Get Mystery Box with random crypto!

CALVARY gospel ministry

የቴሌግራም ቻናል አርማ calvarygospelministry — CALVARY gospel ministry C
የቴሌግራም ቻናል አርማ calvarygospelministry — CALVARY gospel ministry
የሰርጥ አድራሻ: @calvarygospelministry
ምድቦች: ሽያጭ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.31K
የሰርጥ መግለጫ

"But we preach christ crucified, unto.
The jews a stumblingblock, and unto the Greeks foolishness;"
1corinthians 1: 23
☎️ 0989929053 addis ababa
☎️ 0910058808 addis ababa
☎️ 0982031334 addis ababa
☎️ 0989929052 hawassa

Ratings & Reviews

4.00

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-13 08:12:04

268 viewsScripture 𓆩༢࿔ྀુ, 05:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-20 11:31:28 https://vm.tiktok.com/ZMN9arm4w/?k=1
608 viewsYUMMY, 08:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 21:37:28
778 viewsScripture 𓆩༢࿔ྀુ, 18:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-27 14:05:59
46 በመቶ ምዕመናን ብቻ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠውን 'ታላቁ ተልዕኮ' እንደ ‘አደራ’ እንደሚያዩት አንድ ጥናት ገለጸ፡፡
በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 28፡19 ላይ ‘“ስለዚህ ሂዱና ሕዝቦችን ሁሉ በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው፤” የሚለውን ጌታ ኢየሱስ የሰጠውን ታላቁን ተልዕኮ በተመለከተ በመጋቢዎችና በሌላው ምዕመን መካከል ሰፊ የአመለካከት ልዩነት እንዳለ ባርና የተባለ አጥኚ ተቋም ያወጣው አዲስ መረጃ አሳይቷል፡፡
በዚህ ጥናት ውጤት መሰረት ታላቁ ተልዕኮ ለሁሉም ክርስቲያን የተሰጠ አደራ መሆኑን 85 በመቶ መጋቢዎች ሲያምኑ ከምዕመናኑ ግን 46 በመቶዎቹ ብቻ ተልዕኮው የሁሉም አማኝ 'አደራ' እንደሆነ ያምናሉ ብሎዋል፡፡
ሚሽን ኢንዲያ ከተባለ ተቋም ጋር በመተባበር የተደረገው ይህ የባርና አዲስ ጥናት ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የሰጠ 'ታላቁ ተልዕኮ” የማን ሃላፊነት ነው? እና በምን አይነት መልኩ ሊተገበር ይገባል? በሚለው ላይ የቤተክርስቲያን መጋቢዎችንና የሌላውን ምዕመን ግንዛቤ ለማወቅ የተደረገ ሲሆን በርካታ መጋቢዎችና ምዕመናን ተካተውበታል፡፡
የጥናቱ ትንታኔ እንደሚያሳየው በአገልጋዮችና በሌላው ምዕመን መካከል ያለው ይህ ሰፊ የአመለከከት ልዩነት ለምን እንደተከሰተ የቤተክርስቲያን መሪዎች ሊፈትሹት ይገባል ብሏል፡፡
የቤተክርስቲያን መሪዎች ምዕመናኑ ይህንን ተልዕኮ በተገቢው ሁኔታ እንዲረዱትና ተሳትፏቸው በምን መልኩ ሊሆን እንደሚችል እንዲገነዘቡ ማስተማር እንዳለባቸው ጥናቱ ጠቁሟል፡፡
1.4K viewsYUMMY, 11:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-24 13:45:49
" ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ለሕያው ተስፋና ለማይጠፋ፥ እድፈትም ለሌለበት፥ ለማያልፍም ርስት እንደ ምሕረቱ ብዛት ሁለተኛ የወለደን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ፤ ይህም ርስት በመጨረሻው ዘመን ይገለጥ ዘንድ ለተዘጋጀ መዳን በእምነት በእግዚአብሔር ኃይል ለተጠበቃችሁ ለእናንተ በሰማይ ቀርቶላችኋል።"
(1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1:3-5)
785 viewsEnoch <>, 10:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-23 22:07:53
አንድ ሰው ስለ ሕዝብ ይሞት ዘንድ ይሻላል። ዩሐ ፲፰፥፲፬
ስለ ሁላችን በደል በመስቀል ላይ ዕርቃኑን ያደረ፣ሐጢያታችንን ያጠበ፣ነቀፌታችንን ያስወገደ የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው!!
ይህ ቀን የእኔ ና የእናንተ ድህነት መሠረት ቀን ነው። አንዱ ስለ ሁሉ ሞተ፤ሐጢያት የሌለበት ሐጢያት ሆኖ ተቆጠረ።
ከዚህ የበለጠ ፍቅር ለማንም እንደሌለው፣የፍቅርን ምንነት፣የፍቅርን ጥግ አሳወቀን ኢየሱስ ቤዛ ሆኖ ሞተልን።
ራስን በመግዛት፣በፀሎትና በመንፈስ መመላለስ ይሁንልን አሜን።
662 viewsEnoch <>, 19:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-23 05:20:13
568 viewsYUMMY, 02:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-21 21:55:10 ኢየሱስ ይመጣል

