይሮብኝ አያውቅም ። የኔ ልጅ መተሻል እንዴ የእናቱ ድምፅ ነበር በረንዳው ላይ ቆመው ውይ እማ ገና መምጣቴ ነው አልኩና ተጠግቼ ሰላም አልኳት ግቡአ ቤት በቅቤ የታሸ ቆሎ በሳህን ይዛለች አይ እዚው እንሆናለን አልኩ ከሆነ ጥሩ ይሄን ቆሎ ላቀብለው ነበር በሉ አብራቹ ብሎ አለችኝ እሺ እማ በፈገግታ ተቀበልኳት ገባች ኡፍፍፍፍ ቁና ተነፈስኩ ምን ሊለኝ ይሆን ብዬ ተመልሼ አጠገቡ ሄድኩና ቆምኩ ሳህኑን አጠገቡ ያለው ወንበር ላይ አስቀመጥኩት ።
ልጁ ተቀመጪ እንኳን አይለኝም ምን ሆኗል ምን ብዬ ደግሜ ልጠይቀው በዝምታ አቀርቅሬ ጣቶቼን እያጠላለፍኩ በሀሳብ ሄድኩ እሱም አበቦቹን እያጠጣ ነው ። እኔ የምልሽ ከሄድኩበት መለሰኝ ምን አልከኝ ተደነባበርኩ አተነፋፈሴ ተራራ በሩጫ የወጣ ሰው ይመስላል ። አተኩሮ አየኝና የውሀውን ትቦ አስቀመጠው ዘበኛውን ውሀውን እንዲዘጋ ነገረው እጁን እያራገፈ የቆሎውን ሰሀን አንስቶ ወንበሩን ሰጠኝ ምን ሆነሻል አለኝ ማ ምን ሆንኩ አልኩት እራሴን ለማረጋጋት እየሞከርኩ ሰው ምን ሆኗል ደህና ነሽ ግን አዎ ምን ሆንኩ ከእኔም ብሶ ተኮሳተርኩ ።
ከሆነ ጥሩ ነው ግን ልምጣ ስልሽ ለምን ሳታስጨርሺኝ አይ አይ ብለሽ ቀወጥሽው አለኝ ኸረ ምንም ዝም ብዬ ነው ደግሞ ለማፀዳዳት ብዬ ተንኳቷል ለዚያ ነው አልኩት ከሆነ ጥሩ እኔ እኮ ሁሉም ሰው በአንዴ ሚቀየርብኝ ምን አጥፍቼ ነው ብዬ ነው ከፍቶኝ ልነግርሽ ብደውል አስደነገጥሽኝ አሁንም ግን ምክኒያትሽ አልተዋጠልኝም አለኝ ኡፍፍፍፍፍፍፍፍ ትንሽ ተረጋጋው የተኮሳተረብኝ አትምጣ ብዬ ስላልኩት መሆኑ ነው እሺ ምንድነው ያስከፋህ አልኩት .........




.............ይቀጥላል.............

@yebirihan_lijoch
@yebirihan_lijoch

written by Aksan Adane
ፀሀፊት አክሳን አዳነ
308 views19:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-24 20:50:08 https://youtube.com/channel/UCtp5XBjV0p6Mw0BX1Nmu81w


#Subscribe ያላደረጋችሁ አሁን አርጉት
201 views17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-23 20:38:35 መሪር
.......ክፍል 37........
ፀሀፊት አክሳን አዳነ


......የምሳሌ ስልክ ነበር ጌታ ሆይ ገላቲያ ነገረቻት እንዴ ብዬ ደነገጥኩ ።
ሄለው ሚስ አልኩ ልቤ እየመታ
አንቺ ዛሬውኑ ትጠፊያለሽ አለችኝ
አልጠፋውም ኸረ አልኩ እያዛጋሁ ና አይኔን እያሻሸው አንቺ ጉደኛ ተኝተሻል እንዴ ሰአቱን አይተሽዋል? አለችኝ
የግድግዳ ሰአቴን አየሁን 2:41 ይላል አዎ እውነትም በጣም ሄዷል ሰአት ይኸው ልነሳ ነው አልኩ ።
ሰነፍ የሆንሽ አትመጪም አለችኝ 4ሰአት ላይ ክላስ አለኝ ስወጣ መጣለሁ አልኳት
ተነስቼ ተንበረከኩና ትንሽ ፀልዬ ተነሳሁ አልጋዬን አነጠፍኩ ፊቴን ታጠብኩ ቁርስ ሰሪራርቼ በላሁ ቤቴን አፀዳድቼ ሰአቱም ሄደ ልብስ ቀያይሬ ወደ ክላስ ሄድኩ እነ ረጁንም አግኝቻቸው ቡና ጋብዘውኝ ልሄድ ነው አልኳቸው ረጁ የት ጣውንትሽ ጋር ብላ ሳቀች ትቀልጂያለሻ ያልደረሰበት አልኩኝ ውይ ይቅርታ ሰሉ ። በቃ ሂጂ ደግሞ ጣል ጣል አታድርጊን እየደወልሽ አለችኝ ። እኔ የምልሽ አለች ብሌን ነበረች አብረው ስታያቸው ከሚከፋሽ ምክኒያት እየፈጠርሽ ከስራቸው ብትርቂ አለችኝ
እህ ይናፍቀኛላ አልኳት ፊቴ አሳዘናት መሠለኝ እውይ የኔ ውድ በጣም ይቅርታ በናችሽ አታኩርፊ ግን ደግሞ የራሳቸው ጊዜ ያስፈልጋቸዋል በየሄዱበት እንደ ጥላ ከሄድሽ እሱ ምንም ላይመስለው ይችላል እሷ ግን ትጠረጥራለች በናትሽ ተጠንቀቂ አለችኝ ።
እሺ የኔ ውድ አመሠግናለሁ በጣም አልኳት ላይብረሪም ገብተን ትንሽ ወክ አድርገን ሊመሽ አከባቢ ተሰናብቼአቸው ሄድኩ ።

