በዝውውር መስኮቱ 17 ተጨዋቾች ብቻ ዝውውራቸው ጸድቋል #እስካሁን_ፌዴሬሽን_ያወቀው_ዝውውር_የአራት_ክለቦችን_ብቻ_ነው። ሀምሌ 1 በይፋ በተከፈተው የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ባለፉት ስድስት ቀናት ብቻ ህጋዊ ዝውውር ያደረጉት ተጨዋቾች ከ20 እንደማይበልጡ ተነገረ። ከክለቦቹ ታማኝ ምንጭ በተገኘ መረጃ #ኢትዮጵያ_ቡና ብሩክ በየነ፣ አብዱልከሪም ወርቁ፣ ጫላ ተሺታ፣ ሀይለሚካኤል አደፍረስ፣ አብዱል ሀፊዝ ቶፊቅና መስፍን ታፈሰን ሲያስፈርም የሮቤል ተ/ሚካኤል ውልን ማራዘሙ ታውቋል። በርካታ ዝውውር እያደረገ ነው የተባለው #መከላከያ በረከት ደስ፤ ዳግም ተፈራ፣ ምንይሉ ወንድሙና ሳሙኤል ሳሊሶን ሲያስፈርም #ፋሲል_ከነማ በበኩሉ የበዛብህ መለዮ፣ የሱራፌል ዳኛቸውና የሽመክት ጉግሳን ውል ሲያድስ #ባህርዳር_ከተማ ፍጹም ጥላሁን፣ ያሬድ ባዬህና ዱሬሳ ሹቢሳን ማስፈረሙ ታውቋል። ከ16ቱ ክለቦች እስካሁን በኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ማረጋገጫ ያገኙት #አራት_ክለቦች ብቻ መሆናቸው ታውቋል። ምንጭ #ሀትሪክ_ስርአት @bunawuatiawaki @bunawustiawaki 73 views Fisho (የከቡየ ልጅ) , 17:54