Get Mystery Box with random crypto!

'የኔ ያልሆነ!!!' ሊሂድ ባልሽኝ ቁጥር ስንቴ አንቺን ልሸኝሽ በር ድረስ ወጣው ሸኝቼሽ ስመለስ አ | የተሰበሩ ልቦችBroken Hearts💔

"የኔ ያልሆነ!!!"
ሊሂድ ባልሽኝ ቁጥር ስንቴ አንቺን ልሸኝሽ በር ድረስ ወጣው
ሸኝቼሽ ስመለስ አንቺን ነው የማገኘው እራሴን እያጣው
እንዴት አትይኝም!?
እንደ ዘበት መርሳት ላይችል አቅፎ ሰንበር
እንዴት ሄድሽ ልበል ትዝታሽ ጠብቆ እየከፈተልኝ በር

ግን ግን ..........
የሚለኝ አይጠፋም
ስቴድ ሸኝቷት ያዝናል እንዴ ደግሞ
መኖር ይባላል ወይ ካቀፉት ገላ ስር ልብ ሲሸሽ ደግሞ
አየሽ የኔን ህይወት
ከዕለት ለእለት እያደር ቢጠጥርም ከ አለት
ከመሄድሽ በላይ ትዝታን መርሳት ነው አንቺ የለሽም ማለት
አትጠራጠሪ

የሚሆነው ሁሉ ስለሆነ አይደለም ባንቺ የምቀጣው
የኔ ቢመስለኝም የኔ ያልሆነን ነው አግኝቼ የማጣው
ያለፍኩትን ታሪክ ባሻገረኝ ድልድይ ዘውር ብዬ ሳየው
በእርሱ ፍቃድ እንጂ በምኞቴ አይደለም ዛሬ የሚለየው አዎን እመኛለው
የተመኘሁትን አንቺን አግኝቻለው
ያገኘሁትንም አንችን አጥቻለው

ባጣሁት ነገር ላይ ፈፅሞ አልከፋም
ለምን እከፋለው
እንኳን የኔ ያልኩሽ አግኝቼ ላጣሁሽ
እኔ እንኳን እራሴ የእራሴው አደለው
ያ ደግሞ ምንድነው???
የሚሆነው ሁሉ ስለሆነ አይደለም ባንቺ የምቀጣው
የኔ ቢመስለኝም የኔ ያልሆነን ነው አግኚቼ የማጣው
  https://t.me/BrocknHearts