@yebirihan_lijoch

በታክሲ እየሄድኩ ጌታ ሆይ የእነዚህ ሰዎች ህይወት በእኔ ምክኒያት አይበጥበጥ አደራህን የገላቲያን አንደበት ጠብቅልኝ አልኩ ወይ ዲያሪዬን መልሺልኝ ብዬ ልለምናት ይሆን ብዬም አስባለሁ ቤታቸው ደረስኩ የሚስ ወንድሞችም አሉ በረንዳ ላይ ተቀምጠዋል ሠላም አልኳቸው ና ተቀመጥኩ ምሳሌ አንቺ ከጠዋቱ 2 ሰአት ስጠብቅሽ 11 ሰአት ትመጪአለሽ አለችኝ ይቅርታ ሚስ አሳይመንት በዝቶብኝ ነው አልኩ በውስጤ ኸረ ሠላም ያፈጠጠ ውሸት ይደብራል አልኩ ለራሴ ኬቢ እነማሚን አታናግሪም ገብተሽ አለኝ ወይኔ ረሳሁት ብዬ ገባሁ ና ሰላም አልኳቸው ።
ተመልሼ ወደ ውጪ ወጣቶቹን ለመቀላቀል ወጣሁ ትንሿ ሰላም ትምህርት እንዴት ነው? የምሳሌ ወንድም ነበር ጥሩ ነው ከዚያ ነው ምመጣሁ አልኩት ደስ ይላል በርቺ አለኝ ።
አንቺ የማታውን አልረሳሁልሽም ከማን ጋር ስታወሪ ነበር ኬቢ ነው በሹክሹክታ ድምፅ አንተ ያምሀል እንዴ እነ ብሌን ናቸው ሌላ ከማን ጋር አወራሁ አልኩት አአ አይመስለኝም አላምንሽም አለኝ እንዴ አንተ አመረርክ እንዴ እኔ እኮ ማታ ቀልድ መስሎኛል ደግሞ ባወራስ መብቴ አደል አልኩት እኮ እኔ ምን አልኩ እመኚ አለኝ እህህህ ኬቢ ሳላውቀው ጮኹኩ መሠለኝ ሁሉም የየራሱን ወሬ ትቶ አፈጠጠብኝ ይቅርታ በጣም አልኩኝ ገላቲያና ሚስ መሳጭ ወሬ ላይ ናቸው ከአሁን ከአሁን ነገረቻት ብዬ ልቤ በአፌ ልትወጣ ። ኬቢ ደግሞ እንደ እህቱ ስለሚያየኝ ይሁን እንደበፊቱ ይቀልዳል ይመታኛል ጆሮዬን ይቆነጥጠኛል ምሳሌ ፊትለፊታችን ነች እኔ ተሳቅቄ ሞትኩ ምን ያለበት ዝላይ አይችልም አለ የሀገሬ ሰው ። በተለይ ገላቲያን ማየት እጅግ ተሳቀኩ
ምሳሌም ሁኔታችን አሰጋት መሰለኝ ደጋግማ ታየናለች በምን ቋንቋ ልንገረው ወንድሞቿ ባሉበት ይሄ ልጅ ጥርሱን እንዳያረግፉለት አልኩና ብቻዬን ፈገግ አልኩ በመጨረሻም አበድሽልኝ አለኝ አዎ እድሜ ለአንተ ቆየው እኮ አልኩት ።
ይብራራልኝ ሲለኝ ሰው ውሎዉን አደል ሚመስለው ልክ እንደ አንተ ብዬ አስቀየስኩ ። ደግሞ እየመሸ ነው ልሂድ ቤት ማደር አልፈልግም ዶርም መሄድ አለብኝ አልኩት ለምን ቤት አይሻልም አለኝ ለብቻዬ ይጨንቃል ገሊም ክዳኛለች አልኩት ነይ ሁለታቹንም ላድርሳቹ አለኝ አንተ ሰውዬ አሁን ገና አበድክ ምሳሌስ አልኩት ምን ትሆናለች ደግሞ እኔ እመለስ የለ አለኝ አሀሀሀ ገባኝ ሂዱልን ነው ገላቲያም ምቀኛ ሆናብሀለች አልኩት አንቺ ጌታ ይቅር ይበልሽ አታነካኪኝ ሆሆሆሆ እንደውም አብዛኛውን ጊዜ ከገሊ ጋር እንዲሆኑ ነው የምፈልገው ለብቻዋን ብፈልጋት እንኳን ሰዎች በሚበዙበት ስፍራ ነው ።
ሚስቴ እስክትሆን አለኝ ልክ ኖት ጋሼ እኔ ልሂድበት ከነ ረጁ ብሌን ጋር ማሳለፍ ፈልጌ ነው ። ብዬ ተነሳሁ ገና ሳትመጪ ልትሄጂ ነው አለችኝ ሚስ ነገ መጣለሁ ሚስ ሁሉንም ተሰናበትኩ ። ኬቢ ቻው ብዬ ልጨብጠው ስል ቆይ ልሸኝሽ አለኝ አይ ገሊ ትሸኛች ሚስ ነበረች ልቤ ተሰነጠቀ አዎ አልኩኝ ወዲያው እሱ ግን ለምን ይኸው እስከዚች እስከ ታክሲ ቦታ ብሎ በድርቅና መጣ ወይኔ ኬቢ ምን እያደረክ ነው ሚስ ይደብራታል እኮ አልኩት ለምን ታናሽ እህቴን እኔ ካልተቆጣጠርኳት ማን ሊቆጣጠራት ነው አለኝ አደል አልቀረብህም እኔ እኮ አልቀለድኩም አልኩት ባለፈው ቃል ገብቼልሻለው ሚስ ብትመጣም ብቸኝነት እንዲሰማሽ አላደርግም ብዬ እና እኔ ብቸኝነት ተሰማኝ አልኩህ እሷን እያስከፋህ እኔን ማስደሰትህ ነው እንደውም ሌላ ጭንቀት ጨመርክብኝ ኸረ አንቺ ልጅ ሁሉንም ነገር ታከብጂዋለሽ ምን ያስከፋታል ቀን ሙሉ አጠገቧ ስጎለት አልዋልኩም አለኝ ሴት ሆነህ እየው ልበልህ አልኩት አንቺ ልጅ ግን ስለ ቅናት ምናምን የት ነው ምታውቂው ነው የደበቅሽኝ ነገር አለ አለኝ አረማመዱን ገታ አድርጎ በፈገግታ ማ እኔ የት ምን ደብቅሀለው አትቀባጥር አልኩ ኸረ መንተባተብ ተላቀቅናታ ዛሬ በይ የሆነ ነገር አለ ትፊያት አለኝ .....



..........ይቀጥላል ..........

@yebirihan_lijoch
@yebirihan_lijoch

written by Aksan Adane
ፀሀፊት አክሳን አዳነ
201 views17:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-23 20:38:35 መሪር
..........ክፍል36......
ፀሀፊት አክሳን አዳነ


.........አለችኝ ወደ ሳሎን ሄድን ሰው ሁሉ በወሬ ተጠምዷል እነ ምሳሌ ገብተዋል ተብሎ ኬቢ እንኳን ደስ አለህ ደስታህ ደስታዬ ነው አልኩት ። ሙሽራ መስለሻል ምንድነው ነገሩ አለኝ የአንተና የገሊ ስራ ነዋ አንተም አምሮብሀል እኮ አልኩት። ተይ ተይ የአንቺ እዚህ ካለነው ሁሉ ይለያል ነይ እስቲ ውጪ ፎቶ ላንሳሽ አለኝ
ኸረ ኬቢ ስታሽቃብጥ እኮ ማንም አይደርስህም አልኩት ጌታን ከልቤ ነው ነይ ብሎኝ ካሜራውን ይዞ ወጣ ተከትዬው አንተ ልጅ ያምሀል እንግዶቹ ገብተዋል እየተባለ የምን ፎቶ ነው ። ና በል እንግባ አልኩት አርፈሽ ተነሺ ካልሆነ እየለፈለፍሽም አነሳሻለው አለኝ እኔ አልነሳም ብዬው ፊቴን መልሼ ቆምኩ የሚተው ነበር የመሰለኝ ሳየው እያነሳ ነው ኸረ ኬቢ ተው ብለምነው ብለምነው አልሰማ አለኝ ካሜራውን ተቀበልኩት
ፐፐፐ ድንገተኛ ፎቶ እንዲህ ያማረብሽ በስርአት ብትነሺሽ አለኝ ሳያቸው የምርም ያምራሉ ዋው እውነትም ወቶልኛል አልኩት ሲያምርሽ ይቀራል ካሜራ ማኑ እኔ ስለሆንኩ ነው አለኝ ጉረኛ እኔ ምልህ ቆይ አታፍርም ፍቅረኛህ እየመጣች እዚህ ስትጎለት እንዴት ሄደህ አትቀበላትም አልኩት ።
ወንድሞቿ አሉ እናት አባቷ አሉ አንድ እህቷም አለች እዚህ የነበረው ወንድሟ ሊቀበላቸው ሄዷል የምን ጋጋታ ነው ስታሽቃብጥ ሚደርስህ የለም ላልሽው ይሄ በቂ መልስ ነው ። ይሄኔ እያሽቃበጥኩ ነበር አገኘሁሽ አለኝ ።
የመልስ ምት መሆኑ ነው ይሄ ማሽቃበጥ አይደለም እኔ እሷን ብሆን አላናግርህም ነበር አልኩት ወደሽ ነው ያውም በናፍቆት ነበር ምታናግሪኝ አለኝ አይገርምህም አላደርገውም አልኩት እስቲ ሙት በይኝ ብሎ እጁን ዘረጋልኝ ኸረ ጠላትህ ይሙት ምንድነው ምታወራው ሳላውቀው ኮርተር አልኩ ከት ብሎ ስቆ አየሽ የማትችዪውን አታውሪ ለነገሩ እኔም አንቺ ብትሆኚ እዚህ አልቀመጥም ነበር አለኝ ልቤ ደነገጠ ማለት አልኩት እሷ አጃቢዎቿ ብዙ ናቸዋ ቆይ ምን እያወራን ነው አለኝ?
ለኔም ግራ ገባኝ ከልቤ አሳቀኝ አንተ ነሀ የቀበጣጠርከው አልኩት አንቺ ነሽ አንተ ነህ እራስሽ ነሽ እራስህ ነህ ስንጨቃጨቅ የመኪና ከክላስ ተሰማ መጡ መሠለኝ አለ ዘበኛው በሩን ከፈተ እቤት የተቀመጠው ሰው በሙሉ ተንደርድሮ ወጣ ። መኪኖቹም ወደ ጊቢ ገቡ ሁሉም የናፍቆት ሰላምታ ሲለዋወጡ ግራ የገባኝ እኔ ደርቄ ቀረው

