Get Mystery Box with random crypto!

( ታላቅ አባትነት ) በዛን ሰሞን የተለቀቁ የማህበሩ አባላት ፅሁፍ እና ግጥም ላይ ክርክር | በክርስቶስ ( in christ)

( ታላቅ አባትነት )


በዛን ሰሞን የተለቀቁ የማህበሩ አባላት ፅሁፍ እና ግጥም ላይ ክርክር እና ወይይት ይዘናል ። ለተዘጋጀው የስነፅሁፍ ምሽት የምናቀርባቸውን ስራዎች ከመቅረባቸው በፊት ለብቻችን ሂስ እየተራጨን ነበር ። ልንጨርስ ዳር ዳር ስንል በመሃል ግን ተባራሪ ወሬ እና ሀሳብ ተነሳ ... ጉዳዩ ከሰሞኑን በማህበሩ የቴሌግራም ግሩብ ውስጥ በማይታወቅ ስም እየተለቀቀ ያለ ግጥም አለ እና የማን ነው የሚል ነበር ። የማን እንደሆነ ውስጤ አውቆታል ቢሆንም ቢሆንም ቢሆንም እንዲሉ ሀምሳ አለቃ ገብሩ እኔም ባላወቀ በቢሆንም አንዳችም ትንፍሽ ሳልል ተከታተልኳቸው ። በመጨረሻም እጣ ሳይጣጣሉ ማን እንደሆነ ታወቀ ወደ ተባለ ሰው የሁሉም ትኩረት ዞረ ። ግጥሞቹ የሚፃፉበት አዲሱ ስም እንደዚህ ይሰኛል " ታላቅ አባትነት" ። ታላቅ አባትነት እንደ ነፃ ትግል ብዙ አሟገተ ። ታላቅ አባትነት የሚገልፀው አብን እንደሆነ ተረድቻለው ደግሞም ነው ከአብ በላይ አባትነት ይኖራል እንዴ ??

ሐዋሪያው ጳውሎስ የአብን ታላቅ አባትነት አጠር ባለ ሀረግ እንዲህ ይገልፀዋል " የክብር አባት " (ኤፌ1:17) ....የክብር አባት የከበረ አባት ነው እንደማለት ነው ።

አሁንም ጳውሎስ በዛው በኤፌሶን ላይ አባትነት ሁሉ ከሚሰየምበት ከአብ ፊት እንበረከካለሁ ይላል (ኤፌ 3:14) ። ስለ መንበርከኩ ያስረዳል ዝም ብሎ ተንበርካኪ ወይም ትርጉም የሌለው መንበርከክ ሳይሆን ትርጉም ሊሰጥ በሚችል ፊት ነው በጉልበቱ የተንበረከከው ።ይሔን የፃፈው በእስር ቤት ነው ፤እናም ከእስር ቤት መንበርከክ ማለት ከባድ ነገር ነው ። እስር ቤት ሆነ የትም የጳውሎስ ጉዳይ መንበርከኩ በሰው አይደለም ፣ በአለቆች፣ በራሱ ፊትም አይደለም የሚንበረከከው እሱ በሰማይ እና በምድር አባትነት ከሚሰየምበት ከአብ ፊት ነው ።በሰማይ እና በምድር አባትነት ከሚሰየምበት ማለት አባትነት በሰማይም ሆነ በምድር የሚጀምረው ከአብ ነው ። አባት ማለት መገኛ ምንጭ ማለት ነው ።ስለዚህ ከአብ ነው ለምድር ቢሆን አባትነት የመነጨ ። ታዲያ ይሔ በሰማይም ሆነ በምድር አባትነት የሚሰየመው የሚጀምረው ከአብ ከሆነ የአብ አባትነት ታላቅ ነው ። ታላቅ አባትነት !!!ካሉስ ቢሆን ይሔ ነው ።

...... ነገር በ3 ምስክር ይፀናል ካሉ አይሁድ በህጋቸው መሰረት እኛም አንድ ጨምረን የአብ አባትነትን ከጳውሎስ እንመልከት ።

.....
በሮሜ (ሮሜ 8:15) ላይ እንደሚነግረን ማንም ፍጥረታዊ ሰው አብን አባቴ የማለት ብቃቱም ድፍረቱም የለውም ። አብን አባ የማለት አቅሙ ያለው በውስጡ መንፈስ ቅዱስ ያደረ እና መንፈስ ሲረዳው ብቻ ነው ሊል የሚችለው ። የመፀሀፍ ቅዱስ አስተማሪዎች እንደሚናገሩት አሁን የጠቀስነው አብ አባቴ የሚለው ቃል በግሪከኛ አባ አባዬ ብሎ ይተረጎማል ይላሉ ። አባ አባዬ ደግሞ ሁለት መጠሪያ ነው ልክ ንጉሰ ነገስት ተብሎ ከንጉስ እንደሚልቅ ሁሉ አብ አባዬ የላቀ አባትነት ያሳያል ይላሉ ። ታዲያ አባ አባት ታላቅ አባትነት ነው ማለት ነው ። መንፈስ ቅዱስ ይሔን ታላቅነት አባትነት በልብ ውስጥ ያሰርፀዋል ፣ ያፈሰዋል እንድናጣጥም በልባችን ያጥነዋል ያኔ አባ እንላለን አፉን እንደሚፈታ ህፃን እየተኮላተፍን አብን እንጠራለን ።

...........

የፍቅር ሐዋሪያው ዩሀንስ ደግሞ የአብን ታላቅ አባትነት በፍቅር ይገልፀዋል ።እንደ ዩሀንስ አባባል " የአባት ፍቅር " ። 1ዩሀ3:1) ... በዚህ ታላቅ አባትነት ወይንም ለአብ ልጆች ልንባል እንዴት አይነት ፍቅር አየን ። እኛን ልጆች ለማድረግ አብ ህመምን ታሟል ማለትም አንድ ብቻ ልጅ አለው እሱ ኢየሱስ ነው ።ኢየሱስ ውድ ልጁ ነው ። እኛን ለማዳን ውድ ልጁን ሰጠ ..ልጅ ሲሰጥ ቀላል አይደለም ህመም አለው ።ፍቅር ነዋ ልጅ ነዋ ። እና እኛን ልጅ ያረገን ይሔን አልፎ ነው ታዲያ እንዴት ያለ ፍቅር ነው??አዎ ይሔ አባትነት ነው ታላቅ አባትነት ።

ሊሰመርመት የሚገባው እኛ የፀጋ ልጆች ነን ኢየሱስ ግን የባህሪ አምላካዊ ልጅ ነው !!!


ታላቅ አባትነት


ፊሊሞን ነጋ
@ownkin
@cgfsd