Get Mystery Box with random crypto!

የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ከሰኔ 27 እስከ 29 እንደሚሰጥ ተገለፀ የ2014 የ8ኛ ክፍል | Bright side consult & training

የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ከሰኔ 27 እስከ 29 እንደሚሰጥ ተገለፀ

የ2014 የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ከሰኔ 27 እስከ ሰኔ 29 ቀን 2014 ድረስ ለተከታታይ ሦስት ቀናት እንደሚሰጥ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ አስታውቋል።

ቢሮው በ2014 በከተማ አስተዳደሩ በ179 የመፈተኛ ጣቢያዎች 71 ሺህ 832 ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱና ለኹሉም ተማሪዎች አድሚሽን ካርድ መታደሉንም ገልጿል።

ከቢሮ ጀምሮ እስከ ፈተና ጣቢያዎች ድረስ የፈተናውን ሂደት የሚከታተል ኮማንድ ፖስት መዋቀሩም የተገለፀ ሲሆን ሰኔ 24 ቀንም ለኹሉም ፈተናውን ለሚመለከት የትምህርት ማህበረሰብ ኦረንቴሽን እንደሚሰጥም ተነግሯል፡፡