ወደ ውስጥ ገቡ እኛ ሴቶቹ ወደ መስተንግዶ ገባን ደስ የሚል የቤተሰብ ጊዜ በእውነት ያስቀናሉ ።
የኬቢን ደስታ አይቼ በጣም ደስ አለኝ ።
የሚስ ወንድሞች አንደኛው ወንድሟ ቤት ነው የሚያድሩት ዮቶር ይባላል ሌሎቹ እዚሁ ።
እኔ ደግሞ ቀሪዎቹን ተሰናብቼ ። የሚስ ወንድሞች
እግረ መንገዳቸውን እቤቴ ሊያደርሱኝ ወጣን ሶስቱ ከኋላ ተቀምጠዋል ዮቶር ገቢና ነው ። ብቻሽን ነው እንዴ የምትኖሪው አለኝ አዎ ተከራይቼ አልኩት ተገርሞ በዚህ እድሜ እንዴት ቤተሰቦችሽስ አለኝ እሱ ታሪኩ ብዙ ነው።
የተወለድኩት አዲስአበባ ነው እዛም እቤት አለን አሁን እዚህ ዩኒቨርሲቲ እየተማርኩ ነው አልኹት ። እንደሱ ነው ደስ ይላል ቤተሰቦችሽ በጣም ያስቡልሻል ማለት ነው ቤት ተከራይተው ሚያስተምሩሽ አለኝ ። በጣም ኸረ አልኩ በውስጤ ። በሩ ላይ አውርደውኝ ሄዱ በሩን ከፍቼ ገባሁ ስልኬን ከስፒከር ጋር connecte አደረኩት የእንዳለን መዝሙር ሚስጥሬን ለአንተ ነው የምነግርህ....... የሚለውን ዝማሬ በትንሹ ከፍቼ መፅሀፍ ቅዱስ ማንበብ ጀመርኩ ትንሽ እንደቆየ ስልኬ ጠራ እነ ረጀብ ነበሩ የቀኑን ውሎዬን ጠይቀውኝ በየተራ አዋርቼአቸው ዘጋሁት ና ወደ ንባቤ እንደተመለስኩ በድጋሚ ስለኬ ጠራ ኸረ ዲያቢሎስ ስራህ ይፍረስ እያልኩ ሳየው ኬቢ ነው ። ፈገግ አልኩ አጠገቤ ሆኖ ቢሰማ እኔ ነኝ ዲያቢሎስ ብሎ ይገለኝ ነበር ። አንቺ ጉደኛ ይሄ ሁሉ ሰአት ከማን ጋር ነው ምታወሪው መስመሩ ተይዟል የሚለኝ አለኝ ከት ብዬ ሳኩ እኔ ምንም አታውቅም ብዬ ዩኒቨርሲቲ ብልክሽ ተበላሸሽ ማለት ነው በይ ንገሪኝ አሊያም ነገ ጠዋት በጠረጴዛ ዙሪያ እናወራለን ። ኸረ ኬቢ አታስቀኝ እንደ እብድ አልኩት ድሮስ እብድ አይደለሽ ለማንኛውም በሰላም ገባሽ አለኝ አዎ አባባ በሰላም ገብቻለሁ አልኩት በይ ፀልየሽ በጊዜ ተኚ ስልክ ሚባል ነገር እጅሽ ላይ እንዳይገኝ እኔ ስቃለው ኸ አባት ብሆን አላስኬድም አለኝ አይ አያት በሚለው ይስተካከል ጋሽ ኬብሮን አሁን ምን ከመሠለ ንባብ ነው የበጠበጥከኝ ቅዱሱን ቃል ላንብበት አልኩት ። በተራው ከት ብሎ ስቆ ተይ እንጂ ስልክሽ መስመሩ የተያዘው ከመላዕክት ጋር ስታወሪበት ነበር ማለት ነው አለኝ በለው ሰውዬ እንዳታስቀስፈኝ ብለህ ብለህ ከመላዕክት ጋር ልታነካካኝ በል በል ደህና እደር እንግዳ አለብህ እኮ አልኩት አሀ ሰልችቼሻለው ማለት ነው በግልፅ አትናገሪም እሺ ደህና እደሪ ግን ምንም ማለት አይደለም ኸረ እንተ ሰው ተው ተው ለነገሩ ተረድተኸኛል አመሠግናለሁ አልኩት ጥርስሽ ይርገፍ አትሳቂ የረሳሁ እንዳይመስልሽ ጠዋት እናወራለን አለኝ እሺ ቻው ደህና እደር ብዬው ስልኩ ተዘጋ ። ሆሆሆሆ ልጁ አበደ እንዴ ብቻዬን ፈገግ አልኩ ና ሀሳቤን ሰብስቤ ወደ ንባቤ ገባሁ ደስ የሚል ምሽት ከጌታዬ ጋር አሳልፌ ፀሎቴን አሳርጌ ተኛሁ ።
ከእንቅልፌ የቀሰቀሰኝ የምሳሌ ስልክ ነበር...........



...............ይቀጥላል............

@yebirihan_lijoch
@yebirihan_lijoch

written by Aksan Adane
ፀሀፊት አክሳን አዳነ
186 views17:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-22 22:28:42 መሪር
.........ክፍል 35..........
ፀሀፊት አክሳን አዳነ