(የዮሐንስ ራእይ ምዕ. 22)
----------
20፤ ይህን የሚመሰክር። አዎን፥ በቶሎ እመጣለሁ ይላል። አሜን፥ ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ና።

21፤ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ ከሁላችን ጋር ይሁን፤ አሜን።

ስለዚህ እናንተ በእርሱ ስራ
ከጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃኑ የተጠራችሁ
ቅዱሳን
ለእርስቱ የተለየ ወገን የሆናችሁ

የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ ተጠርታችኃል ይህም በመስቀል ላይ ዋጋ ከፍሎ ፍቅር ግድ ብሎት ከሰማያት ወርዶ እኛን ያደነበትን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንድትሰብኩ ነው።

(1ኛ የጴጥሮስ መልእክት ምዕ. 2)
----------
9፤ እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤

10፤ እናንተ ቀድሞ ወገን አልነበራችሁም አሁን ግን የእግዚአብሔር ወገን ናችሁ፤ እናንተ ምሕረት ያገኛችሁ አልነበራችሁም አሁን ግን ምሕረትን አግኝታችኋል።

በዚህ ወንጌል፦
ወገን ያልነበርነው የእግዚአብሔር ወገን
ሆነናል
ምህረት ያላገኘን የነበርን ምህረት
አግኝተናል
በበደላችን ሙታን የነበርን በእርሱ ስራ
ህይወትን አግኝተናል
ከእግዚአብሔር ርቀን የነበርን በእርሱ ስራ
ቀርበናል
ልጆች ተደርገናል
ቤዛነታችንን አግኝተናል
እግዚአብሔር ርስታችን ሆኗል
በመንፈሱ ታትመናል
ጨለማ የነበርን ብርሃን ሆነናል .....

ይህን በጎነቱን በስፍራ ሁሉ በቤተሰቦቻንን በትምህርት ቤት በስራ ቦታ በጎረቤት በአደባባይ ... እናውራ ሙሽራው ኢየሱስ ይመጣል ለዘላለም ከእርሱ ጋር ሊያኖረን ይወስደናል። ከዚህ የሚበልጥ ምን ደስታ አለን።

ስለዚህ እርሱ ለአንድ ነፍስ መዳን ወዶ ይታገሳልና ያንንም የማስታረቅ ቃል በአንተ በአንቺ ውስጥ አኑራልና ወንጌልን በስፍራ ሁሉ በመስበክ እንዲሁም ሙሽራውን በሚጠባበቅ በተዘጋጀ ህይወት በመኖር ጌታ ሆይ ና ማራናታ እንበል።

ሉቃስ 12
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁷ ጌታቸው በመጣ ጊዜ ሲተጉ የሚያገኛቸው እነዚያ ባሪያዎች ብፁዓን ናቸው፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ታጥቆ በማዕድ ያስቀምጣቸዋል ቀርቦም ያገለግላቸዋል።
³⁸ ከሌሊቱም በሁለተኛው ወይም በሦስተኛው ክፍል መጥቶ እንዲሁ ቢያገኛቸው፥ እነዚያ ባሪያዎች ብፁዓን ናቸው።
³⁹ ይህን ግን እወቁ ባለቤት በምን ሰዓት ሌባ እንዲመጣ ቢያውቅ ኖሮ፥ በነቃ፥ ቤቱም እንዲቆፈር ባልፈቀደም ነበር።
⁴⁰ እናንተ ደግሞ ተዘጋጅታችሁ ኑሩ፥ የሰው ልጅ በማታስቡበት ሰዓት ይመጣልና።

