Get Mystery Box with random crypto!

#አማኑኤል_ዮሀንስ_የሚገባውን_ሽልማት_ተቀበለ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዓርብ የወዳጅነት ጨዋታ ለ | የቡና ጉዳይ ይመለከተኛል

#አማኑኤል_ዮሀንስ_የሚገባውን_ሽልማት_ተቀበለ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዓርብ የወዳጅነት ጨዋታ ለማድረግ ዛሬ ከጠዋቱ 3:00 ላይ ወደ ኮሞሮስ ከማቅናቱ አስቀድሞ ትናንት ምሸት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ ቡድኑን ሲያበረታቱ በአፍሪካ ዋንጫው ላይ በሰራው ስራ አማኑኤል ዮሐንስ ሽለማት ተበርክቶለታል።

በትናትናው ፕሮግራም ላይ በቡድኑ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጉዞ ላይ አስተዋፅኦ የነበረው እንዲሁም በአፍሪካ ዋንጫው #ከቡርኪና_ፋሶ ጋር በተደረገው ሦስተኛ የምድብ ግጥሚያ #የጨዋታው_ኮከብ ተብሎ ለተመረጠው እንዲሁም የአፍሪካ ምርጥ ተጫዋቾች ውስጥ መግባት የቻለው የኢትዮጵያ ቡናው የመሀል ሜዳ ሞተር አማኑኤል ዮሐንስ ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የተዘጋጀለት #የክሪስታል_ዋንጫ እና 150 ሺህ ብር ማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶለታል።

@bunawustiawaki
@bunawustiawaki