............ማኪያቶውን እያማሰለ እንዳቀረቀረ ትኩር ብዬ እያየሁት ከነገ በኋላ አላስፈልግህማ አልኩት እንባ እየተናነቀኝ ካቀረቀረበት በቅፅበት ቀና ብሎ አፈጠጠብኝ ምን ማለት ነው ይሄ ደግሞ ለመደበሪያነት ነበር ምትፈልገኝ ማለት ፈልገሽ ነው? የእሷ የፍቅር አጋርነት ሌላ የአንቺ እህትነት ሌላ ኸረ ሰሉ እንደ በፊቷ ሰላም ሁኚልኝ ግራ እያጋባሽኝ እኮ ነው ። በውስጤ አታደርጊውም ሰላም ዋጥ አድርጊው እያልኩ እራሴኑ እቆጣ ጀመር የተናነቀኝን እምባ በግድ ዋጥ አደረኩት ። ፊት ለፊቴ ከተቀመጠበት ወንበር ተነስቶ አጠገቤ ተቀመጠ ደነገጥኩ ሰሉ ፊትሽ ልክ አይደለም ምሳሌ ስትመጣ የምርቅሽ መስሎሽ ከሆነ በእናቴ እምልልሻለው አላደርገውም አለኝ ። አጠገብሽ ሌላ ወንድሞች እህቶች የራሴ የምትይው ሰው እንደሌለሽ እያወኩ ሳትሄድ በፊትም ጣል ጣል ስላደረኩሽ በጣም ይቅርታ ።
እንደ ህፃን በለቅሶ ቀወጥኩት እንዴ ሰሉ በእናትሽ አታስጨንቂኝ የዚህን ያክል በእኔ ተከፍተሻል አቅፎ ያባብለኝ ጀመር ብሶቴ ገንፍሎ ትዕግስቴን ደረማምሶ በለቅሶ ወጣ ። ልክ በሞት የሚለየኝ ይመስል አዘንኩ እራሴን ለማረጋጋት ሞከርኩ እምባዬን እየጠራረኩ ቀና ብዬ ሳየው ፊቱ በሀዘን ኩርምት ብሎአል የቅድሙ ደስታው የለም ይበልጥ አዘንኩ ኬቢ ደስታህን ወደ ሀዘን ስለቀየርኩት በጣም ይቅርታ ለራሴም ለሰውም ደስታ መፍጠር የማልችል ለደስታና ለሰላም ፀር የሆንኩ ነኝ ቤተሰቦቼ ሰላም ብለው የሰየሙኝ በተቃራኒዉ ሳይሆን አይቀርም። በቃ ወደ ጊቢ መመለስ አለብኝ አንተም በጊዜ ወደ ቤት ግባ አየሩ ይከብዳል እና ደግሞ ዝናቡም እየመጣ ነው አልኩት ። ግራ በመጋባት አተኩሮ እያየኝ በቃ በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ነው ትቼሽ ምሄደው? ምንድነው ሚሰማሽ ለምን አትነግሪኝም በእውነት እምልልሻለው ብቸኝነት እንዲሰማሽ አላደርግም ደግሞ ገሊም አለች ቆይ ምን አስበሽ ነው አለኝ በንዴት እውነቱን አፍርጪው አፍርጪው ይለኛል ።
ትንሽ ከቆየን ይሄ ልጅ ብዙ ያናግረኛል ደግሞ ምሳሌ በምትመጣበት ማግስት ህይወቱን ልበጥብጥ ደስታውን እየበጠበጥኩ ደግሞ ምኑን እንድወጣ አላደርገውም ሀሳቤን ሰብስቤ ።
ኬቢዬ ያው ታላቅ ወንድሜ ከዚያ አስቀያሚ ህይወት መልካም መንገድ የሆንከኝ አሁንም አጠገቤ ያለህ ብቸኛ ወንድሜ አንተው ስለሆንክ ነው ቶሎ የሚከፋኝ ይቅርታ በጣም ደግሞ ሚስም በጣም የምታስብልኝ እህቴ ናት ነገ በአዲስ መንፈስ እንቀበላታለን ስላስጨነኩህ ይቅርታ አልኩት እና ፈገግ አልኩ ኡፍፍፍፍፍ ቁና ተነፈሰ ሰሉ ሁለተኛ እንደዚህ አዝነሽ ማየት አልፈልግም ፈገግታ ነው የሚያምርብሽ ጭራሽ በእኔ ምክኒያት ሲሆን ደግሞ እጅግ ይከፋኛል ። ተነሽ ተነሽ አሁን ወደ ቤት እንሂድና በመኪና እሸኝሻለው አለኝ መንገድ አታርዝም እኔ በታክሲ እሄዳለው አንተ በጊዜ ግባ ብዬው ትንሽ ተነታረክን በመጨረሻም በሀሳቤ ተስማምቶ ተሰናብቶኝ ሄደ ።


@yebirihan_lijoch


ወደ ዶርም ስገባ ብሌንና ረጀብ አሉ እንዴት ዋላችሁ ብዬ አልጋው ላይ ግርግዳውን ተደግፌ ተቀመጥኩ ወደ ጣሪያው አንጋጥጬ የማስበውን እንኳን በቅጡ ማወቅ ተሳነኝ ረጀብ ሁኔታዬን አይታ መሠለኝ ሠሉ ምን ሆነሻል ፊትሽ ልክ አደለም አለችኝ ። ብሌንም ስልኳን ትታ እንዴ ጭራስ አልቅሰሻል እንዴ ምነው አሉኝ ስለራሴ የነገርኳቸው በህመም ምክኒያት ትምህርት አቋርጬ እንደገና እንደጀመርኩ ነው ።
አብዝተው የሆንኩትን ጠየቁኝ ። በረጅሙ ተንፍሼ ከየቱ ጀምሬ የቱን ልንገራችሁ አልኳቸው ደስ ካለሽ ቦታ ምን አልባት ይቀልሽ ይሆናል እኛም የምንችለው ከሆነ መፍትሄ እንፈልጋለን ካልሆነም እንፀልያለን አለችኝ ብሌን ።
እሺ ካላችሁ እዚህ ጋ ከእናንተ ጋር የምታወራዋ ሠላም ከአመታት በፊት ሰው የማትቀርብ ሰው አውሬ የሚመስላት በአጋንንት እስራት የተተበተበች ነበረች በዝምታ ተዋጥኩ ሁለቱም ቀጥዪልና አሉኝ ትኩረት ሰጥተው እየሰሙኝ ነው ።
እኔም በእንባ እየታጀብኩ እነሱም በተመስጦና በእንባ ከልጅነት ታሪኬ የገጠሙኝን ፈተናዎ አንድ በአንድ ነገርኳቸው ሰአቱ ለጉድ ሄደ ሌሎቹም የዶርም ልጆች መጡ አፅናንተውኝ መክረውኝ ብሌን ፀልያልኝ ረጀብ ደግሞ ጥሩና የተባረከች ነች ብሌን ስትፀልይ እንኳን አሜን እያለች ትተባበራታለች ጌታ ሆዬ ይህቺን ነብስ አሳልፈህ ስጠኝ ብዬ በውስጤ ለመንኩ ሲያስቁኝ ቆይተን ተኛሁ ። ክላስ ውስጥ ነበርኩ ኬቢ ደወለልኝ ኬቢዬ ክላስ ውስጥ ነኝ ብዬ ቴክስት ላኩለት እሺ እንደወጣሽ ደውይልኝ ብሎ መለሰልኝ ።
ከክላስ እንደወጣሁ ደወልኩለት እቤት እንድመጣ ነግሮኝ ስልኩ ተዘጋ ስገባ ሁሉም አምሮባቸዋል ባለፈው የተዋወኩአቸው የምሳሌ እህቶችም አሉ
ጠረቤዛው በባህላዊ ምግቦች ተሞልቷል ቤቱ አምሮበታል ሁሉንም ሰላም አልኳቸው የኬቢ እናትና አባት በሀገር ባህል ልብስ ከነጩ ሽበት ና ነጠላ ጋር ላያቸው ሲያስቀኑ ። ኬቢ የታሸገ እቃ ሰጠኝ ምንድነው ስለው ከገሊ ጋር ሂጂ አለኝ ተከትያት ሄድኩ ስፈታው የሚያምር ቀሚስ ነበር ፀጉሬን አሳምራ ሰራችኝ ለብሼው ፊት ለፊቷ ቆምኩ እንዴ ሠሉ ቀሚሱን አሳመርሽው አለችኝ ኸረ ፉገራ ተይ እስቲ አልኳት በእውነት ድሮም ቆንጅዬ ነበርሽ የዛሬው ይለያል ።
በነጭ ቀሚስ እንደዚህ ያማርሽ ብትሞሸሪ ሳልኩት ደግሞ ይቅርታ ባለፈው ስለተናገርኩሽ ያው ሚስን በጣም ስለምወዳት ነው አለችኝ ችግር የለውም እህት ለወንድሟ መልካምን ትመኛለች ደግሞ አልፏል አልኳት ።
እሺ ከዚህ በላይ መቆየት የለብንም እየጠበቁን ነው አለችኝ.........