በኢየሱስ ስም አናፍርም የተሰቀለውን ኢየሱስን በስፍራሁ ሁሉ እንጠራለን እንሰብካለን መዳን በሌላ በማንም የለምና።

እየሱስ ይመጣል
CALVARY EVANGELISM
587 viewsYUMMY, 18:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-14 12:41:10
በአሜሪካ በኮነቲከት ግዛትም የታገዘ ራስን ማጥፋት ሕጋዊ ለማድረግ የተዘጋጀው ረቂቅ ህግ ድጋሚ ውድቅ መደረጉ ተነግሯል፡፡
ላይፍ ኒውስ እንደዘገበው 5B 88 የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ ህግ ባለፈው መጋቢት ወር በግዛቱ የህዝብ ጤና ኮሚቴ በኩል ያለፈ ሲሆን ረቂቅ ህጒ ወደ ዳኝነት ኮሜቴ እንዳይሄድ የታገዘ ራስን ማጥፋት ሎቢ ቡድን ጥረት ቢያደርግም ህጉ በዳኞች ኮሜቴ ታይቶ ውድቅ እንዲሆን ተደረጓል ተብሏል፡፡
በተመሳሳይ ዜና የታገዘ ራስን ማጥፋት መፈቀድን በተመለከተ ሊደረግ የነበረን ህዝበ ውሳኔ የጣሊያን ፍርድ ቤት ማገዱም ተሰምቷል፡፡
ዘ ክርስቲያን ቱዴይ እንደዘገበው በመሞት መብት መከበር ላይ ህዝበ ውሳኔ እንዲደረግ ከ 750 ሺ በላይ ጣልያናዊያን የድጋፍ ፊርማ የተሰበሰበበት አቤቱታ የቀረበ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ውድቅ አድርጎታል፡፡
የጣሊያን የህገመንግስት ፍርድ ቤት ግን ጥያቄው በህገመንግስት የተቀመጠውን አስፈላጊን የሰው ልጅ ህይወትና ለደካሞችና ለአደጋ ለተጋለጡ ሰዎች የሚደረግ ዝቅተኛ ጥበቃን አያከብርም ብሏል፡፡
የካቶሊኩ ሊቀ ጳጳስ ፖፕ ፍራንሲስ ይህንን ረቂቅ ህግ ‘ተቀባይነት የሌለው የግድያ ህግ ‘በማለት ተችተውት የነበረ ሲሆን ድርጊቱ ሰብአዊም ክርስቲያናዊም አይደለም ብለውታል፤የህገመንግስታዊው ፍርድ ቤት ህጉን ውድቅ በማድረጉ አድናቆታቸውን አግኝቷል፡፡
በጣሊያን ህግ አንድ ሰው እራሱን እንዲያጠፋ የሚረዳ ማንኛውም ሰው ከአምስት እስከ 12 አመት እስራት ይጠብቀዋል።
637 viewsYUMMY, 09:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-04-13 21:04:22
በኢንዶኔዥያ አንድ ክርስቲያን ዩቲዩበር የ10 አመት እስራት ተፈረደበት።
ክርስትያን ዩቲዩበሩ የ10 አመት እስራት የተፈረደበት አብዛኛ ሙስሊም በሆነባት ኢንዲኔዥያ ሰዎችን ያስከፋ ነው የተባለን ቪዲዮ በዮቲዩ ቻናሉ ላይ በመለጠፉ ነው ተብሏል።
መሀመድ ካሴ የተባለው ቀድሞ የእስልምና እምነት ተከታይ የነበረውና እ.ኤ.አ. በ2014 ወደ ክርስትና በመጣው በዚህ ሰው ላይ በኢንዶኔዥያ ምዕራብ ጃቫ በሚገኘ ፍርድ የ10 አመት እስር የፈረደበት የቀድሞ እምነቱን የሚተች ቪዲዮ በዩቲዩብ ቻናሉ ሲጭን ነበር ተብሎ ነው።
ክርስቲያን ቱዴይ እንደዘገበው መሀመድ ካሴ በእስር ቤት ውስጥ በሙስና ክስ ተይዞ በነበረ ናፖሊዮን በተባለ የፖሊስ ባለስልጣን ድብድባና ስቃይ የደረሰበት ሲሆን በኢንዶኔዥያ በርካታ አብያተ ክርስቲያናት የአምልኮ ቤቶች ግንባታ ለማደናቀፍ ከሚሞክሩ ቡድኖች ተቃውሞና እንግልት የሚደረሰባቸ መሆኑም ይነገራል።
570 viewsYUMMY, 18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