...............ይቀጥላል...............


written by Aksan Adane
ፀሀፊት አክሳን አዳነ
180 views19:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-22 22:28:42 መሪር
.......ክፍል 34.........
ፀሀፊት አክሳን አዳነ


..........ጥዬው የወጣሁበት ቦታ ላይ የለም ልቤ ደነገጠ ገላቲያ ለምን እንዲህ ክፉ ሆነች ለምሳሌ ልታሳያት ነው? ለኬብሮን ልታሳየው ነው? በቃ በጭንቀት ተዋጥኩ ሰው አልባ በነበርኩበት ሰአት የቀረቡኝ የማውቀውም እነሱኑ ነው በቃ ወንድምነቱንም ማጣቴ ነው ። ምሳሌስ ብታውቅ አትገለኝም ድብልቅልቅ ባለ ስሜት ተወረርኩ እያዘንኩ ወደ ጊቢ ተመለስኩ ። ፈተናውም አልቆ ቀኖቹም እየተገባደዱ ነው ኬብሮንን ለመርሳት ባሰብኩ ቁጥር ይብሱኑ እንድወደው ያደርገኛል ። ከክላስ መልስ ቸርችም የትም ቢሆን አብሬው ነው ምሄደው ።
ዛሬ ቅዳሜ ነው ከጊቢ ወጥቼ የነ ኬቢ ቤት ሄድኩኝ ማዘሩ ና ሰራተኛቸው ነበሩ ሰላም ብዬአቸው ተቀመጥኩ አየሩ ቀዝቀዝ ስለሚል ጃኬት ደራርቤአለው እነሱም ቡና አፍልተው ብርዱን ለመቋቋም ቤቱን አሟሙቀውታል እማ ኬቢስ አልኳቸው ይመጣል አሁን እዚህ ነበር ስልክ ሊያናግር ወደ መኝታ ክፍሉ ሳይሄድ አልቀረም አሉኝ ። ለቡና ቁርስ በቀረበው ቆሎ ጥርሴን እያፍታታው ብርዱ ግን እንዴት አያደረጋችሁ ነው አልኩኝ ። ውይይይ ተይው የኔ ልጅ እኔስ ቤት ነው ምውለው ይብላኝ ለእናንተ ማነሽ ነይ እስቲ ጋቢ አምጪላት አንቺንማ በዚህ ቅጥነትሽ ይዞሽ እንዳይበር አሉኝ ኸረ እማ ከእኔ የሚብሱ አሉ አደል እንዴ ጋቢው ግን ይቅርብኝ ትንሽ ሞቅ ካለኝ እንቅልፌም ይመጣ ይሆናል ብዬ ፈገግ አልኩ ። ምን አባቱንስና ተኚያ ቤትሽ አይደል ተነሺ እንጂ አምጪላት ብለው ኮስተር አሉ ገላቲያ ብትኖር በግልምጫ ሳትገለኝ አትቀርም የምን ጠጋ ጠጋ ነው ብላ ነበር ምትገለኝ እድሜ ለምሳሌ የሷን ሱቅ ምትቆጣጠረው እሷ ነች በውስጤ አሰብኩና ፈገግ አልኩ ።
ኬቢ እየተጣደፈ መጣ እማ እማ እየተጣራ ምነው የኔ ልጅ እናት ልቧ ተሰቀለ ፊቱ በደስታ ተፍለቅልቋል እኔም በተቀመጥኩበት ሰራተኛዋም ጋቢውን ይዛ በቆመችበት ለመስማት አቆበቆብን


ሚስ ልትመጣ ነው ነገ እንደሚገቡ ነገረችኝ ከአባቷ ጋር እማ ሚሳሌ ልትመጣ ነው ደስታው ወደር አልነበረውም በተቃራኒው እኔ በሀዘን ተኮራመትኩ እንኳን ደስ አለህ የኔ ልጅ በል ና ተቀመጥ ቡናው ወርዷል አሉት እንዴ ይቺን አይጥ መች ሰላም አልኳት ብሎ ሰላም አለኝ ቆየሽ ከመጣሽ አለኝ እና አንድ ሰአት አይሆንም አልኩት አትዋሺ ከደቂቃዎች በፊት እዚው ነበርኩ አለኝ ደስ ይላል እንኳን ደስ አለህ አልኩት ኸረ እንዲው በደረቁ በዚህ ብርድ ማኪያቶ ጋብዢኝ አለኝ እሺ አልኩት ማዘሩ ኸረ ልጅቷን በብርድ አታንቀዥቅዣት ትቀመጥበት አለችው ኸረ እማ ምን ወጣት አደለች እንዴ አንቺን ስታክል ትቀመጣለች ተነሺ ተነሺ አለኝ
ኸረ ተረጋጋ የተቀዳውን ቡና ልጠጣበት ብዬው ጠጥተን ወጣን ቅርብ ስለሆነ በእግር ወክ እያደረግን ነው ። የከተማዋ ድባብ ደስ ይላል ሰዉ ሁሉ ጃኬት ደራርቦ ኮፊያ አድርጎ ወዲህ ወዲያ ይተራመሳል ግማሹ እንደእኛ ሲያዘግም ግማሹ ይጣደፋል ካፌ ደርሰን ማኪያቶውን አዘዝን ዝናቡ ያካፋ ጀመረ ኸረ ኬቢ ከሞቀበት አውጥተኸኝ ዛሬ ይዝነብና አንተን ነው እንደ ዣንጥላ ምጠቀምህ አልኩት ከቻልሽኝ ግድ የለም ለአንቺ ደግሞ የማልሆነው አለ አለኝ ኸረ ምሳሌን መሰልኩህ እንዴ አልኩት ።
ወይኔ ሰሉ እንደዛሬ ደስ ብሎኝ አያውቅም ገና ሳትመጣ እንዲ ደስ ያለኝ ነገ ምን ልሆን እንደምችል እንጃ ፊቱ በፈገግታ አሸብርቋል ማኪያቶውን እያማሰለ እንዳቀረቀረ ትኩር ብዬ እያየሁት ከነገ በኋላ አላስፈልግህማ አልኩት እንባ እየተናነቀኝ.............


...............ይቀጥላል.................

@yebirihan_lijoch
@yebirihan_lijoch


written by Aksan Adane
ፀሀፊት አክሳን አዳነ
162 views19:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-21 21:25:41 መሪር
......ክፍል 33 .......
ፀሀፊት አክሳን አዳነ



.......እንዲህ ይል ነበር ሠላም ግን ምን ብበድልሽ ነው ። ለአንቺ ክፉ ሆኜ አውቃለሁ? ምን እንደገጠመሽ ስጠይቅሽ ይብሱኑ ተቀያየረሽ ተናዳ ይሆናል ብዬ ነበር ቸርች እያለሁ ጥለሽኝ ተመለስሽ ምን እንደገጠመሽ ለማወቅ በጣት ከሚቆጠር ጊዜ በላይ ደጋግሜ ደወልኩ መልስ የለም የዚን ያክል በህይወትሽ ውስጥ የማላስፈልግሽ ሰው ከሆንኩ ግድ የለም እንደወደድሽ ምን አልባትም ሳላውቅ አስቀይሜሽ ይሆናል። ሰው ነኝና ግን እኛ ህፃናት አይደለንም በንግግር መፍታት ይቻል ነበር አንቺን ካስጠላሁሽ ምን አደርጋለው ካወኩሽ ቀን ጀምሮ እንደ እናቴ ልጅ የምሳሳልሽ እህቴ ነሽ አሁንም ላንቺ ያለኝ ቦታ አልተቀየረም እንደው ትንሽ ለእኔ ቦታ ካለሽ ስልኬን አንሺ ካልፈለግሽም ደስ እንዳለሽ አድርጊ እወድሻለው ትንሿ እህቴ ። ይላል አንብቤ ጨረስኩ
ሳላውቀው አይኔ በእንባ ርሷል ወይኔ ኬብሮን ውስጤ ገብተህ ባየህልኝ ሚሰማኝን ድብልቅልቅ ስሜት ።
ጭንቀቴ በዛ ገላቲያ ደብተሬን ማንበብ አልነበረባትም ምነው መፃፍ የጀመርኩ ቀን እጄን በሰበረው ብዬም ተመኘው ።
ይህ ከተፈጠረ ቀናቶች አለፉ የሚገርመው ግን ለኬቢ አልደወልኩለትም እሱም ከመልዕክቱ በኋላ አልደወለልኝም ። አንድ ሁለት ጊዜ መስሪያ ቤቱ አከባቢ ተደብቄ አይቼዋለው ። ፈተናም ስለደረሰብኝ ትኩረቴን ትምህርት ላይ አድርጌአለሁ እና ደግሞ ከጥናቴ በኋላ ከጌታዬ ጋር አሳልፋለው ሳወራው ጭንቀቴን ረሳለሁ ለዚህም 24ሰአት መፀለይ ያምረኛል የሆነ ሰላም እረፍት ደስታ ይሰማኛል ።
ዛሬ እሁድ ቀን ነው ። ቸርች ከሄድኩ ስለቆየው ፈተናም ነገ ስለምንጀምር በጠዋቱ ነበር የሄድኩት በወንድሞች ህብረት መካከል ደስ የሚል ቃል ተካፍዬ ፀባኦት በሚያደርስ ዝማሬ ተባርኬ ወጣሁ ። ሰዎችን ሰላም እያልኩ ከጊቢው ስወጣ ኬቢ በመኪናው መንገድ ዘጋብኝ መኪናው ውስጥ ገላቲያም አለች ኡፍፍፍፍ መጥፎ ስሜት ጭንቀት ነግራው ይሁን አዋረደችኝ ይሁን ልቤ ይመታ ጀመር ።



ከመኪናው ወርዶ ፊት ለፊቴ ቆመ መሬት መሬቱን እያየሁ አቀረቀርኩ ኸረ ሰላም ክፉ ነሽ ጌታን ከዚህ ሁሉ ጊዜ በኋላም አታናግሪኝም እኔ ኮ ናፍቀሽኝ ውሎዬ ዩኒቨርሲቲው በር ላይ ሆኖ ነበር ተስፋ ቆርጬ ተውኩት እሺ ምን አስቀይሜሽ ነው በናትሽ ኡፍፍፍፍፍ አልኩ በውስጤ አልነገረችውም ማለት ነው ቀና በዬ ሳየው ፊቱ ሲያሳዝን ልምምጥ የሞላበት ንግግር ዝም ብዬ ሳፈጥበቶ እንዴ ቆይ ምነው የዚህን ያክል አለኝ እንደ እባብ ጥምጥም አልኩበት ኸረ ድርቅና ልለቀው ነው ። ይሄኔ በልቡ ልጅቷ ምን ወሰድ መለስ ያደርጋታል ሳይልም አይቀርም ። ገላቲያን ሳያት በመስታወቱ ክፉ አስተያየት እያየችኝ ነው ። ቶሎ ለቀኩት ትንሿ እህቴ ይቅርታ ተደረገልኝ ማለት ነው አለኝ ኸረ ኬቢ አንተ እኮ ሰው ምታስከፋ አይደለህም በአንተ አዝኜ አላውቅም የሆነ ነገር ገጥሞኝ ነው እንደውም በጣም ይቅርታ አልኩት የኔ ትንሽዬ ዋናው አሁን ደህና መሆንሽ ነው ግን ትቀጪአለሽ አለኝ ምን አልኩት ምሳ ትጋብዢኛለሽ አለኝ እሺ ብዬ ተስማማው ወደ መኪናው ገባን ገላቲያንም ሰላም አልኳት የማስመሰል ሰላምታ ነበር ።
እኔ ግን ስለ እውነት ከልቤ ነበር በፊት ወደምናዘወትርበት ሬስቶራንት አቀናን የሚገርም ምሳ በልተን ሂሳብ ልከፍል ስል ኬቢ ኸረ ማምረር ስሚ ተማሪ ነሽ ሌላ ቀን ትክሺኛለሽ ብሎ ሂሳቡን ከፈለ ። ለምን አንቺጋ ሄደን ቡና አታፈሉም አለ ገላቲያ ወዲያው ማሚ ትጠብቀናለች ታውቅ የለ እንሂድ ነገ ይሻላል አለች እኔም የወጣው ቀን ዲያሪውን አልጋው ላይ ወርውሬ መውጣቴ ትዝ ሲለኝ አው ዛሬ አይሆንም አልኩ እንደውም ቶሎ መሄድ አለብኝ ነገ ሚገባ አሳይመንት አልጨረስኩም አልኳቸው ኬቢ ዛሬውኑ ሠሉ ነው? አለኝ እውነት ነገ ክስሀለው አልኩት እሺ ልሸኝሽ ሲል ኸረ አይሆንም ብዬ በቅፅበት ብድግ አልኩ ና ወጣሁ ወደ ቤት ነበር ያቀናሁት እንዳጋጣሚ ቁልፍ ቦርሳዬ ውስጥ አለ ሁላቸውም ጋርም አለ በሩን ከፍቼ ገባሁ ቤቱ ፅድትድት ብሏል ዲያሪው ጥዬው የወጣሁበት ቦታ ላይ የለም......



............ይቀጥላል........

@yebirihan_lijoch
@yebirihan_lijoch


written by Aksan Adane
ፀሀፊት አክሳን አዳነ
220 views18:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-21 21:25:41 መሪር
........ክፍል 32..........
ፀሀፊት አክሳን አዳነ


...........ለቅቄ ወጣሁ ወደ ቤት እንደደረስኩ ገሊ አልጋዬ እግርጌ እጆቿን አጣምራ በእግሮቿ አስደግፋ ተቀምጣለች
ምነው ገሊ ሰላም አይደለሽም አልኳት ኸረ ሰላም ነኝ ሰላም በዝቶ አለችኝ ንግግሯ የፌዝ ነበር ። ምን ሆነሻል የተፈጠረ ነገር አለ አልኳት አንቺን ልጠይቅሽ ስለ ኬቢ አለችኝ ማለት ኬቢ ምን ሆነ አልኳት ሠላም አትድረቂ ገብቶሻል አለችኝ ምኑ ጌታን ግራ እያጋቤባሽኝ ነው አልኳት በቃሽ የጌታን ስም መጥራት አያስፈልግም ማስመሰል ግን አይከብድም እንዴት እስከአሁን ቻልሽበት ገላትያ ትናገሪ እንደሆን ተናገሪ ብዬ እኔም ተቀያየርኩ ።
ጅራፍ ራሶ መትቶ ራሱ ይጮሀል አለ የሀገሬ ሰው ። ይኸውልሻ ብላ ዲያሪዬን ወረወረችልኝ እስትንፋሴ ቀጥ ሲል ተሰማኝ ጉልበቴ ተብረከረከ በምን ሞራሌ ምን ላውራ ወንበሩ ላይ ደርቄ ቁጭ አልኩ እህ መልስሽ ምንድነው ጥሩ ሰው መስለሽ የወንድሜና የፍቅረኛውን ህይወት ልታበላሺ ምን በደልንሽ ለአንቺ ህይወት ያልከፈልነው ዋጋ አለ? ምሳሌስ ብትሆን ለአንቺ ከመልካምነት ውጪ ምን በድላሻለች እንዲህ እየጠላሻት ማስመሠሉን እንዴት ቻልሽበት በጣም ክፉ ሰው ነሽ ሰላም እጅግ በጣም ክፉ
በቃሽ ብዬ አፈጠጥኩባት እኔ ክፉ ሴት አይደለሁም ዕድሌ ነው ክፉ ። እንባዬ በሁለቱ ጉንጮቼ ይጎርፍ ጀመር በጣም ከፋኝ ። አንቺ ግን ምን አይነት ደፋር ብትሆኚ ነው የሰው ሚስጥር ለማንበብ የደፈርሽው አልኳት በደከመ አነጋገር ።
ከአንቺም የሚብስ ደፋር ተገኝቶ ደፋር አልሽኝ እኔስ የወንድሜ መስሎኝ ነበር ለካስ አንቺ ጠላታችን ሆነሽ ኖሮአል ።
ይኸውልሽ ምሳሌ ማለት አብሮ አደጌ መካሪዬ እህቴ ማለት ነች በሷና በወንድሜ ድርድር አላውቅም ።
ኬቢም ይህን ቢያውቅ ይቅር አይልሽም በምሳሌ ቀልድ አያውቅም እና ቤተሰቡ ሁሉ የሚያውቀው ጉዳይ ነው አትድከሚ ይሄን ጠላቻሽን ደግሞ ከምሳሌ ላይ አንሺ ብላኝ እየተመናቀረች ሄደች የዲያሪውን ደብተር ወደ ግድግደረው በሀይል ወረወርኩት ምርርር ብዬ አለቀስኩ እንዴት አትረዳኝም ማፍቀር በኔ ተጀመረ እንዴ ብዬ የሆነ መጫወቻ እንደነጠቁት ህፃን እየተንከባለልኩ አለቀስኩ ምሬቴ ገንፍሎ ተሰማኝ ሰው ለአብሮ አደጉ እንዲህ ያስባል የኔ የአጎት ልጆች ህይወቴን አመሠቀቃቀሉት


በሩን ቆልፌ ፀሎት አይሉት ክርክር አይሉት ጌታ ሆይ ለምን? ለምን? ክፉ ሆንኩ ለምን የሰው ህይወት ለመበጥበጥ አሰብኩ አንተስ ለምን ተውከኝ ለምን ለፍቃዴ አሳልፈህ ሰጠኸኝ በለቅሶ ቀወጥኩት መሬት እንደተደፋው ከለሊቱ 7ሰአት ሆነ አይኔ አባብጦአል ወደ አልጋው ለመውጣትም አቅም አጣሁ በብርዱ እየተንቀጠቀጥኩ አሸለበኝ ስነቃ አይኔን መክፈት አልቻልኩም የማታው ለቅሶ አይኖቼን ጎድቷቸዋል እንደምንም ከአጠገቤ የወደቀውን ስልክ ስከፍተው 4:ሰአት ሆኗል የበሩ መስታወት ውጪው ወገግ እንዳለ ያስታውቃል ።
የኬቢ 29 missd call አለ ። መልሼም አልደወልኩም ተነስቼ ፊቴን ታጠብኩ ልብሴን ቀያይሬ ቤቱንም እንደዛው ትቼው ቆልፌ ወጣሁ ። ቀጥታ ወደ ጊቢ ነበር የሄድኩት ድብርት ተጫጫነኝ ከክላስ እንደወጣሁ ላይብረሪ ሄድኩ ግን ይሄ ሁሉ ነገር ተፈጥሮም ኬቢ ይናፍቀኛል ሰሞኑንማ አጉል ለምጄው ጨነቀኝ በቃ አልቅሺ አልቅሺ ይለኛል ገላቲያ ግን ምን ሆና ነው ምሳሌን የሆነች መሠለኝ እኮ በዚያ ላይ ፅሁፎቼ ሁሉም የሀዘን ብቻ ናቸው ቢያስለቅሱና እንዳሳዝን ቢያደርጉ ነው ። ብቻ አንተ ያልከው ይሁን እያልኩ የተናነቀኝን እንባ ዋጥ አደርገዋለሁ ።
ከላይብረሪ ወጥቼ ወደ ዶርም አቀናሁ አረፍ ብዬ ስልኬ ጮኸ ኬቢ ነው አላነሳሁትም እጄ ላይ ዘጋ ምን ብዬ አወራዋለሁ ብዬ አፈርኩ ከቸርች ትቼው የሄድኩበትን ምክኒያት እንኳን አያውቅም ቢጠይቀኝስ ምን እመልሳለሁ ።
ስጨናነቅ ሳወጣ ሳወርድ ቴክስት ገባ
ርዝመቱ ታሪክ ይመስላል ኬቢ ነበር እንዲህ ይላል............



................ይቀጥላል...............


@yebirihan_lijoch
@yebirihan_lijoch

written by Aksan Adane
ፀሀፊት አክሳን አዳነ
206 views18:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-21 20:15:26 YouTube account ሰብስክራብ አድርጉልን የጌታ ቤተሰቦች አለንላችሁ በሉን እንጂ ተስፋ ሳንቆርጥ። አሁን አንድ አፍታ ገብታችሁ ብታደርጉልን ደስ ይለናል ወዳሰብነው አስተማሪ ጉዳዮችም ለመሄድ ይረዳናል

https://youtube.com/channel/UCtp5XBjV0p6Mw0BX1Nmu81w

አሁን ስለምታደርጉልን እናመሰግናለን።ጌታ ይባርካችሁ
159 views17:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-03-20 21:32:43 መሪር
........ክፍል 31..........
ፀሀፊት አክሳን አዳነ


..........እንቅልፍ ወስዶት ነው አልኳት ኸረ አይደለም ሞቶ ገንዤው ነው አለችኝ ሳቄ አምልጦኝ ድምፄ ጮክ ሲል ነቃ ከነቃህ አይቀር ብዬ በደንብ ሳኩኝ ገሊ በፈገግታ ሴትዮ ዝም ብለሽ አትገልፍጪ ቁርስ እንብላ አለችኝ ።
ኬቢ አይኑን እያሻሸ ምንድነው ሚያስቃችሁ ብሎ መልስ ፍለጋ እንዴ ወደ እሷ አንዴ ወደ እኔ ተመለከተ እቺ ጉደኛ እህትህ ብዬ ከመጀመሬ ዋ ሰላም ዋጪያት ዋጥ አድርጊው አለችኝ እሺ ትቼዋለው ኬቢ ግን አንተ ደህና ነሃ አልኩት ( ወይ ደና ይኸው በድን ሆኜ አለኝ ከገሊ ጋር ተያይተን በድጋሚ ሳቅን ሞቶ ገንዤው ያለችው ትዝ አለኝ እናንተ ምን እየሆናችሁ ነው ብሎ ተኮሳቸረ እንደምንም ሸፋፍነን አለፍን ።
እኔ የምልህ ምሳሌ መች ትመጣለች አልኩት ገና ሳትደርስ መች ትመጣለች አንቺማ ምን አለብሽ ይብላኝ ለእኔ እንጂ ስልኩ ጠራ አንስቶ ማዋራት ሲጀምር
ገሊን አንቺ ባልነግረው ደግሞ ሠላም አይደለሁም አልኳት ድሮስ ምን ሰላም አለሽ በይ ንገሪውና እንተያያለን አለችኝ ቁርስ የበላንበትን ሰሀን እያነሳች ከቢ ስልኩን ዘግቶ ሰዎች ማሚ ናት ኑ እያለች ነው ምርጥ ምግብ አለ መሠለኝ አለን ኸረ ኬቢ ሆዳም አሁን በልተን አሁንም ልንሄድ ነው ስለው የማሚ ምግብ እናንተ እንደምታጨማልቁት ውሀ ውሀ የሚል ሙያ መሠለሽ ነይ እንሂድና እስከዛሬ የበላሻቸውን ምግቦች ትረሺያቸዋለሽ አለኝ ገሊ እሱ አይካድም ግን ምን አይነት ንቀት ነው እስከዛሬ እኛ የሠራነውን መስሎኝ ምትበላው ብላ አፈጠጠችበት አይ እኔ የምሳሌና የማሚ ምግብ ብቻ ነው ምግብ የሚመስለኝ እየሳቀ ጃኬቱን ደርቦ ወጣ የምር ተናደድኩ በሱ ቤት እኮ መቀለዱ ነው ።
ተሰብስበን ወደ እነርሱ ቤት ሄድን እንዳለውም የሚገርም የምሳ ግብዣ ተዘጋጅቷል ቤተሰቦቹ በሙሉ አሉ የማውቃቸውን ሰላም ብዬ የማላውቃቸውን ደግሞ የምሳሌ እህቶች ናቸው ብሎ አስተዋወቀኝ
ሰውነቴን ደነዘዘኝ ቤተሰብ የጨረሰውን ጉዳይ ነው አጉል ተስፋ ያደረኩት ብዬ ፊቴ ቅጭም አለ ቤተሰቦቿ ጋር ነው የምትሄደው አላልከኝም አልኩት እንዴ ታዲያ ሁለቱ እህቶቿ እዚሁ ናቸው እናትና አባቷ አሜሪካ አለኝ እዛ ቆይተን ወደ ጊቢ ተመለስኩ ።


ምሳሌ ከሄደች ሁለት ወራት ተቆጠሩ ውሎዬ ከኬቢ ጋር ሆነ ከጊቢ እንደወጣሁ ወይ እቤት ሄዳለሁ ወይ እሱ ጊቢ በር ጋር መጥቶ ይወስደኛል ገላቲያ ኸረ እናንተ እስክትክዱኝ ድረስ
አበዛችሁት ትለን ጀመር ።
ከስራ እንደወጣ ደውሎልኝ እቤት ሄድኩ
ጊቢው ውስጥ አበቦቹን ውሀ እያጠጣ ነበረ ሰላም ብዬው ማዘሩን ለማናገር ወደ ውስጥ ገባሁ እሳቸውን ሰላም ብዬ እንድቀመጥ ጋበዙኝ ትንሽ አጫውቼአቸው በረንዳው ላይ ቡና ላፈላላቸው ስጠይቃቸው እሰይ የኔ ልጅ እንደው ከአፌ ነጠቅሽኝ መች ይሆን ቡና አፍልተሽ ምታቀምሺኝ ልልሽ ስል በይ እንደነገሩ አሰነዳጂው እኔ አረፍ ልበል አሉኝ እሺ ብዬ እቤት ውስጥ ያለችው ሰራተኛ እያገዘችኝ የሚያስፈልጉትን ግብአቶች በረንዳ ላይ አወጣን ።
ኬቢ እንዴ ሰው ሴት ሆነ አለኝ ምን ማለት ነው ስታስጠላ ብዬ ስኮሳተርበት ኸረ ሰቀልድ ነው ። አታፍጪብኝ ቶሎ ቶሎ አፍዪውና ቸርች መሄድ አለብን አለኝ ውይ እረስቼው ዋናውን ጉዳይ እሺ በቃ ብዬ እጣደፍ ጀመር የሚገርም ቡና አፍልቼ የማዘርን ምርቃት ተቀበልኩ ትንሽ ተጨዋውተን ኬቢም ልብሱን ቀያይሮ ወጣን መኪናውን ሊያስነሳ ጊቢ አስከፍተን ምሳሌ ደወለችለት ሲያወራት በእርጋታ ነው በትህተና ነው አይኖቹ ያሳዝናሉ ለወራት ሳይሆን ለዘመናት ያልተገናኙ የው የሚመስሉት ከኬቢ ጋር እንዲህ እየተቀላለድን ረጅም ሰአታት አብረን እያሳለፍን የሚያወራልኝ ስለሷ ነው ታማኝነቱ ይበልጥ እንደወደው አደረገኝ ። የእውነት ምሳሌ እድለኛ ሴት ነሽ አልኩኝ በውስጤ እንዴ የት ሄድሽ የኬቢ ንግግር ከሄድኩበት ሀሳብ አባነነኝ አለው እባክህ የት ሄዳለው አልኩት ብሶቴና ምሬቴ ፈንቅሎ በእምባ ሊወጣ ጥቃት ቀርቶት መስኮቱን ተደግፌ በዝምታ ተዋጥኩ እሱ ያወራል እኔ መልስ አልሰጠውም ቢቸግረው መኪናውን አቁሞ ሠሉ ምን እየሆንሽ ነው ፊትሽ ልክ አደለም የሆንሽውን ንገሪኝ አለኝ ኬቢ ምንም አልሆንኩም እየረፈደ ነው አምልኮውን በጊዜ እንድረስ አልኩት ኸረ ሠሉ ያፈጠጠ ውሸት እኔ አላውቅሽም ፊትሽ ልክ አደለም ስልሽ በጌታ ምን ሆንሽ ሳላውቅ አስቀየምኩሽ እንዴ አጉል ቀልዳለው እያልኩ ንገሪኝ ጨቀጨቀኝ ዝም አልኩና ጭቅጭቁ ሲበረታ ኬብሮን በፈጠረህ አትጨቅጭቀኝ ቸርቹን እንሂድ አይ ካልክ ደግሞ ወርጄ በእግሬ ሄዳለሁ አልኩት ደንግጦ ይሁን በአንዴ ዝም አለ መኪናውን አንስቶ የንዴቱን ይሁን በፍጥነት ያሽከረክረው ጀመር በንግግሬ የሌለ ተሸማቀኩ ጭራሽ ኬብሮን ብዬም ጠርቼዋለው ለካ ።
ዝም እንደተባባልን ቸርች ደረስን ፀሎት ተጀምሮ ነበር ሀሳቤን ሰብሰብ ለማድረግ እሞክር ጀመር ገላትያ ደጋግማ ትደውላለች ሁለት ሶስቴ አላነሳሁም ሲደጋገም ወጥቼ ሄለው ገሊ አልኳት የት ነሽ ሠላም አለች ድምፇ ያስፈራል ምነው ገሊ ሰላም አይደለሽም አልኳት ከኬብሮን ጋር ነሽ የቁጣ ጥያቄ አዎ ምነው ቸርች ነን አልኳት በጣም ስለምፈልግሽ አሁኑኑ አንቺ ቤት ነይ አለችኝ ልቤ ለሁለት ተሰነጠቀ እሺ ለኬቢ ነግሬው መጣሁ አአአ አላስጨረስችም በፍፁም አይሆንም ብቻሽን ነይ አለችኝ ሀሳቤ ድብልቅለቁ ወጣ ቀጥ ብዬ የቸርቹን ግቢ ለቅቄ ወጣሁ ............


................ይቀጥላል...........

@yebirihan_lijoch
@yebirihan_lijoch


written by Aksan Adane
ፀሀፊት አክሳን አዳነ
219 views18:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